Get Mystery Box with random crypto!

🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨

የቴሌግራም ቻናል አርማ haniya_calligraphy — 🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨 H
የቴሌግራም ቻናል አርማ haniya_calligraphy — 🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨
የሰርጥ አድራሻ: @haniya_calligraphy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.59K
የሰርጥ መግለጫ

ውድና ተወዳጅ ቤተሰቦች በዚህ ቻናል ብዙ ነገሮችን እናገኛለን የ calligraphy ጥበቦች ያልተነበቡ አዳዲስ ታሪኮች ያገኛሉ ቀለል ያሉና አስተማሪ video ወ.ዘ.ተ
ለማንኛውም አስተያየት @hanuni_calligraphy_bot
የመወያያ ግሩፕ @hanan_calligraphy
እንዲሁም Instagram ላይ @Hanuni_h123follow በማድረግ አባልነታችሁን አሳዩን

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-06 14:39:34 ♡አላህን ጠብቅ፤ ይጠብቀሃል፤ አላህን አስታውስ ይስታውስህል ዓብደላህ ኢብን ዓባስ እንዲህ አለ፡ “የሆነ ቀን ከነብዩ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ኋላ ነበርኩ። ከዛም እሳቸው አንተ ልጅ ሆይ እኔ ንግግሮችን አስተምርሃለሁ አሉኝ።
አላህን ጠብቀው (አስታውሰው) ይጠብቅሃል። አላህን ጠብቀው (አስታውሰው) ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ። ከጠየቅክ (መጠየቅ ከፈለግክ) አላህን ጠይቅ። ከታገዝክ (አገዛን ከፈለግክ) በአላህ ታገዝ። ህዝቦች ሁሉ
አንተን ለመጥቀም ቢሰበሰቡ አላህ ካልጻፈው በቀር አይጠቅሙህም። ህዝቦች ሁሉ አንተን ለመጉዳት ቢሰበሰቡ አላህ ካልጻፈው በቀር አይጎዱህም። መጻፊያውም ተነስቷል። መጽሃፉም ደርቋል።”
ሓዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል።

ከቲርሚዚይ ውጭ በሆኑ ሌሎች ዘገባዎች ደግሞ : “አላህን ጠብቀው (አስታውሰው) ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ። በምቾት ግዜ አላህን ተዋወቀው በችግር ግዜ ያውቀሃል። ደግሞ እወቅ! የሳተህ ነገር ሊያገኝህ አልነበረም፥ ያገኘህ ነገር ደግሞ ሊስትህ አልነበረም። አሁንም እወቅ! ድል ከትዕግስት ጋር ነው፣ መገላገል ደግሞ ከችግር ጋር ነው፣ ከክብደት ቡሃላ ደግሞ ቅለት አለ።”
ሰው ሁሉ ተሳሳች ነው
‹‹ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ " ባትወነጅሉ ኖሮ እናንተን አጥፍቶ፣ እያጠፉ የአላህን ምህረት እየጠየቁ የሚምራቸው ሕዝቦች ይፈጥር ነበር"›› ሙስሊም ዘግበውታል

»ሰው ሁሉ ተሳሳች ነው ፣ስህተት ተፈጥሯዊ ተግባሩ ነው፣ ከነርሱ በላጩ ደግሞ ተመላሾች ናቸው።

‹‹ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ "የአደም ልጅ ሁሉ ተሳሳች ነው ከተሳሳቾች ሁሉ የበለጠ ደግሞ ንስሃ ገቢዎች ናቸው"›› ቲርሚዚይ ዘግበውታል
»አንተ ስታምፀው እርሱ ሊምርህ ጸጸትህን በናፍቆት ይጠብቃል! አንተስ ምህረቱን አልናፈክምን?
««አላህም ቃል ገባ ፦
""ባሪያዎቼ ሆይ! በየእለቱ በቀንና በሌሊት ወንጀል ትፈፅማላችሁ እኔ ሁሉንም ወንጀል እምራለሁ ። እናም ወንጀላችንን ማረን በሉኝ እምራችኃለሁ።""
رَبَّنَا فَاغْفِرْ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرْ عَنَّا سَيِّئَاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ الْأَبْرَارِ
«ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤» (አሊ-ዒምራን :193)
807 viewsibro smile , 11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:38:49 ቴሌግራምን ወደድኩት
.
ፌስቡክ ማለት ሁሉም እንደሻው የመጣለትን የሚናገርበት፣ ተራ ወረፋ የሌለው፣ አደብና ሥርዓት የማይታወቅበት፣ ምኑን ከምን የማትለይበት፣ ከሰው ሁሉ ተቀላቅለህ፣  ከጥሩ መጥፎ ተጋፍተህ፣  እየተጯጯህክ የ የምትኖርበት መድረክ ነው።
ቴሌግራም ደግሞ የብቸኝነት ዓለም ነው። ቤትህን ከፍ ባለው ጋራ ላይ ትሠራና " ኑ ብሉልኝ ጠጡልኝ" ብለህ ታዳሚዎችህን ትጠራለህ። መቼም እንግዳ ጠርተህ በመጥፎ ነገር አታስተናግድም። እንዲደሰቱብህ፣  ሳታውቅ ሳትሰማ ዱዓእ እንዲያደርጉልህ ብለህ እጅግ ጥሩ የሆነ ነገር ለማቅረብ ሽርጉድ ትላለህ።
.
የዚህ ቤት ባለቤት ያለ ልዩነት ሁላችሁንም ይወዳችኃል።
.
አላህ ፅናቱንና ጉልበቱን ይስጠን። ለፈጠረን አምላክ ብቻ ብለን ከወደድናቸው ጋር ሁሉ ያለ ወረት ያዝልቀን። ነገም "ኑ ለኔ ብላችሁ ተዋዳችኋልና በጥላዬ ሥር እረፉ" ብሎ ይጥራን።
.
አሚን ያ ረብ!

ibro smile
@Haniya_calligraphy
@Haniya_calligraphy
718 viewsibro smile , 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:38:10 የአላህ መሻትና የሰው መሻት

~ ዩሱፍን ሊገድሉት አስበው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ዩሱፍ አልሞተም። በአላህ ፈቃድ ተረፈ ።
~ ከሚወደው አባቱ ነጥለውና ከዐይኑ አርቀው እንዲረሳው ብለው ከአገር አስወጡት፤ ጭራሽ የአባቱ ፍቅር ጨመረ። በናፍቆት ብዛትም ዐይኑ ሊጠፋ ደረሰ።
~ ባሪያ ሆኖ እንዲቀር ብለው በትንሽ ገንዘብ አሳልፈው ሸጡት፤ ጭራሽ ቤተመንግሥት ገባና ሚንስቴር ሆኖ አረፈው።
.
የሚገርመው ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ቅናትና ምቀኝነት ያቃጠላቸው የገዛ ወንድሞቹ ናቸው።
.
ግና የአላህ መሻት ከሰው ልጅ መሻት በላይ ነውና ምንም ሊያደርጉት አልቻሉም።
የአላህ እጅ ከሌለበት፤ ሰዎች ሁሉ ሊጎዱህ ቢሰባሰቡና ቢያሴሩ ምንም ሊያደርጉህ አይችሉም።
እናም አትዘን ወንድሜ
አትዘኝ እህቴ

የአላህ ጥበቃ አይለያችሁ መልካም ቀን ይሁንላችሁ
.
716 viewsibro smile , 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 18:18:25
ጥሩ ነገር ላይ ሳትኖር ስትቀር
ወደ ጥሩ ነገር ጎትቶ የሚወስድህን
ጓደኛ አድርገህ ያዝ!

ሁሌም እኔ የናንተው ምርጥ ጓደኛ ነኝ!!
#ዉብ_ምሽት ይሁንላችሁ
798 viewsibro smile , 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 18:13:56 ምን መሰላችሁ! "አላህ ቆንጆ ቆንጆ ነገርን ብቻ ነው ከሱ የምንጠብቀው።' ይላሉ ዐሊ።

አዎ በጠረጠራችሁኝ ቦታ ታገኙኛላችሁ ብሏልና ደግ ነገርን ከአላህ እንጠረጥራለን፣ ይምረናል ብለን እንጠረጥራለን፣ ያዝንልናል ብለን እንጠረጥራለን፣ ኑሯችንን ያስተካክልልናል ብለን እንጠረጥራለን፣ ጀነት ያስገባናል ብለን እንጠረጥራለን። ችግራችን ሁሉ ተፈቶ ያድራል ብለን እንጠረጥራለን።
ብናጠፋም አላህ ዘንድ ሁሌም ልጅ ነን። ወደሱ እንጂ ከሱ ወዴት እንሄዳለን?።
በአላህ ላይ ማንም ሊፈታው የማይችለዉን መልካም ጥርጣሬ በልባችን ቋጥረን እንተኛለን።

እኔ ኑሮዬ እንዲህ ነው ወዳጆቼ፣
እናንተስ?
742 viewsibro smile , 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 18:13:14 በቀን አምስቴ ዉዱእ ካረግሽ ምንም ሜካፕ አያስፈልግሽም፣ ኑሩ ብቻ ይበቃሻል።
አደል እንዴ
@anbeb_Islamic
@anbeb_islamic
707 viewsibro smile , 15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 07:30:03
836 viewsĤĄŊÏŸª, 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 07:30:03
768 viewsĤĄŊÏŸª, 04:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 06:35:32
በጧት የመጀመሪያው ስራህ ፈገግ የሚያስብልህን ሰው ፈልግ ምክንያቱም የጧት ፈገግታ ምርጥ ቀን ይፈጥራል!
صباح الخير ..
@haniya_calligraphy
827 viewsĤĄŊÏŸª, edited  03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:44:31
ወላሂ ተአምርርርር ነዉ።ሱብሀነከ
1.0K viewsĤĄŊÏŸª, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ