Get Mystery Box with random crypto!

ጠይቅ፣ እመን፣ ተቀበል! ፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨፨ ከአምላክህ ጋር ያለህን ግነኙነት አጠንክር | መድብለ ጥበብ

ጠይቅ፣ እመን፣ ተቀበል!
፨፨፨፨፨////////፨፨፨፨፨፨
ከአምላክህ ጋር ያለህን ግነኙነት አጠንክር። ጠይቅ፤ እመን፤ ተቀበል። ጠይቀህ የሚነፍግህ አምላክ የለህም፤ እያመንከው የሚክድህ አባት የለህም፤ ለመቀበል እየጠበከው በእምቢታ የሚጎዳህ ፈጣሪ የለህም። ዝምታው በእራሱ አንደኛው ምላሹ ነው። የሚጠበቅብህን አድርግ እርሱም በጊዜው ነገሮችን ውብ አድርጎ ይሰራቸው ዘንድ ፍቀድ።
ፍላጎትህ ምንድነው?
ማሳካት የምትሻው፣ እንዲኖርህ የምትመኘው ምንድነው? ከአምላክህ ውጪ የሚሰጥህ እንደሌለ እወቅ። ያለማቋረጥ ጠይቅ፣ ያለመሰልቸት ለምን፣ ያለመታከት ተማፀን። የጥያቄህ ዘላቂነት፣ የማይቋረጠው ልመናህ እውነተኛው ፍላጎትህን /Desire/ የሚያሳይ ነው። ከልብህ የምትፈልገውን ለመጠየቅ ሊደክምህ አይችልም፤ በፍፁም አትሰለችለም። ቢርብህ፣ ቢጠማህ ልመናህ አይቆምም። መሰረታዊና እጅግ አስፈላጊ ለምትለውም ፍላጎትህ ልመናና ተማፅኖህ አይቋረጥም።

አዎ! ጀግናዬ..! ጠይቅ፣ እመን፣ ተቀበል! እስከዛሬ ከልብህ በፅናት እስከጥግ የጠየከው፣ ለማግኘት የታገስከው፣ በትጋት የሰራህበት ነገር ምንድነው?
ባለመጠየቅህ፣ ቃል ባለማውጣትህ፣ ፍላጎትህን ባለመለየትህ በሃሳብ የቀረው ነገርስ ምን ይሆን?
አዎ! "ጠይቁ የሰጣቹሃል፤ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል" መባሉ ያለምክንያት አይደለም። አምላክ የልብ መሻታችንን ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፣ ምንያክል እንደምንፈልገውም ጠፍቶት አይደለም፤ የጥያቄያችን ምላሽ ማስተማሪያ እንዲሆን ይፈልጋል፤ የተሰጠንን መብት መጠቀሙ ሃይል እንዲሆነን፣ እምነታችንን እንዲያጠነክር ነው። መጠየቅ ውስጥ እምነት አለ፤ የማግኘት ተስፋ፣ ጥበቃ አለ። የፈለጋቹትን ጠይቁ የሚል አባት እያለ ለጥያቄ መስነፍ ተገቢ አይደለምና የምትሻውን ወሳኝ ነገር ጠይቅ፤ እንደሚሰጥህ እመን፤ ለመቀበል ተዘጋጅ፤ ሳትጠይቅና ጠይቀህ በተሰጠህም እያንዳንዱ ነገር አመስግን።
"የመጠየቅ ነፃነት ስለሰጠሀኝ አመሰግናለሁ፤
እንዳምንብህ ስላደረከኝ አመሰግናለሁ፤
ለምላሽህ ጥበቃ ተስፋን ስለሰጠሀኝ አመሰግናለሁ።"
@habtewman