Get Mystery Box with random crypto!

የተከፈተ በር (በውቀቱ ስዩም) የቤታችን በሩ ፤ ከፍተሽው እንደሄድሽ ፤ዛሬም አልተዘጋም የነበረኝ | Haile Bee ᥫ᭡

የተከፈተ በር
(በውቀቱ ስዩም)
የቤታችን በሩ ፤
ከፍተሽው እንደሄድሽ ፤ዛሬም አልተዘጋም
የነበረኝ የለም፤ ለቀማኛ አልሰጋም
እምቢ ካልሽ እምቢ ነው ፤ፅኑ ነው ያንች ቃል
እንደማትመለሽ ፤አእምሮየ ያውቃል
ግን አልፈርድበትም፤ልቤ ቢያመነታ
ምኞት በሞላው ቤት ፤እውቀት የለው ቦታ
ተስፋ አይቆርጥም ደሞ፤
ልቤ ህልሙን ያምናል
ይለኛል ደጋግሞ፤
“ትመለስ ይሆናል
ትመለስ ይሆናል
ትመለስ ይሆናል፤”
እኔም በምላሹ ፤ ልቤን ፊት ሳልሰጠው
እንዲህ እለዋለሁ፤ ተስፋ ላስቆርጠው
“ጠጠር ላይቀቀል፤ አልማዝ ላይከለስ
በደመና ራስጌ፤ ጎጆ ላይቀለስ
እኔም አልሻሻል፤ እሱዋም አትመለስ፤
ሰማይ ሰም ይመስል፤ ቢንጠባጠብ ቀልጦ
የረር ፈልሶ ቢሸሽ፤ ቢከተል እንጦጦ
ባህሮች ቢከስሙ፤ ምድር ብትናወጥ
እሱዋም አትመለስ ፤እኔም አልለወጥ”
በዙርያየ ያለው ፀጋ ብዙ ነበር፤
ግና ክንፍ አብቅሎ
ፍቅርሽ ጥሎኝ ሲበር
ከኔ ጋር የቀረው
የተቆለፈ ልብ፤ የተከፈተ በር፡፡