Get Mystery Box with random crypto!

የቅድመ-ወር አበባ ቅምረ ህመም - Premenstrual syndrome (PMS) ከወር አበባ በፊ | Hakim @ሐኪም

የቅድመ-ወር አበባ ቅምረ ህመም - Premenstrual syndrome (PMS)

ከወር አበባ በፊት እና ከኦቭሌሽን በኋላ (ከ5-7 ቀን) የሚከሰቱ ምልክቶች ሲሆኑ አብዛኛውን ጊዜ የግለሰባዊ ግንኙነቶች እና መደበኛ እንቅስቃሴን ሲያስተጓጉል ይስተዋላል። የቅድመ-ወር አበባ (Premenstrual syndrome) ዓለም አቀፍ ስርጭት 47.8% ሲሆን 90% የሚሆኑት የመራቢያ ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች በሕይወታቸው ውስጥ በሆነ ጊዜ ይጠቃሉ።

ይህ ሲንድሮም ትክክለኛ መንስኤ በትክክል ባይታወቅም እንቁላል ከወጣ በኋላ በሆርሞን ለውጦች ምክንያት እንደሚነሳሳ ይታመናል። ፕሮጄስትሮን ከ PMS ምልክቶች በስተጀርባ ያለው ዋና ምክንያት ነው።

ምልክቶቹ
• ውጥረት ወይም ጭንቀት
• ድብርት
• ማልቀስ
• የስሜት መለዋወጥ እና ንዴት ወይም ቁጣ
• የምግብ ፍላጎት ለውጦች
• እንቅልፍ የመተኛት ችግር (እንቅልፍ ማጣት)
• ማህበራዊ ግንኙነትን ማቋረጥ
• ደካማ ትኩረት
• አጠቃላይ ህመም
• ማቅለሽለሽ
• ብጉር እና የአለርጂ ምላሾች

መፍትሄ

• በቫይታሚን B6 ፣ ካልሲየም እና ማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች ሊመከሩ ይችላሉ።
• ትራይፕቶፋን የያዙ ምግቦችን መመገብም ሊረዳ ይችላል። ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ የወተት ተዋጽኦዎች፣ አኩሪ አተር፣ ቱና እና ሼልፊሽ ናቸው።

• በወሩ ውስጥ ብዙ እንቅልፍ ለመተኛት ይሞክሩ።
• እንደ ውሃ ወይም ጭማቂ ያሉ ብዙ ፈሳሽ ይጠጡ። ለስላሳ መጠጦችን፣ አልኮልን ወይም በውስጡ ካፌይን ያለበትን (ቡና፣ ኮካ) ያስወግዱ።

• ቢያንስ በየ 3 ሰዓቱ የሚበላ ነገር ይኑርዎት። ነገር ግን ከመጠን በላይ አይብሉ።
• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ጡንቻን ማዝናናት እና የማያቋርጥ ማነቃቂያ መደጋገም ፣ ለምሳሌ በእያንዳንዱ እስትንፋስ ጊዜ “አንድ” የሚለው ቃል እየደጋገምን; ለ 10-20 ደቂቃዎች ልምምድ ማድረግ

• የግንዛቤ ባህሪ ሕክምና (Cognitive behavioral therapy) እና በሀኪም የሚታዘዙ መድሀኒቶችም ስለሚኖሩ አስጊ ደረጃ የሚደርስ (PMDD) ከሆነ ሀኪም ያማክሩ።

Dr. Beimnet Ayenew

@Hakim_Doctors_Ethio_health_tena