Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ንባብ እና አንባቢን ለማወዳጀት እና ውጤታማ ትውልድን ለማፍራት | ግቢ Memes🇪🇹

ማስታወቂያ

ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ንባብ እና አንባቢን ለማወዳጀት እና ውጤታማ ትውልድን ለማፍራት የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

የመጻሕፍት ባንኩ እስካሁን ድረስ ከራሱና ከበጎ አድራጊ ወዳጆቹ ከሰላሳ አራት ሺህ (34,000) በላይ መጻሕፍትን አሰባስቦ በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ አንዳንድ ትምሕርት ቤቶች ፣ ንባብ ቤቶችና ማረሚያ ቤቶች በነፃ ለግሷል።

አሁን ደግሞ፣ ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ይህን መሰል ተግባራት በስፋት ያከናውን ዘንድ የአስተዳደር ወጪዎቹን ይሸፍንለት ዘንድ፣ የመጻሕፍት መደርደርያዎችን አሰርቶ በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

የመጻሕፍት መደርደርያዎቹ ለራሳችሁ(ለቢሮም፣ ለመኖርያ ቤትም)፣ ለተማራችሁባቸው ትምህርት ቤቶች፣ ለምትወዷቸው ቤተሰቦች እና ወዳጆች እንዲሁም ለምታደንቋቸው ግለሰቦች ጭምር እንደ ስጦታ የሚበረከቱ ናቸው።

ለበለጠ መረጃ ፦0900651010
                      -0976066720 ይደውሉ።
በቴሌግራም :- https://t.me/zMARAKI
መመልከት ይችላሉ። እንዲሁም በተጠቀሱት ስልክ ቁጥሮች እና @BKP2727 በቴሌግራም ሊጽፉልን ይችላሉ።