Get Mystery Box with random crypto!

ኤክቶሞርፍ(ectomorph) ኤክቶሞርፎኦች በተፈጥሯቸው ቀጭን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።እነዚህ ሰዎ | Gym Motivation ethio 🇪🇹

ኤክቶሞርፍ(ectomorph)

ኤክቶሞርፎኦች በተፈጥሯቸው ቀጭን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።እነዚህ ሰዎች በሌላ ሰም አጠራራቸው Hard gainers ይባላሉ።እንደዚህ የተባሉበት ምክንያት በቀላሉ ለውጥ ማምጣት ስለማይችሉ ነው።እንደውም አይታቹሀቸው ከሆነ ይህኛው የሰውነት አይነት ያላቸው ስዎች ምንም እንኳን አብዝተው ቢበሉ ክብደት ለመጨመር ሲቸገሩ ይታያሉ።ይህን ስል ግን ለውጥ ማምጣት አይችሉም እያልኩ እንዳልሆነ ይሰመርልኝ።

ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምን ቢበሉና ምን ቢሰሩ ለውጥ ማምታት ይጀምራሉ?

ከምግብ ስንጀምር

የሰውነት አይነታቸው ኤክቶሞርፍ የሆኑ ሰዎች በአብዛኛው መመገብ ያለባቸው Carbohydrate የሆኑ ምግቦችን ነው።
በፐርሰንት ስናስቀምጠው
55%Carbohydrate,25%protein,20%fat.
ሌላው ደሞ Calorie surplus ላይ መሆን አለባቸው።ስለዚህ ነገር ባለፎው ስለተናገርን አሁን ላይ ብዙም አላብራራውም ግን ለማስታወስ ያህል calorie surplus ማለት በፊት ሰውነታችን የተለያዩ ነገሮችን ለመከወን ከሚያስፈልገው የካሎሪ መጠን ጨምረን መስጠት(መመገብ) ማለት ነው።በፊት ሰውነታችን የሚፈልገው 2000ካሎሪ ከነበረ አሁን ደሞ ከ2000 በላይ ካሎሪ ስንመገብ ያ calorie surplus ይባላል።
ከቻላችሁ በቀን ውስጥ ከ4-6 ጊዜ ብትበሉ ይመረጣል።ይህም ማድረግ ጥቅሙ፦
በቀን ውስጥ የምትመገብትን የካሎሪ መጠን እንዲጨምርላችሁ ስለሚያግዝ
እንዳትራብ ስለሚያግዛችሁ ነው።ምክንያቱም መራባችሁ በውስጣችሁ ሀህል በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ለሀይል የሚሆነውን ፋት ይቀንሰውና ወደ ጡንቻዎቻችሁ ሀይልን ለመግኘት ይመጣል በዛን ጊዜ የጡንቻን መጠን ይቀንሰዋል።ስለዚህ መራብ አይመከርም ።
ስለዚህ ectomorph የሆኑ ሰዎች ይህን የአመጋገብ ስርዐት ቢከተሉ የተሻለ ነው።

ወደ ስፖርቱ ስንመጣ

Ectomorph የሰውነት አይነት ያላቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ከካርዲዮ ይልቅ ኮምፖውንድ ኤክሰርሳይሶች ላይ ማተኮር አለባቸው።ለዚህም እንደ ምክንያት የምናስቀምጠው ከሌሎቹ የሰውነት አይነቶች ውስጥ ኤክቶሞርፎች የፋት መጠናቸው አነስተኛ ስለሆነ ነው።ስለዚህ ኮምፖውንድ ኤክሰርሳይሶች ማዘወተር አለባቸው ማሽኖች ላይም ጊዜያቸውን ማጥፋት የለባቸውም።
በተለይ ዋና ዋናዎቹ የሚባሉትን የኮምባውንድ አይነቶች ስሩ።ለምሳሎ bench press,militarily press or shoulder press,squat,deadlift እነዚህ ላይ በደንብ ስሩ።በቀለላችሁ ቁጥር ኪሎ መጨመር እንዳትረሱ።

ሌላው ዕረፍት ነው።እረፍት በጣም ወሳኙ ነገር ነው።ዕረፍት ስል እንቅልፍ ብቻ ሳይሆን ሰፖርት ከሰራችሁ በኋላ muscle Recover እንዲያደርግ የምትሰጡትን ጊዜ ጨምሮ ነው።

ስለ Ectomorph body type በአጭሩ ይህን ይመስላል።በቀጣይ ሌላ BODY TYPE የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

@gymworkoutethio
Join for more