Get Mystery Box with random crypto!

ባለፉት ዓመታት ሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳሰ ክለብ በዓመት ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ውጪ አውቷል። 'ስ | ሀዲያ ሆሳዕና

ባለፉት ዓመታት ሃዲያ ሆሳዕና እግር ኳሰ ክለብ በዓመት ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ውጪ አውቷል። "ስንት ሚሊዮን ብር ገቢ አስገብቷል?" ካላቹኝ ከአስር ሚሊዮን ብር በታች የሚል ነው መልሴ። ምክንያቱም በይፋ የሚታወቀው ገቢው ከ DSTV የሚያገኘው ብቻ ነው። ከእስቴዲየም አልያም ከደጋፊው የሚሰበስበው ገንዘብ የለውም። "ለምን?" ካላቹኝ እንደሚታወቀው ከእስቴዲየም ገቢ እንዳያገኘ ውድድሩ የሚካሄደው በተመረጡ ሜዳዎች ብቻ ነው። ደጋፊን የገቢ ምንጩ እንዳያደረግ ደግሞ በመጀመሪያ የተዘረጋ አንዳችም ሲስተም አልነበረም።

በቅርቡ የተቋቋመው የደጋፊ ማህበር የክለቡን ደጋፊዎች የእረጅም ጊዜ ጥያቄን የመለሰ ስራ ሰርቷል። ሃዲያ ሆሳዕና በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ ከጀመረበት 2008 ዓ/ም ጀምሮ እኔ በግሌ እስከማውቀው ደጋፊውን የሚመጥን፣ ጥራቱን የጠበቀና ክለቡንም የሚገልፅ መልያ ለደጋፊ ቀርቦ አያውቅም። አዲስ የተቋቋመው ማህበር ከሃገር በቀሉ የትጥቅ አማራች ከሆነው "ጎፈሬ" ጋር የአንድ ዓመት ውል በተፈራረመበት በአጭር ጊዜ ውስጥ መልያዎችን በማሳተም ለገቢያ አቅርቧል።

ይህ ጅማሮ የሚበረታታ ነው። ይበል የሚያሰኝም ጭምር። ምከንያቱም በቀጣይ ሌሎች ስራዎችን እየሰራቹ ደጋፊዎችን ወደ ገንዘብ በመቀየር ከመንግስት ካዝና የሚወጣውን በጀት በመቀነስ ለልማት እንዲውል የእናተ እግዛ ያስፈልጋልና በርቱልን ለማልት እውደሃለሁ!

ደጋፊዎችም የምትወዱትን ክለብ መልያ በመግዛት ከሞራል በለፈ በገንዘባችሁ ደግፉ!
@tariku_abera