Get Mystery Box with random crypto!

የሀዘን እንጉርጉሮ የሸክላ እቃን እሳት ይፈትነዎል የሰውንም ገላ አፈር ይበላዎል ወፍ ከዘመዱ ይኖ | ሰናይ ግጥም

የሀዘን እንጉርጉሮ

የሸክላ እቃን እሳት ይፈትነዎል
የሰውንም ገላ አፈር ይበላዎል
ወፍ ከዘመዱ ይኖራል
ሰውም ኑሮ ኑሮ ወደ አያቶቹ ይጨመራል
ዝናቡ አመረረና ብላቴናውን ወሰደ
መኖሪያ አሳጥቶ ቤተሰቡን አሰደደ
ምነው እዮባ ምነው በክረምቱ
ምነው በጨለማው ምነው በሌሊቱ
አፈር ለመሆን ምን አስቸኮለህ ቢወጣ ክረምቱ
ሞት ሆይ ሰው በደህና ሲኖር ቀምተህ የምትወስደው ላፈር
ምነው ሰውን ብታከብር ብታፍር


ባለፈው እሁድ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በተፈጠረው የጎርፍ እና የመጋዘን መደርመስ አደጋ ወጣት #እዮብን አተናል በጣም አዝነናል በእውነት ብዙ ህልም ማሳካት የሚፈልገው ነገር ይኖራል ግን ህይወት እንደዚ ነው እኛ ስለፈለገን አይደለም ምንም ነገር የሚሆነው ሁላችንም መጠንቀቅ ነው ያለብንን ያለነው ክረምት ላይ ስለሆነ ዝናቡም እየከበደ ነው ስለዚህ ነቅታቹሁ ተኙ እያልኩ የወንድማችንን ነፍስ በአፀደ ገነት ያኑርልን

በእኔ እና በግጥም ቤት ስም ይሁንልኝ ሰናይት ሲሻው

@giximochi