Get Mystery Box with random crypto!

እህቴ በእለተ ኢድ አል አድሀ አረፋ እህቴ ውድ እህቴ የተከበርሽ እህቴ እነዚህ | 🌹Islamic_deawa 🌹

እህቴ በእለተ ኢድ አል አድሀ አረፋ እህቴ ውድ እህቴ የተከበርሽ እህቴ እነዚህን ነገሮች አትዳፈሪ እህቴ አላህን ፍሪ ኢተቂላህ አላህን ፍሪ እነዚህን ከማድረግ ተቆጠቢ ከዛም አጠገብሽ ያሉትን አስጠንቅቂ ኢተቂላህ እህቴ ምን ያህል እንደማስብልሽ ወላሂ እህቴ በመንገዴ እኮ እናንተን የሚነካ ካለ አለቀውም በቻልኩት አቅም እታገለዋለሁ በአላህ ፍቃድ አሸናፊ ነኝ እነዚህን

1 እህቴ በአላህ ይሁንብሽ ወደ ሰላት ቦታ ከጥሩ ጓደኞችሽ ጋር ሂጂ እነዚያ ክብርሽን ዝቅ ስታደርጊ ደስ ከሚላቸው ጋር አትሂጂ አደራ እህቴ በአላህ

2 አደራ ታክሲም ላይ የትም ላይ ድምፅሽን ቀነስ አድርገሽ አደራ እህቴ ኢተቂላህ

3 አደራ ተክቢራ ስትዪ ከወንድ ጋር ተቀላቅለሽ እንዳይሆን በሴትነትሽ ድምፅሽን ዝቅ አድርገሽ አላህን አወድሺው እህቴ አደራ

4 አደራ ኢተቂላህ አላህን ፍሪ አላህን ፍሪ አላህን ፍሪ እህቴ ሰዎችን የሚጣራ ሽቶ ልብስ ጌጣጌጦች አደራ እህቴ የኢዱ ቀን እኮ አላህን የምናወድስበት የምናመሰግንበት ነው መሆን ያለበት ወላህ አንድ ቤት አውቃለሁ ለአረፋ እየተዘጋጁ ከቤታቸው አንድ ሰው ሞተ እና እህቴ አደራ አላህን ፍሪ

5 ኢተቂላህ እህቴ ወንድሞችሽን ወደ ዝሙት አትጥሪ እህቴ ኢተቂላህ በልብስሽ በጌጥሽ በሽቶሽ አደራ እህቴ ለዝሙት ብሎ የሚወጣ ወንድ አይጠፋም አንቺ ከተሰተርሽ ሀሳቡ አይሳካም አንቺ ግን ከተገለፅሽለት ያሀ ስሜቱ ይቀሰቀስበታል ከሸይጣን ጋር አንድ ላይ ያብሩበታል

6 አደራ እህቴ አላህን ፍሪ ከሰገድሽ በኋላ ከወንድጋር ሳትቀላቀይ ወደ ቤትሽ ከተቀላቀልሽ ሰዎች አሉ እነዚያ ለወሲብ ስሜታቸው የሚኖሩ መንገድ በተጨናነቀ ጊዜ ረጋጣሚውን በመጠቀም የእህቶቼን የተከበረ ሰውነት በቆሻሻ እጁ ይነካል አላህ እጁን ይያዘው እህት ምን ያህል ያስጠላል እህት ትወጂዋለሽ ይህን ተግባሩ መጥቶ የተከበረ ሰውነትሽን ሲነካ ደስ ይልሻል እህቴ በዚህ ወጥመድ ላለመግባት ጠንቀቅ በይ እህቴ


7 አደራ ከተሰገደ በኋላ በፍጥነት ወደ ቤት በመመለስ እኖቶቻችንን አቤቶቻችንን እንግዳዎቻችንን እንካድም ወላጆችን መካደም አላህን ማስደሰት ነው አደራ እናቴን ካድሚያት ያቺ በምድር ላይ ምትክ የሌላት አባትንም አደራ እንግዶቻችንን እናክብር ኢተቂላህ

8 የማከብርሽ የምጠነቀቅልሽ የምሳሳልሽ እህቴ ቀኑን በተክቢራ እንዳንረሳ አላህን እናስደስት አላህን እናጥራ ኢዳችን አላህን የምንገዛበት ነው መሆን ነው ያለበት አደራ እህት ስሜቱን ለሚከተል ወራዳ ፊት አትስጪ በሸሪአ አላህ በደነገገው ነብዩ ባዘዙት መሰረት ነው መሆን ያለበት እህቴ አላህን ፍሪ ኢተቂላህ




እህት ይህን ስፅፍ አንቺን በነዚህ ተግባራት ጠርጥሬሽ አይደለም ግን ሰው ይፈተናል በሁለት ነገሮች አንደኛው በደስታው አመቱን ወሩን በሙሉ እሱ ሚታወቀው በኸይር ስራው ነውየደስታው ቀን ባልጠበቅነው ቦታ እናገኘዋለን የአላህን ዲን ጥሶ ሁለተኛው ደግሞ በሀዘን ወቅት ሰዎችን በሰብር ያዝ ነበር በራሱ ሲደርስበት ሰዎችን ሲከለክል በነበረው ተግባር ይገኛል ለዚህ ነው እህቴ ተረዳሽኝ ? እህቴ አስብልሻለሁ እጨነቅልሻለሁ እህቴ እነዚህ ላለማድረግ ከልብሽ በአላህ ስም ቃል ግቢልኝ ፅሁፋ በኢተቂላህ ታጅቧል ይህን ከተዳፈርን ያሳዝናል እህቴ አላህ ይዘንልን ፈተናዎች ወደ እኛ ነጎዱ ወላሂ እኛ ደግሞ ቀን በቀን በአመፃችን ብሶብናል ማክሰኞ ወደ ቀራኒዮ አካባቢ የዘነበው ዝናብ ሀይለኛ እንደሆነ ሰምቻለሁ መስጂዶች አዛን እስከማለት ደርሰው ይህን ቢያንስ በእኔና በአንቺ ምክንያት ፈተና አይምጣ ለኸይር ሰበብ እንሁን




ውድ የተከበርሽ የምድር ማጣፈጫ ለህይወት ቅመም የሆንሽ እህቴ ይህን ፅሁፍ ለእህቶችሽ አስተላልፊ አደራ ሼር አድርጊ እህቶችሽንም አስጠንቅቂ አላህ ይጠብቅሽ አላህ ሁሉንም ኸይር ያድርገው ኸይሩን ያምጣልን ከሸረኞች ይጠብቀን ቃል ግቢ እህቴ

https://t.me/joinchat/KoYMWLdIV7AzNjk0