Get Mystery Box with random crypto!

የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamreel — የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamreel — የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @hamreel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.69K
የሰርጥ መግለጫ

የ ኢ/ኦ/ተዋህዶ/ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የጠበቁ የ አባቶች ምክር;ግጥም;ተከታታይ አምዶች;ልሳነ ግእዝ;ጥያቄናመልሶች የምናገኝበ ስለሆነ ቻናሉን ይቀላቀሉ። for any opinion @Abeln ይላኩ
"ይህች ቤተክርስቲያን
ክርስቶስን ከቶ አታውቀውም" በሉ
ግድ የለም ለቃሉ !
ግን ድምጽ ቀንሱ !
የጌታን መከራ ሕማሙን አስባ
ስግድት ላይ ናትና ልጆቿን ሰብስባ
ግድ የለም አንቋሿት
ግን አትረብሿት !!

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-02 15:28:14 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ለቋሚ ሲኖዶስ ማብራሪያ ሳይሰጡ ቀሩ!

በመስቀል አደባባይ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ቋሚ ሲኖዶስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ጋር ዛሬ ጥር 25/2014 ዓ.ም ሊያከናውነው የነበረው ውይይት ከንቲባዋ በጠየቁት የውይይት ቦታ ለውጥ ምክንያት ሳይደረግ ቀርቷል።

ቋሚ ሲኖዶሱ መንበረ ፓትርያርክ ውስጥ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ውይይቱን ለማድረግ እየተጠባበቀ የነበረ ቢሆንም ከንቲባዋ ቦታው ወደ ሸራተን አዲስ ሆቴል ይቀየር በማለታቸው ምክንያት ውይይቱን ለማድረግ እንዳልተቻለ ታውቋል።

ከ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጀምሮ የቀድሞ የከተማዋ ከንቲባ እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ባለስልጣናት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር የሚኖራቸውን ውይይት ወደ መንበረ ፓትርያርክ በመመጣት ሲያከናውኑ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን የዛሬው የከንቲባዋ ድርጊት ሊቃነ ጳጳሳትን ያሳዘነ ደርጊት ሆኗል።

ምንም እንኳን ከንቲባዋ በውይይቱ ላይ ባይገኙም ቋሚ ሲኖዶሱ ግን ስብሰባውን እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን እኛም ጉዳዩን እየተከታተልን አስፈላጊውን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
1.3K viewsአቤል ታደሰ, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 20:36:55 "አሁን እየጾምክ ነው? እስቲ ጾምህን በተግባር አሳየኝ? የቱን ሰራህ? ድሃውን ባየህ ጊዜ ምህረትን አሳየው። ጠላትህን ስታየው ታረቀው። ስኬታማ የሆነ ወንድምህን ስታየው አትቅናበት በመንገድ የምትሔድ ሴትን ስታይ ዝም በለህ እለፋት። በአጠቃላይ አፍህ ብቻ አይጹም ነገር ግን ዓይንህ፣ እግርህ፣ እጅህ ሁሉም አካልህ ይጹም። እጅህ ከመስረቅና ከስስት ይጹም፣ እግሮችህ ወደ ኃጢአት ከመጓዝ ይከልከሉ፣ አይኖችህም በሌሎች ሰዎች ውበት ላይ ተተክለው ከመዋል ይጹሙ።

አሁን ስጋ እየበላህ አይደለም አይደል? በዓይንህም መጥፎ ነገር አትመልከት፤ መስማትንም ጹም። የፈውስ ጾም ክፉን አለመስማት የሌሎችንም ስም አለማጥፋት ነው። አንደበትም ከክፉና ከአጸያፊ ንግግር ይጹም። የዶሮና የአሳ ስጋ ከመብላት እንከለከላለን ነገር ግን የወንድማችንን ስጋ ስናኝክና ስንበላ እንውላለን። የወንድሙን ስጋ የሚበላ ደግሞ የተረገመና አሳች ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” እንዳለን። ገላ.5:15

ሆዳችንን ከምግብ ብቻ ባዶ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን ሁለንተና ሕይወታችንን ራሳችንንም የምንቆጣጠር እኛ ወደ መንፈሳዊ ነገሮች የምንመራ መሆን አለብን።"

(የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን ውርስ ትርጉም #መምህር_ንዋይ_ካሳሁን)
1.3K viewsአቤል ታደሰ, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-21 20:37:07 #ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘነሐሴ_ኪዳነ_ምሕረት

፩/ ነግሥ ( ለኲልያቲክሙ )

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡

ዚቅ፦

ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፨ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፨ ከመ ትኵኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ፨ ለሕይወት ዘለዓለም ፨ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ ፨ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

፪/ ነግሥ ( እምጌቴሴማኒ ፈለሰት )

እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤
ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን፤
አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤
ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤
እመቅድሀ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን፤
ወበውስቴታ ተሠርዓ ቊርባን፡፡

ዚቅ፦

ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል ፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጐላት ፨ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፨ እንተ ሠረፀት ለሕይወት፡፡

፫/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ኪዳነ ምሕረት )

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ተሐደሰ፤
እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤
ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቊዓኪ አንሰ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤
እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡

ዚቅ፦

ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፨ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፨
ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፨ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፨ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።

ወረብ፦

ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤
በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ
ወዓሊ።

፬/ ለዝክረ ስምኪ ( መልክአ ማርያም )

ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኒ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትእዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡

ዚቅ፦

ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፨ ወልድኪ ይጼውዓኪ፨
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡

ወረብ፦

ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት፤

ወልድኪ ወልድኪ ይጼውዓኪ ውስተ ሕይወት ወምንግሥተ ክብር።

፭/ ለእስትንፋስኪ ( መልክአ ማርያም )

ሰላም እስትንፋስኪ ዘመዐዛሁ ሕይወት፤
ከመ መዐዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፥
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት፡፡

ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፨ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፨ ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡

ወረብ፦

ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል መዓዛ አፉሃ ታንሶሱ፡፡

፮/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ፍልሰታ )

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤
ወዘኢይነጽፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤
ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤
ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤
ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ ፡፡

ዚቅ፦

ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ማኅደረ መለኮት ፨እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ሰማያዊት ፨ እንተ በምድር ታንሶሱ፡፡

ወረብ፦

ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤
ማኅደረ መለኮት ጽርሕ ንጽሕት።

+++++ አንገርጋሪ +++++

ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፥
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፡፡

ወረብ ዘአመላለስ፦

ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤

ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ወይቤላ ሠዓለም፡፡

+++++ ዘሰንበት +++++

የማነ ብርሃን ኀደረ ኀበ ማርያም ድንግል፨ጥዕምት በቃላ ወሠናይት በምግባራ፨ እሞሙ ለሰማዕት ፨ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፨ እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን ፨ መድኃኒተ ኮነት ለኵሉ ዓለም፡፡

አመላለስ፦

እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን ፤
መድኃኒተ ኮነት ለኲሉ ዓለም።

+++++ መዝሙር ++++++

ሃሌ በ፰ እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ፨ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፨
ጸቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፨ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ ፨ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ።

መልካም በዓል
1.8K viewsአቤል ታደሰ, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-19 09:37:38 በደበረ ታቦር በዓል #ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሃይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
1.3K viewsአቤል ታደሰ, 06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-12 09:15:55 ነሐሴ፮ - የዕለቱ ምንባባት
ዘቅዳሴ
፩ኛ ቆሮ ፫፡፲ ወበከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር
፩ኛ ጴጥ ፫፡፩ ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና
ሐዋ ፲፮፡፲፫ ወወፃዕነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሀገር
ምስባክ መዝ ፵፬፡፲፪-፲፫
ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን
ትርጉም
የጢሮስ ሴት ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል፣ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ፣ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው።
ወንጌል፡ ዘማርቆስ ፲፮፡፱
ቅዳሴ፡ ዘእግዝእትነ አው ግሩም
1.1K viewsአቤል ታደሰ, 06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-25 20:55:19 ሥርዓተ ማኅሌት_ዘሐምሌ_ቂርቆስ  ( ዘሐምሌ ፲፱ )

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ገብርኤልና ለቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ነግሥ

ሰላም ለአቍያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን፤
አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን፤
ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን፤
ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ ዕብን፤
ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡

ዚቅ፦

ሃሌ በ፫ ፤ አንቃዕዲዎ ሰማየ፤ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ ፤ ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ ፤ እጼውዓከ እግዚእየ ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር እጼውዓከ ቅዱስ እግዚእየ ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር፤ እጼውዓከ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ።

ነግሥ

ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤
ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤
ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤
አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤
እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡

ዚቅ፦

ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ወብሥራት ለገብርኤል፤ ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

ነግሥ

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ፦

ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ፤ ኀደረ ላዕሌሃ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ።

መልክአ ቂርቆስ

ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን፤
ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን፤
ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን፤
ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን፤
ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡

ዚቅ፦

ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ፤ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ፤መላእክት ይትዋነይዋ፤ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ፤ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን፤እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።

ወረብ፦

ኢየሉጣ ወለደት ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት፤
ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ።

መልክአ ቂርቆስ

ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ፤
እንተ ተመትረ እምጒንዱ፤
ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ፤
ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ፤
ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ።

ዚቅ፦

ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ፤ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጐድጓደ ክረምት፤ ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት።

ወረብ፦

ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ፤
ድምፃ ለጽሕርት ለጽሕርት ከመ ነግጐድጓደ ክረምት/፪/

መልክአ ቂርቆስ

ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ፤
ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ፤
ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ፤
መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ፤
ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ።

ዚቅ፦

ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ፤ነበልባለ እሳት፤ ኢትፍርሂ እም ፤ ንፈጽም ገድለነ።

ወረብ፦

ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት፤
ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም።

መልክአ ቂርቆስ

ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ፤
ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ፤
በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስእለትከ መብረቅ፤
አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ፤
ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ።

ዚቅ፦

በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት፤ ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር ጽዋዓ ሕይወት፤ ወሀቦሙ መገቦሙ ወመርሆሙ፤እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡

ወረብ፦

በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት፤
ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ።

መልክአ ቂርቆስ

ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ፤
እለ ሥዑላን በነድ፤
አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ፤
ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ፤
ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡

ዚቅ፦

በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም፤ ወኢብድብድ በሰብእ ፤ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ፤ ወኢዓባረ እክል ፤ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ፤ወልደ አንጌቤናይት፡፡

ወረብ፦

በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ፤
ባርካ #ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን።

መልክአ ኢየሉጣ

ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ፤
ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ፤
ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ፤
ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ፤
ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ።

ዚቅ፦

ሃሌ ፫ ፤ሰላማዊት ሰላም ለኪ፤ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ፤ኢየሉጣ እምነ ፤ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ ሰአሊ ለነ፤ አስተምሕሪ ለነ፤ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡

መልክአ ገብርኤል

ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ፤
ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ፤ ገብርኤል ውኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ፤
አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ፤
ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ።

ዚቅ፦

ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት፤ ወበላሕኮሙ እምእሳት፤አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ እምዕለት እኪት።

ወረብ፦

ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት፤
እግዚኦ አድኅነነ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እም ዕለት እኪት።

አንገርጋሪ

ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እእም
ነበልባለ እሳት ዘአድኃኖሙ
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ።

አመላለስ

ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል፤
ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ።

እስመ ለዓለም

ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ፤ አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ፤ በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ ፤  አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን፤  ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም፤  አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን፤ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ እቶን፤አኃዛ  ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሐበ ቅድመ መኰንን ፤ አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን ፤ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ፤ እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ፤ አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን፤አእኰትዎ ወሰብሕዎ ወባረክዎ ለአብ፡፡

አመላለስ

አእኰትዎ ወሰብሕዎ፤
አእኰትዎ ወሰብሕዎ።

አቡን

ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን ፤ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን ፤ እንዘ ሀሎ ውስተ ምኵናን ፤ ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን ፤ይቤላ ሕጻን ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ጥብዒኬ ፤እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ፤ ከመ ንርአይ ገጾ ለአምላክነ ፤ይቤሎ ሕጻን ለእግዚኡ ዘመጠነዝ ገድለ ተጋዲልየ ፤  ምንተኑ ተዓሥየኒ ፤ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ፤  ይቤሎ እግዚኡ ለሕጻን አዓሥየከ ዘሀሎ ውስተ ልብከ፤ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ፤ ይቤሎ ሕጻን ለእግዚኡ ኢትቅብር ሥጋየ ዲበ ምድር ፤ ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ይቤሎ እግዚኡ ለሕጻን አልቦ ዘየዓብየከ በመንግሥተ ሰማያት፤  ዘእንበለ ዮሐንስ መጥምቅ ፤ ወአነፈጣሪከ ወዓዲ ከመ ኢይማስን ዲበ ሠረገላ ኤልያስ ህየ አነብረከ።

ዓራራይ

ጸርሐ ሕፃን ኀበ እግዚኡ እንዘ ይብል ፤  ዘመጠነዝ ገድለ ተጋዲልየ ምንተኑ ተዓሥየኒ ፤ አዓሥየከ ዘሀሎ ውስተ ልብከ ፤ ዘሐነፀ መርጡሉከ ወገብረ  ኢየኀጉል በኀቤከ ወበኀቤከ ፤ ወዓዲ ከመ ኢይማስን ሥጋከ ዲበ ሠረገላ ኤልያስ ህየ አነብረከ።
1.5K viewsአቤል ታደሰ, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-30 21:04:42 የማይታመም የርሱን ሕማሙን እንናገራለን፣የማይሞት የርሱን ሞቱን እንናገራለን፣የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ሕሊናም ይመታል!"
እጅን ወደኋላመታሰር፡- ሰው እጁን ወደ ኋላ ቢታሰር ልቀቁኝ፣ ምን አደረኩ፣ አለቃችሁም እያለ ይዝታል፣ ለመፈታትም ይታገላል። ክርስቶስ ግን ይህን አላደረገም በቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት ”እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት፣ እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፣ ሊፈርዱበት በአደባባይ ተቀመጡ። ”ሲል እንደተጻፈ ሁሉን በሥልጣኑ ማድረግ የሚችል ጌታ ዝም ብሎ በፍቅር ተጎተተላቸው።
በገመድ መጎ’ተት፡- መጎ’ተት ድካምን ያበረታል፣ ሰውነትን እየከረከረ ከባድ ስቃይን ያደርሳል፣ ያቈስላል፣ አካልን ይልጣል፣ እንኳን ለሰው ልጅ ለእንስሳት እንኳን ምን ያህል ከባድ ነው?ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ይህን ስለ ፍቅር ታገሠ።
ምድር ላይ መውደቅ፡- ከምድር ላይ መውደቅ ለእሾህ እና ለጠጠር ያጋልጣል። በሰዎች ዘንድም መሳለቂያ ያደርጋል። ምንም ባልቀመሰ፣ ውሃን እንኳን ባልቀመሰ ሆድ ሲሆን ደግሞ ስቃይ ይበረታል።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ይህን ስለ ፍቅር ታገሠ።
ልብስን መገፈፍ፡-ሰው እርቃኑን በልብሱ ይሸፍናል፣ ማዕረጉንም በልብሱ ይገልፃል። ለከዋክብት የብርሃን ልብስ ያለበሳቸው እርሱ ግን በዕለተ ዓርብ እርቃኑን በቀራንዮ አደባባይ አቆሙት።ይህንንም ስለ ፍቅር ታገሠ።
ምራቅ ሲተፉበት መታገስ፡- ምራቅ መትፋት ሰውን ያስቀይማል፣ ጥላቻንና ንቀትን ያሳያል። የዕወሩን ዓይን ያበራ እርሱ በፊቱ ላይ ተተፋበት። ቅዱስ ኤፍሬም “ለእኛ ፊት ክብርን የሰጠ እንዳንተ ያለማን አለ? የዕውሩን አይን ስታበራ እንኳን አርአያችንን አክብረህ ወደ መሬት ተፋህ እንጂ በፊቱ ላይ አልተፋህበትም” ሲል ገለጸ።እነርሱ ግን ይህን ድንቅ የሚያደርግ ጌታ ተፉበት እርሱም ስለፍቅር ታገሣቸው።
በጥፊ መመታት፡-በጥፊ መመታት ንዴትን እልህን፣ብሶትን ቀስቅሶ ለድብድብ ይጋብዛል፣ ትዕግሥትን ይፈታተናል።እርሱ ግን ስለወደዳቸው ፈንታ በጥፊ ሲመቱት ምንም አልመለሰም።
ጀርባን መገረፍ፡-በጅራፍ መገረፍ ይለበልባል፣ሰውነትን ያቆስላል።ጅራፉ ጫፍ ላይ ስለት ሲኖረው ደግሞ ስቃዩን ማሰብ ይከብዳል።ስጋውአልቆ አጥንቱ እስኪታይ ቢገርፉትም እርሱግን ይህንንም ስለፍቅር ታገሠ።
ራስን በዱላመመታት
የእሾህ አክሊል መድፋት፡-አንዲት እሾህ ስትወጋን እንኳን ሰውነታችን ላይ ታላቅ ህመም ይፈጥርብናል፡እሾሆችን ሰብስቦ አክሊል ሠርቶ በራሱ ሲያደርጉበት ስቃዩ እንዴት የከፋ ይሆን?ለሱራፌል የብርሃን ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ አክሊል አቀዳጁት።ይህንንም ስለፍቅር ታገሠ።
መስቀል መሸከም
በችንካር መቸንከር
በመስቀል ላይመሰቀል
መራራ ሐሞትንመጠጣት፡-ሐሞት መራራ ጣዕም ያለው ሲሆን ተጠማሁ ባላቸው ጊዜ መራራ ሐሞትን ሰጡት።
2.1K viewsአቤል ታደሰ, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-29 21:57:25 #ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚባላ ንፍሮ ነው፡፡ የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር፤ አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት፤ ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበርና ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል፡፡

በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል፡፡ ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል፡፡

(ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002)
1.5K viewsአቤል ታደሰ, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-29 10:03:07 #የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ

#ጸሎተ_ሐሙስ
በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17)

#ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡
1.6K viewsአቤል ታደሰ, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-03-28 08:18:25 #መጻጉዕ- የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት

በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው "ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም" አለው። "ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ" ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ "የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ" እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ "በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና "በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ" እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡

ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

#የዕለቱ_ምንባቦች፦
1ኛ. የቅ.ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላ. 5÷1-26
2ኛ. የቅ. ያዕቆብ መልእክት 5÷14-20
3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3÷1-12

#የዕለቱ_ምስባክ፦
መዝ 4ዐ(41)÷3
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።

(እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡) መዝ 4ዐ÷3 የሚለው ይሆናል፡፡

#የዕለቱ_የወንጌል፦
በዮሐንስ ወንጌል 5፥1-25 ድረስ ያለው ነው፡፡

ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታች ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡
2.5K viewsአቤል ታደሰ, edited  05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ