Get Mystery Box with random crypto!

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sane

የቴሌግራም ቻናል አርማ gfyygy — አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sane
የቴሌግራም ቻናል አርማ gfyygy — አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sane
የሰርጥ አድራሻ: @gfyygy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ።
ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ
እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-24 10:44:16 በወንድማማቾች መካከል የጥላቻና በጎሪጥ የመተያየት ፍቱን መድኃኒት
———
በተለይ በዱኒያዊ ነገር ተጨቃጭቀህ ወደ ጥላቻና በጎሪጥ መተያየት ከመሄድ ተቆጠብ!!። የተጣላሀው ሰው ካለም የሚከተለውን ፍቱን መድኃኒት ወስደህ ነፍሲያህን አሸንፈህ ብትበደልም እንኳን ይቅር በል!፣ አላህ አንተን ስንት ነገር ይቅር ብሎሃል???

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሂላህ) እንዲህ ብለዋል:-
«እርስበርስ ከመጠላላት በሚከተለው መልኩ መጥራት ይቻላል:-

በመጀመሪያ:- በዚህ መጠላላት ያለውን ወንጀል እና የሚያመልጠውን መልካም ነገር ማስታወስ ነው። ስራዎች እንኳን ወደ አላህ የሚቀርቡት ሰኞና ሀሙስ ነው፣ በሁለት ሰዎች መካከል ጥል ካለ አላህ “እነዚህ እስከሚታረቁ ድረስ ስራቸውን አቆዩት” ይላል። አምላካችን አላህ በአንተና በወንድምህ መካከል ጥል ካለ ሰኞና ሀሙስ የስራህን ውጤት አይመለከትልህም ማለት ነው።

ሁለተኛው:- ይቅር በማለትና በመታረቅ፣ ይቅር ባዩ ብዙ መልካም ነገር እንዳለው ማወቅ ነው። ይህ ይቅር ባይነቱ አሸናፊነትን/ክብርን እንጂ አይጨምርለትም። ልክ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት:- “ለባሪያው ይቅር በባይነቱ አላህ አልጨመረለትም አሸናፊነትን ቢሆን እንጂ።” [ሙስሊም ዘግበውታል።]

ሶስተኛው:- ሸይጧን ጠላቱ እንደሆነና የጥላቻንና በጎሪጥ የመተያየትን እሳት በሙእሚኖች መካከል የሚያቀጣጥለው እሱ እንደሆነ ሊያውቅ ይገበዋል። ምክንያቱም ሸይጧን ሙስሊሞች ተዋደውና ተግባብተው ሲያይ ይተክዛል። ተበታትነው በመካከላቸው ጥላቻና በጎሪጥ መተያየትን ሰፍኖ ሲመለከት ይደሰታል።
ሰዎች በመጠላላትና በጎሪጥ በመተያየት ላይ ያለውን ጥቅምና ጉዳት በሚያስታውሱ ጊዜ ጥቅም ያለበትን በመያዝ ጉዳት ያለውን መተው ቅሮት የለውም!።

ነፍሲያህን በመታገል አደራ!! ምንም እንኳን ከላይ ሲታይ ያሳነስካት/ያዋረድካት ቢመስልህም በእውነቱ ግን አሸናፊ ታደርጋታለህ፣ ምክንያቱም ለአላህ ብሎ የተናነሰ አላህ ከፍ ያደርገዋልና አላህ ለባሪያው ይቅር ባይ በመሆኑ አሸናፊነትን እንጂ ሌላን አልጨመረለትም።
ይህን በተግባር ሞክረህ እየው! አንተ ይህን ባደረግክ ጊዜ ይቅር ካልክ በአንተና በወንድሞችህ መካከል ያለውን ነገር ካስተካከልክ በምቾትና በተረጋጋ ሁኔታ፣ በልብ መስፋትና ልብህ በደስታ የተሞላ ሆናህ ትኖራለህ። ነገር ግን በልብህ በነሱ ላይ ጥላቻ ካለ ነፍሲያህን በጭንቀትና በውጥረት ውስጥ ሆና ታገኛታለህ። ሸይጧን እየመጣ በሰውዬው ንግግር ላይ የተለያዩ መላምቶችን ይነግርሃል፣ ሸሪዓችን አንድ ሰው የወንድሙን ንግግር ሸር ቢመስለው እንኳን በመልካም መገመት እንዳለበት የደነገገ ከመሆኑም ጋር ሸይጧን ግን ሁሉንም በሸር እንዲጠረጥረው/እንዲያስበው ያደርገዋል።»
[ሸርህ አል-ሙምቲዕ ዐላ ዛዲል ሙስተቅኒዕ 2/341]
አላህ ነፍሲያቸውንና ሸይጧንን አሸንፈው ይቅር ከሚባባሉት ያድርገን!!።
ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
121 viewsAbdurahim Sane Adama, 07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:57:08
143 viewsAbdurahim Sane Adama, 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:57:08
138 viewsAbdurahim Sane Adama, 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ