Get Mystery Box with random crypto!

ዘመንኩኝ አትበይ ..... ዘመንኩኝ አትበይ ------??? ዘመንኩኝ አትበይ ወደ ኃላ ቀርተሽ፤ | 🌹Islamic_deawa 🌹

ዘመንኩኝ አትበይ .....
ዘመንኩኝ አትበይ ------???

ዘመንኩኝ አትበይ ወደ ኃላ ቀርተሽ፤
የተፈጠርሽበት አላማን እረስተሽ ፤

ዘመንኩኝ አትበይ የጨስኩኝ አራዳ፤
ድርጊትሽ መስካሪ ከሁሉ የሚያስረዳ፤
ዘመንኩኝ ባትይስ ከቶ ማን ይሰማሽ፤
በአደባባይ ሲታይ ደስ የማይለው ስራሽ፤

ማንኛው' ማንነው ማንነው አትበይኝ እህቴ፤
ለማንም አይደለም ለአንች ነው ስስቴ፤

እስኪ ተመልከችው ያረግሽውን ሂጃብ፤
ኧረ !ሂጃብ አልኩት እንዴ? የደረብሽው እስከርብ፤

እጅጉን ይገርማል የእህታችን ጉዳይ ፤
ፀጉሯ ተገላልጦ ሲታይ በአደባባይ፤
ሂጃብ ያልኳት ብጣሽ ተንጠልጥላ ከላይ፤

ደግሞ የሚገርመው በጣም የሚደንቀው፤
በአርቲፊሻል ዊግ ፀጉር አስመስላው፤
እፍረት የላት ጭራሽ እንደው ጉድ እኮ ነው፤

ሀቂቃው ይገርማል ምን ነክቶሽ ነው እህት፤
አለቃው ጅብራኤል መልዕክቱ ሲያወርዱት፤

ይህማ አይደለም መዘመን መሠልጠን፤
የነዛ መንገድ ነው የምዕራቦች ፋሽን፤

ኢስላም የሚያዝሽን የጥዋቱ የጥንቱ፤
እሡን በደንብ ያዥው ይጠቅምሻል እቱ፤
አንችኛዋ ደግሞ ጥግ ላይ ያለሽው፤
ለጅልባብሽ ጌጥም ሂጃብ የደረብሽው፤

ኧረ ለምን ሲባል ጅልባቡ ይደምቃል፤
ምን ነካሽ እህቴ በደመቀ ከለር ይሸበራረቃል፤

አንች የለበሽው የአኢሻ ጅልባብ፤
እንኳን ሊሽሞነሞን ከላዪ ሊደረብ፤
ቁርአን እንዳለሽ እንደታዘሽው፤
ሌላውን ተይና በላይሽ ልቀቂው፤

ጅልባብ ምን እንደሆነ ጠንቅቀሽ ተረጅ፤
ወንፊት ልብስ ለብሰሽ የትም አትሂጅ፤

የጌታሽ ፍራቻ በውስጥሽ ላይ ኖሮ፤
በሰይጣን ሽወዳ እንዳትይ እሮሮ፤

ከመጥፎ ተግባሮች ከሁሉም እርቀሽ፤
በቁርአን በሀዲስ ልብሽን አንፀሽ፤

ውስጠ ኻቲማሽን እንዲያምር ከፈለግሽ፤
ዘመን ያመጣውን ወደ ኃላ ትተሽ፤
መኖር ያዋጣሻል ትዕዛዙን ተግብረሽ፤
በኹሹዕ በኢማን ፈጣሪሽን ታዘሽ፤

ከቁርዓን ከሀዲስ ቀደም ቀደም አትበይ፤
ቁጭ ብለሽ ተማሪ ዘመንኩኝ አትበይ፤

ኡሙ አብደላህ

t.me/umumahi1