Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴ ,.... ዝም ብሎ አንዳንዴ ዝም ብዬ አስባለሁ አብሰለስላለሁ ከራሴ አወራለሁ በሀሳብ | 🎨 HANIYA CALLIGRAPHY 🎨

አንዳንዴ
,....
ዝም ብሎ አንዳንዴ
ዝም ብዬ አስባለሁ
አብሰለስላለሁ
ከራሴ አወራለሁ
በሀሳብ እሄዳለሁ
ምን እሆን! እላለሁ
እጨናነቃለሁ
ተስፋም አደርጋለሁ …
……
የደረሰ ለታ የዚያ ሞት ቀጠሮ
ጌታዬ ሲጠራኝ ተራህ ደርሷል ብሎ
አውጥቶ ሲጥለኝ አንጀቱ ጨክኖ
ወገን ሲጨምረኝ ከጉድጓድ ቆፍሮ
አፈር ሲቆልሉ ድንጋይ ሲጭኑብኝ
ለናኪር ለሙንከር ብቻዬን ሲተዉኝ
ትተውኝ ሲሄዱ በነበር ተሣፍሮ
እላመደው ይሆን ያንን ከባድ ኑሮ!!
…..
ምን ይሆን ፈንታዬ ምን ይሆን ዕድሌ!
ጀነት ወይስ እሣት መግቢያ መቃብሬ?
ጠባብ ወይስ ሰፊ ጥቁሩ ማረፊያዬ?
ብርሃን ወይስ ፅልመት የብቻ ጓዳዬ?
ታየኝ በሀሳቤ ያ መጪዉ ሁናቴ
ሥጋዬ ፈራርሦ ስቀር በአጥንቴ
አጥንቴ አፈር ሲሆን ሲደቅ ሰውነቴ
ይመች ይሆን በርግጥ ሁለተኛው ቤቴ!!
……
እየቀረብኩ ነው ሳልወድ በግዴ
ጥርጥር የለውም እውን ነው መሄዴ
ቢደላኝ ባይደላኝ ጎጆዬን ልረከብ
ባሳለፍኩት ሁሉ አምላኬ ፊት ልቀርብ
……
የዱንያ ሁካታ ሩጫና ዉዥንብር
አስረስቶኝ እኔን የአኺራን ነገር
ጉራዬን ስጎርር ወሬዬን ስነዛ
ጊዜዬን ጨረስኩት በዋዛ ፋዛዛ

ወይ አለማወቄ ከንቱ ቢስ ልፋቴ
ብርሃን በእጄ የለኝ ለመሬት ሥር ቤቴ
ስንቅ አላሰናዳሁ ለረጅም መንገዴ
ትርፍ ሥራ የለኝ ኪሣራ ነው ንግዴ
….
አትጣለኝ ያ ረቢ አትራቀኝ በረሕመት
ምን አለኝና ካለአንተ እዝነት
የፊትናዋን አገር ዱንያን ለቅቄ
በስንብት ስሄድ ዘመድ ወዳጅ ርቄ
ኮንትራት ጨርሼ አልቆ ቆይታዬ
እንደ ሌሎች ሁሉ እኔም በተራዬ
ነጥለው ሲወስዱኝ ከሀብት ንብረቴ
በአንዲት አቡጀዲ ሲያስወጡኝ ከቤቴ
አጥበው ሲከፍኑኝ ለረጅም ጉዞዬ
ቀብር የገባሁ ለታ ጀናዛ ተብዬ

afdel