Get Mystery Box with random crypto!

ግሎባል መረጃ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ global_mereja — ግሎባል መረጃ®
የቴሌግራም ቻናል አርማ global_mereja — ግሎባል መረጃ®
የሰርጥ አድራሻ: @global_mereja
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 445
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ወደቻናላቺን በሰላም መጡ
ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ዜናዎችንና የተለያዩ መረጃዎችን እናቀርባለን። ምንጊዜም ከግሎባልመረጃ ከማንም ያልወገኑ፣ ሚዛናዊ፣ተዓማኒ፣ ግልጽና እውነተኛ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሎ
➡1.አዳዲስ ዜናዎች ና መረጃዎች
➡2.ድንቃድንቅ ወሬዎች
➡3.ስፖርታዊ ዘገባዎች
➡4.የመዝናኛ ዜናዎች
🅰👉 @global_mmerejabለ አስተያየ
🅰👉 @global_merejabot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-18 08:41:50
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት  የ500 ሜጋ ዋት ሁለት የፀሐይ ብርሃን ኃይል ጣቢያ  በጋራ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ 

የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ማስዳር ኩባንያ ጋር የ500 ሜጋ ዋት ሁለት የፀሐይ ብርሃን ኃይል  ማመንጫ ጣቢያ በጋራ ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር  ገፃቸው ኢትዮጵያ ሰፊ የታዳሽ ኃይል ሀብት ያላት  መሆኑን አስታውሰዋል።

የተፈረመው ስምምነት በአለም አቀፍ ደረጃ የካርቦን ልቀት ዜሮ የማድረግ ኢላማ ታዳሽ ሀብታችንን ለመጠቀም እና አስተማማኝ፣ ንፁህ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ሃይል ለኢትዮጵያ እና ለሌሎችም ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ዐቅም እና እድል የሚሰጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
20 viewsNEWS, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 21:01:24
በአዲስአበባ በነገዉ እለት ትምህርት አይኖርም ተባለ!

በነገው እለት የሚከበረውን የከተራ በዓል ምክንያት በማድረግ መንገዶች ስለሚዘጉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት የማይኖር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በተለምዶዉ በከተራ እለት ወይንም በጥምቀት በዓል ዋዜማ የግማሽ ቀን የትምህርት ግዜ የነበረ ቢሆንም በነገዉ እለት ግን ትምህርት አይኖርም ተብሏል።
              ┈••●◉◉●••┈
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU

join Us
https://www.facebook.com/Global-Feta-media-107879608174044/
  ለአሰተያየት
   @global_merejabot
57 viewsNEWS, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 20:57:58
በፖሊስ ተይዘዋል

ፖሊስ አግቢውን ፣ ልጅቷንና እናቷን ቁጥጥር ስር አውሏቸው ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

የ31 ዓመቱ ጎረምሳና የ12 ዓመቷ ህጻን ጋብቻ ትናንት ምሽት በዚህ ገጽ ከተለቀቀ በኋላ ሲነጋ ጉዳዩ የሕግ አካላትን አነጋግሮ ዛሬ ጠዋት የጉዳዩ ፈጻሚዎችና አስፈጻሚዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንደተጀመረ መረዳት ችያለሁ

የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አት ደስታነው አየነው ጋ ደውዬ ስለሁኔታው ጠይቄያቸዋለሁ ። አቶ ደስታነው መረጃው እውነት መሆኑንና ጉዳዩ ተጣርቶ እንዳለቀ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚላክ ነግረውኛል

አያይዘውም የተዳረችው ህጻን እድሜ ጉዳይ በወላጅ እናቷ 16 እንደሆነ የተገለጸ ሲህን የግንደወይን ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ እና ከከንቲባ ጽ/ቤቱ ጋር በመሆን ጤና ጣቢያ እንድትመረመር ተደርጎ እድሜዋ ከ12 እስከ 14 ዓመት እንደሚሆናት ተገምቷል

የከተማዋ ሴቶች ፣ ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አዳምነው የሻነው በስልክ እንደገለጹልኝ የልጅቷ ክብረንጽህና አለመገሰሱ በጤና ጣቢያ ደረጃ የተረጋገጠ ሲሆን ነገ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል እንደምትላክ አስታውቀዋል

መረጃው ትናንት ማታ በፌስቡክ ላይ እንደተገጸ ዛሬ ጠዋት ተጠርጣሪዎቹን ከፖሊስ ጋር በመተባበር ወደ ጣቢያ የወሰዱ ሲሆን የእሳቸው ቢሮ ዋና ስራ ያለ እድሜ ጋብቻ የተፈጸመባት ልጅን ማዳን ሲሆን ቀሪው ስራ የፖሊስና የፍ/ቤት መሆኑን ገልጸዋል ። አግቢው ፣ ልጅቷ እና እናቷ በአሁኑ ወቅት በሕግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ ።

የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትና የከተማዋ ሴቶች ፣ ሕጻናትና ማህበራው ጉዳይ ጽ/ቤት ለወሰዱት ፈጣን እርምጃ ምስጋናችንን እናቀርባለን ።

ደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
58 viewsNEWS, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 20:56:33
አዲስ አበባ ፖሊስ ተጨማሪ የደንብ ልብስ ስራ ላይ ማዋሉን አስታወቀ፡፡

የፀጥታ ተቋማትን የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብሶቹን  አመሳስሎ መጠቀም በህግ የሚያስጠየቅ ተግባር መሆኑ ተገልጿል፡፡


በአገር አቀፍ ደረጃ የፖሊስ ተቋማትን ለማዘመን በተያዘው ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መሰረት የፖሊስ ሰራዊት አርማ እና የደንብ ልብስ እንዲቀየር መደረጉ ይታወቃል፡፡ 

የአዲስ አበባ ፖሊስ ስትራቴጂክ ዕቅዱን መሰረት በማድረግ ልዩ ልዩ አዳዲስ የደንብ ልብሶችን አስመርቆ እየተገለገለ ይገኛል፡፡


ተቋሙ ከዚህ ቀደም ለተወርዋሪ ኃይል ሲጠቀምበት ከነበረው የደንብ ልብስ በተጨማሪ ከጥር 10 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተጨማሪ የደንብ ልብስ ስራ ላይ እንደሚያውል በአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡


የአዲስ አበባ ፖሊስ የተወርዋሪ ኃይል እየተገለገለበት ካለው የደንብ ልብስ በተጨማሪነት ስራ ላይ እንዲውል ያደረገው የደንብ ልብስ በተሻለ መልኩ ጥራቱን ጠብቆ የተዘጋጀ መሆኑን ም/ኮማንደር ማርቆስ ገልፀው ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አካለት ይህንን የደንብ ልብስ የለበሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራሮችና አባላት መሆናቸውን ተገንዝበው ተገቢውን ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡


የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ መገልገል ሆኖ አስመስሎ መጠቀም የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑን ኃላፊው አስታውሰው የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ የሚገለገሉ ሆነ አመሳስለው የሚጠቀሙ አካላት ከህገወጥ ድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገበ የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
52 viewsNEWS, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 20:55:25
በፍቃዳቸው ከነበሩበት ሃላፊነት ለቀቁ!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትላቸው በፍቃዳቸው ከሥራቸው መልቀቃቸው ተገለጸ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው ሰለሞን አረዳ “በፍቃዳቸው ከሥራቸው መልቀቃቸው” ታውቋል።


ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 9 እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።


ይህን ተከትሎ ረዳት ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሾሙ፤አበባ እምቢአለ ደግሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡
መረጃ በፍጥነት ለማግኘት እዚህ ግቡ 
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
53 viewsNEWS, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 16:02:55
ተሾሙ!

ቴዎድሮስ ምህረት ከበደ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾመዋል፡፡

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ፕሬዚደንት በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
67 viewsNEWS, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 11:43:27 የአዲስ  አዳማ  የፍጥነት መንገድ በአደጋ ምክንያት ተዘጋ።

የፈጣን መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ኢንስፔክተር ብርሃኑ ኃይለሚካኤል  ለኢትዮ ኤፍኤም እንዳስታወቁት የአዲስ  አዳማ  የፍጥነት መንገድ በአደጋ ምክንያት ተዘግቷል ብለዋል፡፡


ትላንት ምሽት 4:45 በአዳማ  ክፍያ ጣቢያ  በአጋጠመ የእሳት አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10 ሚሊየን ብር የተገመተ ንብረት መዉደሙ ይታወሳል ::

ይህን ተከትሎ ለጊዜው የፍጥት መንገዱ አገልግሎት መስተጓጎሉን ሰምተናል፡፡


በዚህም ከአዲስ አበባ ተነስተው  ወደ አደማ የሚያቀኑ አሽከርካሪዎች   ሃምሳ ስድስት ወይንም    በአሮጌው የአዳማ መንገድ መጓዝ ይችላሉ ተብሏል፡፡


ሁለተኛዉ አማራጭ  በስልሳ ወይንም (ምእራብ አዳማ ) በኩል  አማራጭ መንገድ አድርገው መጠቀም እንደሚችሉ የአካባቢዉ የትራፊክ ፖሊሶች ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቀዋል፡፡

ይህንን የሚያስተባብሩ   ጠቋሚ የደህንነት ሰራተኞች እንደሚገኙ በስራፍው የሚገኙት   የፈጣን መንገድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ኢንስፔክተር ብርሃኑ ኃይለሚካኤል  ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡


መንገዱ በፍጥነት ተስተካክሎ  ለተሸከርካሪ ክፍት  እንደሚሆንም  ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቷል፡፡

ትናንት ምሽት ለደረሰው የእሳት አደጋ ምክንያት የሆነዉ የአበሻ አረቄ  በርሜል የጫነ ኤፍ ኤስ አር  ተሽከርካሪ በእንቅስቃሴ ላይ እንዳለ  በመቃጠሉ ነዉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ሌሎች ሶስት ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸዉን  የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በሰዓቱ   እሳቱ ተባብሶ በተሽከርካሪዎች  እና  አንድ የክፍያ ጣቢያ ትኬት ቆራጭ በጥቅሉ የ4 ሰዎች ህይወት ወዲያው ሊያልፍ መቻን ነግረውናል፡፡

ተጨማሪ  አራት ሰዎችም  ከባድ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸዉ በአዳማ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ ብለውናል።
@global_mereja
@global_merejabot
67 viewsNEWS, 08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-17 11:42:24
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ 2 አመራሮችና 6 ባለሙያዎች በቁጥጥር ሥር ዋ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ኹለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

በቁጥጥር ሥር የዋሉትም አመራሮች፡-

1. መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ

2. ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ሃላፊ

እንዲሁም ፈፃሚዎች ፡-

3. ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)

4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)

5. በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)

6. ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)

7. ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)

8. ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) መሆናቸው የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የተጀመረው ሕግን የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙስና ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
66 viewsNEWS, 08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 21:08:12
የሩሲያ ጦር ማርሹን ቀየሯል
ጥቁር ባሕር ላይ አስደንጋጭ ነገር ተፈጥሯል!

>ኔቶ በፍጥነት ለዩክሬን የጠየቀችው ይሰጣት እያለ ነው
>የሩሲያና ቤላሩስ ጦር ወታደራዊ ልምምድ ብሎ ባልተጠበቀ አቅጣጫ መጥቷል
>ማርኮር የተባለው ዘግናኝ ድሮን ወደ አውደ ውጊያው ገብቷል

አንድ አመቱን ሊደፍን ቀናቶች የቀሩት የሩሲያ ዪክሬን ሲደመር ኔቶ ጦርነት መልኩን ቀይሯል።

ልክ የዛሬ አመት ሩሲያ ዩክሬን ላይ የመጀመሪያውን በትር ስታሳርፍ ተጠቅማው የነበረውን አንድ ጆከር ዳግም በሌላ አቅጣጫ መዛለች ምንድነው ካልን ደግሞ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የሚል ነው። ሩሲያ ከጎረቤት ቤላሩስ ጋር የጋራ ወታደራዊ ልምምዷን መጀመሯ ዛሬ በሰበር ዜና ከጥቁር ባሕር ሰርጥ ተሰምቷል። በሰማይ የሚደረገው ኒውክለር ሚሳኤል ተሸካሚ የጦር አውሮፕላኖች የሚሳተፉበት ልምምድ አሁን በምድር ጦር ተጅምሯል።

ይሄ ከመሆኑ አስቀድሞ የዩክሬኑ መሪ የሩሲያ ጦር ወደ ዋና ከተማዋ ኬቭ ዘልቆ መግባት ጀምሯል ከቤላሩ አቅጣጫም በወታደራዊ ልምምድ ሰበብ ዋና ከተማው ኬቭን ጨምሮ መላው ዩክሬንን ለመጠቅለል ከሩሲያ ብቻ 2 መቶ ሺ ጦር ያቀፈ አዲስ የውጊያ ስልት ነድፈዋል የሚሉ ምክኒያቶችን በመዘርዘር ለአሜሪካ መሩ የምዕራቡ ሃይል ተጨማሪ የመሳሪያ እገዛን ጠይቋል።

ከሰሞኑ ዋግነር ጦርነት ከፊት ያሰለፈው የሩሲያ ጦር ለአውሮፓ የጨው እናት የምትባለውን ከተማ ደም አፋሳሽ ውጊያ አድርጎ መቆጣጠሩና ወደፊት መገስገሱን ተከትሎ የኔቶ ቃል አቀባይ ጄንስ ስቶልተንበርግ በፍጥነት ለዩክሬን የጠየቀችው እንዲሰጣት የሚል ውሳኔ አዘል ንግግር አድርገዋል።

ይህ በእንዲህ ሳለ ሩሲያ በሰው ልጆች ላይ አልጠቀመው ምክኒያቱም ዘግናኝ ነው ያለችውን ማርኮር የተሰኘውን ድሮኗን ወደ አውደ ውጊያው ማስገባቷንም አሳውቃለች።
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
73 viewsNEWS, 18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 21:06:06
ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ አይነ-ስውራንን ለመደገፍ የሚደረገውን ዘመቻ ተቀላቀለ

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በኢትዮጵያ የሚገኙ አይነ-ስውራን ዜጎችን  ለመደገፍ የሚደረገውን ዘመቻ መቀላቀሉን አስታውቋል፡፡

ሜሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት÷ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ አይነ ስውራን  ዜጎችን  ለመደገፍ ከኦርካም ቴክኖሎጂ ጋር በትብብር ለመስራት በመስማማቴ ክብር ይሰማኛል ብሏል፡፡

የኦርካም ቴክኖሎጂ በሺህዎች የሚቆጠሩ አይነ ስውራንን ሕይወት እያሻሻለ መሆኑን ያነሳው ሜሲ÷ቴክኖሎጂው አይነ ስውራን ህልሞቻቸውን እንዲያሳኩ ይረዳቸዋል ብሏል፡፡

የቀዳማዊ እመቤት ጽህፈት ቤት በቅርቡ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት የሆነ ኦርካም ማይ አይ የተሰኘ አይነ ስውራንን የሚያግዝ መነጽር ለ2 ሺህ አይነ ስውራን ማስረከቡ ይታወሳል፡፡

ይህ ዘመናዊ መርጃ መሳሪያ አማርኛም ሆነ እንግሊዝኛ ያነባል፤ የገንዘብ ኖቶችን ይነግራል፤ ቀለም ይለያል ከፊት ለፊት ምን እንዳለ እና ማን እንደመጣ መዝግቦ በመያዝ መረጃ ይሰጣል፡፡

ኦርካም አይነ ስውራን በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ታግዘው የተሻለ ህሕወት እንዲመሩ ለማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም ነው።
https://t.me/+TzosZJYH8TDoROZU
65 viewsNEWS, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ