Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሶስት በጋብቻ ስም የሚሰሩ የሃራም መንገዶችና ሌሎች የማናስታውላቸው ወደ ሃራ | 🌹Islamic_deawa 🌹

ክፍል ሶስት


በጋብቻ ስም የሚሰሩ የሃራም መንገዶችና ሌሎች የማናስታውላቸው ወደ ሃራም የሚወስዱን መንገዶች።


በጣም ወሳኝ ማስታወሻ ሁሉም እህቶቻችን ማወቅ ያለባቸው እሳት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት።
ሃቅን ፈላጊ ለሆናችሁ እህቶቻችን ማስታወሻው ይጠቅማችኋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። እያወቁ ለሚያጠፉትም አላህ ሰበብ ያድርግላቸው።

የሃራም መንገዱን /መፍትሄውን /እና ምክር


ክፍል ሶስት

የሚገርመው ይሄን መንገድ ኒቃቢስቶች ሳይቀሩ እየተሸወዱበትና መጨረሻው ወደ ሃራም እየወሰዳቸው ነው ሚገኘው።

አንዳንድ ወንዶች አንዲትን ሴት አይተው ቁጥብ መሆኗን በተለያየ መንገድ ያውቃሉ በአላባበሷ ሊሆን ይችላል ወይም መስጅድ ስትመላለስ ሊሆን ይችላል እናም ወንዱ ቁጥብ መሆኗን ሲያውቅ በሃራም ለማግኜት መንገዱን ይጀምራል ከዛም ስልኳን ፈልጎ ወይም ከሷም በሆነ መንገድ ተቀብሎ እሷን የሚያሳምንበት የውሸት ሰበቦችን ይደረድራል። በዲኔ ደካማ ነኝ እንዳንቺ አይነት ጠንካራ እህት ያስፈልገኛል ፣ቤተሰብም የለኝም ፣ ሰዎችም አይወዱኝም እያለ በቃ የተለያየ ምክንያት በማቅረብ እንደማንም አሳዝኖ ከልጅቷጋ በፁሁፍ ማውራት ይጀምራል ከዛም በቃ እንደ እህትና ወንድም እንሁን ሌላ ምንም አልፈልግም ይላታል እሷም እውነት መስሏት እሽ ትለዋለች ከዛም መጀመሪያ ላይ ስለዲን ያወራታል ከዛ እየቆየ ወሬው ሁሉ ይቀየራል እሷም መቅረብ ካለባት በላይ ድምበር አልፋ ትቀርበዋለች አጅ ነብይ መሆኑንም ትረሳዋለች በዛ መሃል ልጅቱ በልጁ ትሳባለች ማለትም በፊት ሲያወራት በነሩት የውሸት የእዝነት ቃላቶች ተፅእኖ ይፈጥርባታል ከዛም ልጁ የሚፈልገውን ሃራም ነገር ካልሰጠችው እንደሚርቃት ይነግራታል ከዛም ልጁን ከማጣው ብላ ወደ ሃራም ግኑኝት ተገባለች። ከዛ መጨረሻው ዚና ይሆንና ህይወቷን አበላሽቶ ይርቃታል።
በተለይ ወንዶች አንዴ ዚና ካደረጉ ወዲያው ነው ከልጅቱ ላይ ያለው ፍቅራቸው የሚወጣባቸው ከዛም ልጅቱን እንደ ወሲብ እቃ በማየት ለስሜቱ ማራገፊያ ነው ሚጠቀማት ልጅቱም የሚወዳት እየመሰላት ህይወቷን መከራ ውስጥ ትከተዋለች መጨረሻውም መለያየት ነው ሚሆነው ምክያቱም አላህን አስከፍተን መቸም ጥሩ ነገር አናገኝም። በዚህ ምንገድ አልፈው ብንጋባ እንኳ ትዳራችን በፈተና የተሞላና የሚያስጠላ ነው ሚሆንው ምክንያትም ቤት ውስጥ በፊት የነበረውን ነገር ነው ሚያደርጉት ከዛም መሰለቻቸት ይመጣል ትዳር ማለት ደግሞ አብሮ መተኛት ብቻ አይደለም።

አያችሁ ሸይጧን ትንሽ ክፍትት ብቻ ነው ሚፈልገው!
ስህተቶችን ቶሎ ማረም ካልቻክን ወደ መጥፎ መዘዝ ነው የሚያስገባን።

ውድ እህቴ ወንድሜ ብለሽ ስለቀረብሽው የስጋ ወንድምሽኮ አይሆንም ወይም አጅ ነብይነቱ ሊጠፋ አይችክም ይሄ ትልቅ የሆነ ስህተት ነው ቁርዓን የሚያቀራሽ ቢሆን እንኳ ልቅ ሁነሽ ልትቀርቢው አይገባም አጅ ነብይሽ ነው እናም አላህን እንፍራ በዚህ ምንገድ በጣም በርካታ ሰዎች አሉ እና ድምበር አንለፍ ሃቁን እያወቅነው ስሜታችንን አንከተል። መጨረሻው ፀፀት ነው።

አንደኛ ልጁ በዲኔ ደካማ ነኝ ካለሽ መስጅድ ሂደህ ቅራ በይውም ከዛ ውጭ ደግሞ ከቻልሽ አንዳንድ የሱና ቻናል ላኪለትና ልጁን ብሎክ አድርጊው ከዛ ውጭ እንደ ቀላል አይተሻቸው አንዳንድ ነገር ምታወሩ ከሆነ አንደኛ ይሄ የሃራም ምንገድ ነው ሁለተኛ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄድሽ መሆኑ ልትረሽው አይገባም በሃራም ምንገድ በሃራስ መተማመን ሚባል ነገር የለም።

እና ውድ እህቴ እንደዚህ ልቅ ሁነሽ ቀርበሽው እንዴት ከወንድምና ከእህትነት ውጭ የሆነ ነገር አይፈጠርም ብለሽ ታስቢያለሽ? ይሄ ራስን ማታለል ነው አንዳንዶች ራሳቸውን ለመሸወድ ሲፈልጉ እኔ ከወንድምነት ወይም ከእህትነት ውጭ አልፈልግም ይሉና አቀራረባቸው ግን ልክ እንደ ባልና ሚስት ነው እናም ራሳችሁን አትሸውዱ ግንኙነታችሁ ወደ መጥፎ ነገር ከመቀየሩ በፊት ሁኔታችሁን አስተካክሉ።
በዛ ምንገድ ተቀራርባችሁ ወደ ትዳር መቀየር ፈልጋችሁም ከሆነ ቶሎ ወደ ትዳር ቀይሩት ከዛ ውጭ በዛ ስሜት ላይ ሁናችሁ ከቀጠላችሁ መጨረሻው እራስን እሳት ውስጥ መጣል እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም አላህን እንፍራ ወደ አላህ እንመለስ

አንዳንዶች ደግሞ እንደ እህት እንቀራረብ ይሉና ልጅቱን ወጥመድ ውስጥ ማስገባት ፈልገው ከግዜ በኋላ ወድጄሻለሁ ፍቅረኛ እንሁን ይላታል እሷም በማውራት ብዛት ልጁን ትወደውና እንዳይለያት በማሰብ አላህን አስከፍታ ግኑኝነታቸው ወደ ሃራም ይቀየራል ይሄ አንዱ የወንዶች ማጥመጃ ዘዴያቸው ነው። እንንቃባቸው

ሌላው እንደዚሁ እንደ እህት እንቀራረብ ብለው ከግዜ በኋላ አፈቅርሻለው ፍቅረኛ እንሁን ይላታል እሷም እንደ ወንድም ስለቀረበችው እኔ ከወንድምነት ውጭ አስቤህ ስለማታውቅ እንደዛ መሆን አንችልም ስትለው እሱም እሽ በቃ ትቸዋለሁ እንደ እህት እንቀጥል ይላታል እሷም እሽ ብላ እንደበፊቱ ትቀጥላለች። ውድ እህቴ እንዴት ብሎ ነው ፍቅር ይዞት ከነበረ ወደ እህትነት ሊቀየር የሚችለው? ይሄ ውሸት ነው እንደ በፊቱ እንቀጥል የሚልሽ አንቺን ወጥመድ ውስጥ ለመጣል ወይም ፍቅር አስይዛለሁ ብሎ ያልሆነ ነገር አደርጋለሁ ብሎ ስለሚያስብ ነው እናም ከዚህ የሸይጧን መንገድ ቶሎ እንራቅ


በዚህ ምንገድ በጣም ብዙ እህቶች ስህተት ይሰራሉ እየተሸወዱም ነው ከነሱ ትምህርት እንውሰድ!
እንደወንድም ተቀራርባችሁም ይሁን ድምበር ያለፋችሁ ካላችሁ ከዚህ ምንገድ ራሳችንን እናውጣ ገና እየገባንበትም ከሆነ ከዚህ ምንገድ እንራቅ። ካልገባንበትም ራሳችንን እንጠብቅ።
ቁጥብ መሆን ለራስ ነው ሚጠቅው።!

(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)


ክ ፍ ል አራት ይ ቀ ጥ ላ ል


በዚህ መንገድ ሌላ ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ እንዲሁም ይሄንንም መንገድ አስተላልፈው ትምህርት ይሆናል የምትሉት ካላችሁ በውስጥ ፃፉልኝ። ከሃራም መንገድ ለመውጣት ከአላህ በታች እገዛ ካስፈለጋችሁ ማማከር ትችላላችሁ።


@Jezakellah
@Jezakellah


ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

ለሴት ጓደኞቻችሁ በምትችሉት ሼር አድርጉት።
አንዲት ሴት ከ15 ላላነሱ እህቶች ሼር ታድርግ እንዲሁም በግሩፖች ሼር አድርጉት። ጀዛከላሁ ኸይረን


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ ፁሁፎች ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን
በዝሙት አንዘምን ๓
Join us on
telegram channel

https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina