Get Mystery Box with random crypto!

ለማን አቤት ይባል ጎንደር ሽምጥ እየጋለበች በፍጥነት ወደኋላ እየተጓዘች ነዉ !! ይህ ከ | Amhara today

ለማን አቤት ይባል

ጎንደር ሽምጥ እየጋለበች በፍጥነት ወደኋላ እየተጓዘች ነዉ !!

ይህ ከምስሉ የምትመለከቱት በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ ወደ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ዲፖ አካባቢ (የቆፈሩት ) ገደል ጭቃ ዉስጥ የገባ መኪና ነዉ ።

ይህ መንገድ ከተጀመረ ግማሽ ደረዘን አመታት ያስቆጠረ ሲሆን ባለፈዉ ካድሬዎችና ሹመኞች በቴሌቪዥን ቀርበዉ ሰኔ ላይ እናጠናቅቃለን ብለዉ ነበር ነበር ሁኖ የዜና ማዴመቂያ ሁኖ ቀረ እንጂ
ይህ አስፖልት ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ቢያንስ ድልድዮችን ስሩ ብለን ጩኋን ሰሚ አላገኘንም
ይሄዉ ዛሬ ገና በቅጡ ሳይዘንብ አደጋ ማድረስ ጀምራል ።
ነገ ዝናቡ ሲዘንብ ደግሞ
ከልደታ እስከ ፋና ያፈረሷቸዉ ድልድዮች በመኖራቸውና በአፈር በመሞላታቸዉ ከተራራዎች የሚመጣ ጎርፍ ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ላይ አደጋ እንደሚያደርስ ምንም ጥርጥር የለዉም ።

እና ምን ተሻለን ታላቅ ከተማ ላይ ተቀምጠን የመናገሻ ከተማ ነዋሪዎች ተብለን ሌላው መሰረተ ልማት ቢቀር እንኳን እንዴት በወራት የሚያልቅ 12 ኪሎሜትር መንገድ ከአምስት አመት በላይ ይፈጃል ።

ለነገሩ ስንጠቋቆምና ስንገፋፋ ገና ከዚህም በላይ ችግር ዉስጥ መገባቱ አይቀርም

ትመጣለህ ብየ ዙሬ ዙሬ ባይ
ጎንደር ወደኋላ መቅረትህ ነዉ ወይ

ታዴ የማመይ ልጅ