Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል አስራ ሦስት #ኢየሱስ_አማላጅ_ከሆነ_እንደት_ፈራ_ሆነ ይህ ጥያቄ የሚነሣ ስለኢየሱ | Christlikeness

ክፍል አስራ ሦስት


#ኢየሱስ_አማላጅ_ከሆነ_እንደት_ፈራ_ሆነ
ይህ ጥያቄ የሚነሣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት ካልተገነዘበ ኅልና የተነሳ
ይመስላል፡፡በመጀመርያ መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ(አምላከ-ሰው) መሆኑን መረዳት ይጠበቅብናል፡፡ኢየሱስ የሰው ልጅ በመሆኑ እግዚአብሔር በሰዎች ላይ እንድፈርድ ሥልጣንን ሰጥቷል፡፡
‹‹ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድም
ሰው ስንኳ አይፈርድም፡፡››ዮሐ5፡22-23
እንድፈርድ ሥልጣንን እግዚአብሔር አብ ለእግዚአብሔር ወልድ የሰጠበት ምክንያት የሰው ልጅ በመሆኑ የሰውን ልብያውቃል፤እርሱም ምሉዕ ሰው ስለሆነ የሰዎችን ድካም ሆነ ስሜታቸውን ስለምረዳ ነው፡፡
ስለ ፍርድ ስናነሳ #ፍርድ ወይም #መፍረድ የሚለውን የቃሉን ትርጉምና ስለ ፍርድ ዓይነቶች ማወቅ ይጠበቅብናል ፡፡እስክ ወደ ቃሉ ትርጉም እንሂድ፡-
መፍረድ/condemnára የሚል ቃል ከላትን com/ኮምና damnár/ዳምናር ከሚለው
ሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን በግሪክ katakrino/ካቲአክርኖ የሚለው ደግሞ ካታ(kata)ና ክርኖ(kpivw) ከሚለው ሁለት ቃላት የተገኘ ነው ትርጉሙ ፈረደ፡የሚፈርድና ፈራጅ የሚል ነው፡፡ በዕብራይስጥ #ሻውፋት ወይም #ምሽፓውት የሚለው ከግሪኩ ጋር ተመሳሳ ትርጉም አለው፡፡ የቃሉን ትርጉም በዚህ መልኩ ካየን የፍርድ ዋና ሀሳብ እውነትን ከእውሸት ለመለየትና ለሰሩት ስራ ለድካማቸው መሸለም ወይም መክፈል የሚል እድምቷ አለው። በእኔ አመለካከት ፍርድ ከዓይነቱ አንጻር በዋናነት በሦስት ይከፈላል፡፡
1.የፍትህ ፍርድ
2.የተግሣጽ ፍርድ
3.የሕይወት ትንሣኤና የሞት ትንሣኤ ፍርድ

የመጀመርያ የፍትህ ፍርድ የምንለው በበዳዩና በተበዳዩ መካከል እግዚአብሔር በመዳኘት በዳዩን በቅጣት ተበዳዩን በማጽናናትና በመካስ የሚፈርድ ሲሆን ይህም የፍትህ ፍርድ ይባላል፡፡ዮሐ 8፡1-11፤አሞጽ 6፡12-14፤ኤርም 25፡29፤1ቆሮ 5፡4-5
የተግሣጽ ደግሞ ከአለም ጋር እንዳይፈረድብን እግዚአብሔር #በምድር ላይ የሚገስጸን ነው፡፡ 1ጴጥ 4፡14፤ዕብ12፡5፤2ቆሮ7፡9
ሦስተኛው የዘላለም ሕይወትና የዘላለም ሞት ፍርድ የሚንለው #የመጨረሻ ፍርድ በመባል ይታወቃል። ከፍትህና ከተግሣጽ ፍርድ የሚለየው ሁለቱ ከትንሣኤ በፊት የሚፈጸሙ ሲሆኑ ይህ የመጨረሻ ፍርድ ግን አንዳንዶች ለዘላለም ሕይወት ሌሎቹ ደግሞ ለዘላለም ሞት ከትንሣኤ በኃላ የሚፈጸም ነው፡፡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን እየፈረደ ያለው የመጨረሻ ፍርድ ሳይሆን #የፍትህና_የተግሣጽ ፍርድ ነው፡፡ማወቅ የሚገባን ነገር ኢየሱስ የሚማልደው ለፍትህ ወይም ለተግሣጽ ፍርድ ሳይሆን ከደረስንበት ጽድቅ እንዳንወድቅ ሞት እንዳይፈረድብን እስከ መጨረሻ መጽናት እንድንችል ነው፡፡ ምልጃው ከኃጢአት አንጻር ነው እንጂ ከፍትህ ወይም ከተግሣጽ አንጻር አይደለም፡፡በአሁን ጊዜ በማንም ላይ የመጨረሻ ፍርድ አልተሰጠም፤ይልቁንም አሁን
ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት እንድያገኙና ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንድቀላቀሉ የምስራቹ እየተሰበከ ያለወቅት ነው፡፡
ለአንዳንዶችየሚዘገይእንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም ነገር ግን ሁሉ ወደ ንሰሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል፡፡1ጴጥ 3:9
እንዲሁም
እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንሰሐ
ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤ቀን ቀጥሮአልን በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው
እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው ፤ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል፡፡ሐዋ17፥30-31
የመጨረሻ ፍርድ የሚከናወነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስመጣ ነው፡፡
ዮሐ5፡28-29፤ማቴ
12፡36-37፤1ጴጥ 1፡7፤ሮሜ 2፡16፤ኢሳ2፡12፤አሞጽ5፡18-20፤ሚል4፡1-5
ስናጠቃልል ኢየሱስ አሁን ደሙን ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ስለገባ በአብ ፊት እየታየና እየማለደ ይገኛል እንጂ የመጨረሻ ፍርድ እየፈረደ አይደለም፡፡ኢየሱስ አሁን እየፈረደ ሳይሆን እየማለደ ይገኛል ምልጃው እስከ ፍርድ ቀን ብቻ ነው፡፡በፍርድ ቀን ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም አሁን ግን አማላጅ ነው፡፡

#የኢየሱስ_አማላጅነቱ_እስከ_ፍርድ_ቀን_ድረስ_ፈራጅነቱ_ደግሞ_በፍርድ_ቀን_ነው፡፡


ይቀጥላል.......................................

መ/ር ኣያሌው ዋቀዮ
2014

ጥያቄ ካለዎት

@ayalewwakeyo
@ayalewwakeyo

Email:- ayalewwakeyo77@gmail.com


ሸር ያድርጉ


https://t.me/+MKJHZ8gH6iphMTdk


አስታየት ይስጡ