Get Mystery Box with random crypto!

«አንድን ሰው በግፍ የገደለ እሱም በተመሳሳይ መንገድ ይገደላል።» አለ ዐሊይ አቡጧሊብ (ረዐ) ከእ | (Hamid Al_ashariy

«አንድን ሰው በግፍ የገደለ እሱም በተመሳሳይ መንገድ ይገደላል።» አለ ዐሊይ አቡጧሊብ (ረዐ)
ከእሱ በፊት ዑስማን (ረዐ) ተገድለው ነበር። ዐሊይም (ረዐ) የዑስማንን (ረዐ) ገዳዮች ገደላቸው።
ቀጥሎም ዐሊይ (ረዐ) ተገደለ። የእሱን ገዳዮች ደግሞ ሙዓዊያህ (ረዐ) ገደላቸው።
ከዚያም ሑሰይን (ረዐ) ተገደለ። የሑሰይንን (ረዐ) ገዳዮች ደግሞ ሙኽታር አል-ሰቀፊ ከየቤቱ እየለቀመ ሰቀላቸው።
ሙኽታር ነቢይ ነኝ ብሎ የተነሳ ሰው ነው። ነገርግን አላህ በሙርተድ እጅ ለተበደሉት በቀሉን አነሳ።
በእርግጥ የጊዜ መቀዳደም ሁሉም የእጁን ያገኛል።
«አላህንም በደለኞች ከሚሰሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ።»
(ኢብራሂም 42)

https://t.me/hamid_al_ashariy