2022-08-31 10:58:31
ዳግማዊት ራህመት
ደራሲ ኢሳቅ ሀብታሙ
ክፍል አንድ
ስሜ ሪድዋን ይባላል ውልደትና እድገቴ በጅማ ዞን በምትገኘው ጮጬ በምትባል አከባቢ ነው ጮጬ በቡና ታዋቂ ናት ካሊድ የተባለው ፈየል ጠባቂ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡናን ያገኘው በዚህች አከባቢ ነው ብዙ የውጭ አገር ዜጎች ለጉብኝት ይመጣሉ ከታ ሙዱጋ ይባላል የሚጎበኘው ቦታ ህዝቡም ቢሆን እንግዳ ተቀባይ ነው ስለ ጮጬ ይሄን ያህል ካልኩ ይበቃኛል አሁን ስለራሴ ትንሽ ልበላቹ በተፈጥሮ የተሰጠኝ ፀጋ የግጥምና የልቦለድ ደራሲ ነኝ ለትምህርት ቤታችን ግጥም አቅርቤ ነበር እናም ያጋጠመኝ ነገር እስካሁኑ በአዕምሮዬ ይመላለሳል አንዲት እብድ ልጅ ተደብቃ በጠጠር ወገቤን ትመተኛለች ከዛም እሷ እንደሆነች ሳውቅ
ችግር አለ እንዴ እህት
አዎ በጣም እንጂ
የሚነገር ወይስ የማይነገር
የሚነገር ለማንኛውም ራህመት እባላለሁ ጓደኞቼ ራሙ ይሉኛል ከተመቸህ አንተ ደግሞ ራሚ ብለህ ጥራኝ
ሪድዋን እባላለሁ ንገሪኛ
ፈርምልኝ አድናቂ ነኝ
ልብሽ ለይ ከሆነ ነዋ
እረ ደፋር ቻው በቃ ብላ ተሰናበተችኝ
ከዛ ቡኃላ ስለሷ ማሰብ መጨነቅ ጀመርኩ ሌቱን በፊልም ካሳለፍኩ ቡኃላ አርፍጄ ትምህርት ቤት ሄድኩ በትምህርት ቤታችን ህግ መሰረት ያረፈደ ጊቢ ያፀዳል እኔም አልቀረልኝም ነበር ልክ ትዛዛችንን እንደጨረስን ደብተር ወዳስቀመጥንበት ሩጫ በዚ መሀል ከአንዲት ልጅ ጋር ግንባር ለ ግንባር ተጋጨን ቀና ብዬ ሳይ ያቺ ራህመት የሚሏት እብድ ናት ለስለስ ባለ አንደበት
ኦ ይቅርታ አልታየህኝም ነበር
በቁመትማ አልታማም
እረ ባክህ አልቀረብህም
አንቺ ቀልጂ እኔ ፈተና አለብኝ ቻው ብዬ ወደ ክፍሌ ገባው ፈተናውን ኮርጄም ቢሆን ሙሉ አገኘው እረፍት ሰዓት ለይ ልወጣ ስል ራህመት ወደ ክፍላችን መጣች ለምን ይሆን?ክፍሌን ደግሞ የት አወቀችው ?
ወደኔ የቀረበች ስትመጣ ይበልጡኑ ግራ ተጋባው አማረኛ ደብተሬን ይዛ ነበር የመጣችው ደግሞ ከየት አገኝታው ይሁን እረ ወይ መልሱን አላገኘ ወይ መጠየቄን አላቆም ለነገሩ መጠየቅ እንኳን ጥሩ ነው አልበርት አንስታይን እንዲህ ይላል
ከትላንት ተማር ዛሬን ኑር ነገን ተስፋ አድርግ ግን ሁሌም ቢሆን መጠየቅህን አታቁም በሌላም ንግግሩ እኔን ከሰዎች ለየት ያደረገኝ ነገር ሰዎች በአምስት አመታቸው መጠየቅ ያቆሙትን ነገር መጠየቄ ነው ስለዚህ መጠየቅ ክፋት የለውም እሷም መጣችና
ይህው አማረኛ ደብተርህ
ከየት አገኘሽው
ያው ከደቡብ ሱዳን ነዋ እዚህው ጎረቤታችን ጋር
የቀለድኩ አይደለም
ደብተርህን የማን ሻንጣ ለይ ነው ያስቀመጥከው
የአንቺ ሻንጣ ለይ ነዋ
የሆነ ነገር ላስቸግርህ
የምችለው ከሆነ
በደንብ ትቸለዋለ
እሺ ምንድ ነው?
ግጥም ፃፍልኝ መምህራችን አዘጋጁ ብሎናል
እሺ ለመቼ ነው?
ለነገ
እሺ ችግር የለውም ግን ክፍሌን እንዴት አወቅሽው?
አፋልጉኝ አውጥቼ ነዋ
እኔ ምልሽ ስንተኛ ክፍል ነሽ?
ስድስተኛ አሁን እስከ ክፍላችን ትሸኘኛለህ?
በደስታ ነዋ
በቃ ምን ልበላቹ በጣም ደስ ትላለች በዛ ለይ ጫወታ አዋቂ ፈግግታዋ ገዳይ ቃላት የማይቀልፃት የውቦች ውብ እብደቷ ደግሞ ከሁሉም በላይ ይስባል አሁን በየትኛው መንገድ ይሆን በእጄ የማስገባት?ዋናው መቀራረባችን ነው ደስ የሚለው ነገር የግጥም አፍቃሪ መሆኗ ስራዬን ያቀልልኛል ያለችኝን ግጥም ሰጠዋት ስለ ትራፊክ አደጋ አሳጥሬ ነበር የፃፍኩት
የተናቀው ገዳይ
በምን ላስረዳ የለኝም ቃላት
አልሰበሰብ አሉኝ ፊደላት
በደም ተነክሮ በዋናው ጠላት
ረገፉ ነፍሳት ልክ እንደ ቅጠላት
ሰዎነታቸው ደቀቀ አፈር ድሜ በሉ
የተረፈውም ቢሆን ሲጎል አካሉ
የሰው ልጅ ደም ረከሰ
ስጋና አጥንቱ የተከሰከሰ
ያገባኛል በሚል ስሜት መንፈስ
አደጋውን እንቀንስ
ይሄ ግጥም ነበር የሰጠዋት ተደመመችብኝ
ከሷ እንደተለያየው ሀሰን የሚባል ጓደኛዬ ሊያናግረኝ መጣ ስለ ራህመቴ ምን ሊለኝ ይሆን?
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@Halal_Fonqaa
┗━ ━━━━ ━┛
1.3K views Cʀᴀᴢʏ ʟᴏᴠᴇ , 07:58