Get Mystery Box with random crypto!

በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያ | የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የደንግል ማርያምን ፅንሰቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተደላ እንደሚሆን ነገረው፡፡

ይህ ጻድቅ ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ፤ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበረ፤ የእስኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና፡፡

እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር፡፡ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሄር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ፡፡

የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሲጸልይና ሲማድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ፡፡ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷም ድኅነት የሚሆንባን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች፡፡

በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚህች ቀን የከበረች ቅድስት ሐና ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ፀነሰች።
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር