Get Mystery Box with random crypto!

ቋሚ ተሰላፊው ጅህልና ሁሌም ወንጀልና ሙሲባ (በላ) ባለበት ቦታ ቋሚ ተሰላፊ በመ | ሐምዱ<=>ቋንጤ

ቋሚ ተሰላፊው ጅህልና


ሁሌም ወንጀልና ሙሲባ (በላ) ባለበት ቦታ ቋሚ ተሰላፊ በመሆን የሚያገለግል መሳሪያ ቢኖር ጅህልና ነው።

የትኛውም ዓይነት ወንጀል ሲሰራ ለዝያ ወንጀል መገኘት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ጅህልና አይቀሬ ምክንያት ነው።

የትኛውም ዓይነት ሙሲባ ሲከሰት ለዝያ ሙሲባ መከሰት ምክንያት ተደርገው ከሚጠቀሱ ነገሮች ጅህልና አይቀሬ የሆነ ምክንያት ነው።

ለምሳሌ……
ከወንጀሎች ብናይ፦
ስለ ክህደት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ቢድዓ ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ዝሙት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ምቀኝነት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።


ከሙሲባ ብናይ፦
ስለ ፊርቃ ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ጠላት መሰለጥ ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።
ስለ ጀሀነም መግባት ከተወራ…
ጅህልና አንዱ ምክንያት ነው።

ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች በዋነኝነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዱ ይህ ጅህልና (አለማወቅ) ከሆነ ይህንን በሽታ ከራስ ለማስወገድ መጣር (መማር) የእያንዳንዱ ሙስሊም ግዴታ ይሆናል።

ጅህልና የሚባለው ነገር በ2 መልኩ ልናየው እንችላለን።
1ኛው, አለ ማወቅ ወይም አለ መማር ሲሆን፤
2ኛው, ባወቁት አለ መስራት ይሆናል። ምክንያቱም "ዕውወት" ማለት የተሸመደደው ሳይሆን የጠቀመው ነው።

https://t.me/joinchat/Q0mf35Z6QEmajDQB