Get Mystery Box with random crypto!

ድምጽን ከፍ በሚደረግባቸው (ጀህሪይ) ሶላቶች ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም አብሮ ከፍ ይደረጋል ወይስ በ | (Hamid Al_ashariy

ድምጽን ከፍ በሚደረግባቸው (ጀህሪይ) ሶላቶች ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም አብሮ ከፍ ይደረጋል ወይስ በዝግታ ነው ወይስ ከእነ ጭራሹ አይቀራም?

ሶላት አሰጋገድ ውስጥ በመቶዎች ኺላፎች (የሊቃውንት) ልዩነቶች አሉ:: ከእነዚህ ውስጥ አንዱ በጀህሪይ ሶላቶች ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም ድምጽን ጎላ ተደርጎ ይነበባል ወይ የሚለው ነው::
-> ከእነ ጭራሹ አይቀራም የሚሉ ውሱን ዑለሞች አሉ::
-> ሀንበሊዮች ድምጽን ዝቅ ተደርጎ ይነበባል የሚለውን ይዘዋል::

የሁለቱ መረጃ የአነስ ኢብን ማሊክ ሀዲስ ሲሆን ከነቢዩ ﷺ ከአቡበክር, ከዑመርና ከዑሥማን ጋር ሰግጃለሁ:: ሶላትን በአልሃምዱሊላሂ ረቢል ዐለሚን ነው የሰገዱት ይላል:: ሀዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል::

-> ሻፍዒዮቹ በአቡሁረይራ ሀዲስ ነው የሄዱት:: ከነቢዩ ﷺ ከአቡበክር, ከዑመርና ከዑሥማን ጋር ሰግጃለሁ:: ሁሉንም ሶላት በ ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም ነው የሰገዱት ብለዋል:: ይህ ሀዲሱ የተረጋገጠ ሶሂህ ነው::

ሻፍዒዮቹ <<ካልሰማው አነስ ኢብኒማሊክ የሰማው አቡሁረይራ ሀዲስ ይጠነክራል:: ካልሰማማ አልሰማም:: ሰማሁኝ ያለ ታማኝ ከተገኘ በቂ ነው>> ይላሉ::

ከሊቃውንቱ ከፊሉ አነስ ኢብን ማሊክ ያልሰማው ምናልባት ከሗላ ይሰግድ ስለነበርና ነቢያችን ﷺ ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂምን ድምጻቸው ዝቅ አድርገው ቀርተውት ስላልሰማ ስለሚሆን ድምፃችንን ዝቅ እናድርግ እንጂ አንተወውም በሚለው የሄዱ አሉ::

በዘካ, ንግድ, ኒካህ, ሀጅ የሀነፊይ መዝሃብ ሲመረጥ ሶላት ላይ ደግሞ የሻፍዒይ ይመረጣል:: በመሆኑም ቢስሚላሂ ራህማኒ ራሂም በየቁርአኑ መግቢያ መደጋገሙ ልዩ ትኩረት ስላለው በግልጽ ማድረጉ ይወዳል በሚለው የሀበሻ ዑለሞቻችን ሄደዋል:: ወሏሁ አዕለም ወአህከም
https://t.me/hamid_al_ashariy