Get Mystery Box with random crypto!

ከመፃህፍት ገፆች

የቴሌግራም ቻናል አርማ gudukasabookcenter — ከመፃህፍት ገፆች
የቴሌግራም ቻናል አርማ gudukasabookcenter — ከመፃህፍት ገፆች
የሰርጥ አድራሻ: @gudukasabookcenter
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 150
የሰርጥ መግለጫ

ኑ ማንበብን ባህል እናድርገዉ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-27 22:52:33
267 views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 13:00:59
289 views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 21:31:14
ኑ ጭቃ እናቡካ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ በቅርብ ቀን

የ ቻናላችን ቤተሠብ በመሆን አዳዲስ እና አስተማሪ ነገሮችን ይከታተሉ



https://t.me/joinchat/eD8ZZ2SLi5cwZjU0
267 viewsedited  18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 21:30:47
ኑ ጭቃ እናቡካ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ በቅርብ ቀን



https://t.me/joinchat/eD8ZZ2SLi5cwZjU0
264 viewsedited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 21:29:57
ኑ ጭቃ እናቡካ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ በቅርብ ቀን



https://t.me/joinchat/eD8ZZ2SLi5cwZjU0
254 viewsedited  18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 21:28:36
ኑ ጭቃ እናቡካ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ በቅርብ ቀን
244 viewsedited  18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 21:21:34
ኒኮላ ቴስላ

ኒኮላ ቴስላ፣ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9/10፣ 1856 የተወለደው በክሮኤሺያ ውስጥ ሲሆን የተለያዩ የፊዚክስ ግኝቶችን ያገኘ ሰው ነው። አባቱ የኦርቶዶክስ ቄስ ነበር; እናቱ ያልተማረች ነበረች ግን በጣም አስተዋይ ነበረች። በጉልምስና ወቅት፣ አስደናቂ ምናብ እና ፈጠራ እንዲሁም የግጥም ችሎታ አሳይቷል።

ስለ ኒኮላ ቴስላ 5 አስገራሚ እውነታዎች

1. ቴስላ የተወለደው በመብረቅ ማዕበል ወቅት ነው።

2. ቴስላ እ.ኤ.አ. በ1901 የሞባይል ስልክ ቴክኖሎጂን እና ሽቦ አልባ ኢንተርኔትን ከመፈጠራቸው ከብዙ አመታት በፊት ቀድሞ አስቦ ዲዛይኑንን ስሎታል።

3. ኒኮላ ቴስላ በጊዜው ሌላ ታዋቂ ፈጣሪ እና የወደፊት ተቀናቃኙ ለሆነው ለቶማስ ኤዲሰን ለመስራት ወደ አሜሪካ ተዛወረ።

4. ኒኮላ ቴስላ በ1891 የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ሆነ።

5. ኒኮላ ቴስላ ኤሌክትሪክን በአየር ማስተላለፍ እንደሚቻል ለሰዎች ሲነግራቸው እብድ ብለው ይጠሩታል፡ ቴስላ በአመለካከቱ እና በማሰብ ችሎታው "እብድ ሳይንቲስት" በመባልም ይታወቅ ነበር. በተጨማሪም የ ቅንጣት ሽጉጥ( atomic gun ) ወይም የሞት ጨረሮችን ሰርቷል።



https://t.me/joinchat/eD8ZZ2SLi5cwZjU0
278 viewsedited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 15:41:31 እንኳን አደረሳችሁ
282 views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 07:59:03 አሜሪካዊው ቢሊዬነር ስቲቭ ጆብስ በህይወቱ መጨረሻ ሰዓት ላይ ያስተላለፈው
አስደናቂ መልዕክት፦ ስቲቭ ጆብስ በ56 አመቱ ያረፈ አሜሪካዊ ቢሊዬነር ሲሆን
ህይወቱ ያለፈው በካንሰር በሽታ ነው፡ በንግዱ አለም ውስጥ የመጨረሻ ከፍታ
ጫፍ የሚባለው ቦታ ደርሻለሁ፣ ይሁን እንጂ ከዚህ ሁሉ ሀብት ደስታን ማግኘት
አልቻልኩም። በልፋቴ ካከማቸሁት ሃብት ያገኘሁት ደስታ እዚህ ግባ የማይባል
ነው። አሁን በህይወቴ የመጨረሻው ሰዓት አካባቢ አልጋ ላይ ሆኜ ያሳለፍኩትን
ነገር ሁሉ ወደሗላ ሳስበው፤ እኮራበት የነበረው ሀብቴና ዝናዬ ከንቱ እና ትርጉም
አልባ እንደሆነ ተረድቻለሁ።
~አንድን ሰው መኪና እንዲነዳልህ ወይም ሰርቶ ገንዘብ እንዲያስገባልህ
ልትቀጥረው ትችላለህ፤ እየተሰቃየህበት ያለውን ህመም እንዲሸከምልህ ግን
ልትቀጥረው አትችልም፡፡ -ምድራዊ የሆኑ ቁሳቁሶች ሁሉ ሊጠፉ፣ ዳግም
ሊገኙም ይችላሉ፤ አንድ ጊዜ ካመለጠ ደግመህ ልታገኘው የማትችለው አንድ
ነገር ግን አለ. እርሱም # ህይወትህ ነው!! ~አንድ ሰው የቀዶ ጥገና
ወደሚደረግለት ክፍል ሲገባ አንብቦ ያልጨረሰው አንድ መጽሃፍ ትዝ ቢለው
የመጽሐፉ ርዕስ "ጤናማ ህይወት የመኖር ሚስጥር" የሚል ሊሆን እንደሚችል
ጥርጥር የለውም። -በየትኛውም የህይወት ከፍታ ላይ ብንሆን የህይወታችን
መጋረጃ የሚዘጋበትን ቅጽበት ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት አንድ ቀን መምጣቱ
አይቀርም። -ለቤተሰብህ፣ ለትዳር አጋርህ እና ለጏደኞችህ የፍቅርን ውርስ
አስቀምጥላቸው። -ራስህን ተንከባከብ ፣ ከሌሎች ጋር መልካም ግንኙነት
ይኑርህ።
-እያደግን ስንሄድና የህይወት ትርጉሙ ሲገባን ውድ ሰዓትም አሰርን ርካሽ ሰዓት
፣ ሁለቱም የሚነግሩን ጊዜ እኩል መሆኑ ይገባናል፡ -በኪሳችን ውድ ቦርሳም
ያዝን ርካሽ ቦርሳ፣ በውስጡ የሚኖረውን የገንዘብ መጠን አይቀይረውም። -
የአንድ ሚሊዮን ብር መኪናም ነዳን የሶስት መቶ ሺህ ብር መኪና ፣የመንገዱ
ርዝመት አይቀየርም፤ አቅጣጫውም ያው አንድ ነው፥ የምንደርሰውም ያው
እዚያው ቦታ ነው። -ውድ መጠጥም ጠጣን ርካሽ መጠጥ፣ ስካሩና አድሮ
የሚያመጣው ራስ ምታት ለውጥ የለውም። -ሰፊ ግቢ ውስጥ ኖርንም ጠባብ
ቤት፣ ብቸኝነቱ ያው እኩል ነው፡፡ የውስጥ ደስታ በቁሳቁስ እንደማይገኝ ያን ጊዜ
ይገባሃል። ~አውሮፕላን ላይ የክብር ቦታም ተቀመጥክ ወይም ተራ ቦታ
አውሮፕላኑ ከተከሰከሰ እኩል ቁልቁል ትወርዳለህ። | እውነተኛው ደስታ
የሚገኘው ከቤተሰብህ፣ ከጓደኞችህ፣ ከዘመዶችህ ጋር በሚኖርህ ውብ ጊዜኣት
ብቻ ነው፡፡ ከእነርሱ ጋር በምታሳልፈው ጊዜ፣ በምትጫወተው ጨዋታ፣
በምትዘምረው መዝሙር፣ በምትስቀው ሳቅ እውነተኛ ደስታን ታገኛለህ።
5 ሊካዱ የማይችሉ የህይወት እውነታዎች አሉ ~ልጆችህ ሀብታም እንዲሆኑ
አታስተምራቸው፥ ይልቅ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ አስተምራቸው።
ሲያድጉ የነገሮች ዋጋ ሳይሆን ጥቅማቸው ይገባቸዋል። ~ምግብህን እንደ
መድሃኒት ውሰድ ካልሆነ መድሃኒት እንደምግብ ትወስዳልህ፡፡ -የሚወድህ ሰው
በቀላሉ አይለይህም፣ ከኣንተ ለመለየት 99 ምክንያት ቢኖረው እንኳ መለየት
በማይችልባት አንዲት ነገር ላይ ፀንቶ ይቆማል። - ሰው ሆኖ በመፈጠርና "ሰው
በመሆን" መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፥ ይህ የሚገባቸው ጥቂት ሰዎች ናቸው። -
ስትወለድ ውድ ነበርክ፣ ስትሞትም ውድ ትሆናለህ፣ በመካከል ያለውን
ማስተካከል ያንተ ፋንታ ነው። -በፍጥነት ለመሄድ ከፈለክ ብቻህን ሂድ፣ ሩቅ
ለመድረስ ከፈለግህ ግን ከሌሎች ጋር አብረህ ተጓዝ
309 views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-14 16:33:01 ከማዛሮት መጽሐፌ የተወሰደ
ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ እንደገለጸው ውሃን የመሳብ ከፍተኛ ዐቅም ያላት ጨረቃ በእኛ ውስጥ ያለውንም ከፍተኛ የውሃ መጠን በመሳብ የውስጣችን ውሃ ማዕበልነት ታስነሣለች፡፡
በተለይ በጠፍ ጨረቃ (new moon) እና ሙሉ ጨረቃ (full moon) በምትሆንበት ጊዜ አእምሯቸው የታወከ ሰዎች በሚታከሙበት ሆስፒታል የሚሠሩ ሐኪሞች ሕመምተኞቹ እንደሚረበሹ፣ እንደሚቅበጠበጡ በስፋት ይገልጣሉ፡፡
በዚህ ምክንያት የአእምሮ ሕመምተኛ “ሉናቲክ” ይባላል፡፡ “ሉና” ማለት በላቲን ጨረቃ ማለት ሲሆን ሕመማቸው የበለጠ በሙሉ ጨረቃ ጊዜ የሚጐላ መሆኑን ለማሳየት ከጥንት ጀምሮ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡
ለዚህ ነው የኢትዮጵያ መተርጒማን ሊቃውንት ምልአተ ወርኅ (ጨረቃ ሙሉ) ስትሆን ደም ይመላል፣ ብርድ ብርድ ይላል፣ ደዌ ይቀሰቀሳል በማለት የጻፉት፡፡
በ2011 “ዎርልድ ጆርናል ኦፍ ሰርጀሪ” ላይ የቀረበ ጥናት 40 ፐርሰንት የሕክምና ኀላፊዎች “የሙሉ ጨረቃ ዕብደት” (ፉል ሙን ማድነስ) በሕመምተኞች ላይ እንደሚከሰት እንደሚያምኑ ሲገልጽ የአደጋ ጊዜ ስልክ ጥሪዎችም በሙሉ ጨረቃ ጊዜ 3 ፐርሰንት ሲጨምሩ በጠፍ ጨረቃ ጊዜ ደግሞ 6 ፐርሰንት ይቀንሳል ይላል፡፡
በ2008 ላይ የብሪቲሽ አጥኚዎች የጨረቃ ዑደትና ዶክተሮች እንዴት ሕመምተኞችን እንደሚያዩ በዘረዘሩበት ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ “ሜዲካሊ አንኤክስፕሌንድ ስትሮክ ሲምተምስ” በማለት በህክምና ሊገለጽ የማይችል ሕመምተኞች በሙሉ ጨረቃ ጊዜ የራስ ሕመም፣ የድንዛዜ ስሜት፣ ያመናል ይላሉ፤ ሲመረመሩ ግን በነርሱ ሰውነት ላይ ግን ምንም ችግር የለም፡፡ ይህ በሕክምናው ይህ ነው ተብሎ የማይገለጥ መልስ የለሽ ነው የሚል አስተያየት ተገልጧል፡፡
ከልብ ጋር በተያያዘ ከላይ እንደተገለጸው በአንጎላችንና ልባችን የያዘው ውሃ መጠን → 73% ነውና “Indian Journal of basic and applied research” ላይ የወጣው ጽሑፍ በጠፍ ጨረቃና በሙሉ ጨረቃ ጊዜ ልብህ የመጨረሻ የአፈጻጸም ብቃት ላይ ስለሚሆን ስለዚህ ወደ ስፓርት መሥሪያ (ወደ ጂም) ከመሄድህ በፊት ጨረቃ ያለችበትን ሰሌዳ አረጋግጥ ይላል፡፡ ምክንያቱም ሰውነታችን ውስጥ ያለውን ውሃ በመሳብ የውስጣችንን ማዕበል የምታስነሣ በመሆኗ፡፡

[የድንዛዜ ዘመን እያበቃ ነውና ለራሶ ሲሉ ማዛሮትን ያንብቡ።]
154 views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ