Get Mystery Box with random crypto!

ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉን መሳሪያወች 1. መፍቻ ፦ ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል | Get Tech Info

ለሞባይል ጥገና የሚያስፈልጉን መሳሪያወች

1. መፍቻ ፦ ስልካችን ለመፍታት እና ለመግጠም ይጠቅማል።

2. መልቲ ሜትር:- ሬዚስታንስ ፣ ቮልቴጅ እንዲሁም ከረንት ለመለካት እና የሰርኪዩት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ይጠቅመናል።

3. ቲነር ፦ ዝገት ለመከላከል እና ቆሻሻ ለማስወገድ ይጠቅማል።

4. ፔስት ፦ አይሲዎችን በመንቀያና በማስቀመጫ ሰአት ቦርዳችንና የሚነቀለዉ አይሲ በሙቀት እንዳይጓዳ ይጠቅማል።

5. ብሎወር ፦ ሙቀትን በመስጠት አይሲዎችን ለመንቀልና ለማስቀመጥ ይጠቅማል።

6. ካዉያ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ ይጠቅማል።

7. ሊድ ፦ ሁለት የተላቀቁ ክፍሎችን ለመበየድ እንደ ቀላጭ የምንጠቀምበት ነዉ።

8. ጃምፐር ዋየር ፦ ሁለት የተለያዩ የሰርኪዩት ክፍሎችን /የተላቀቁ ክፍሎችን/ ለማያያዝ የሚጠቅም ቀጭን ሽቦ ነዉ።

9. ትዊዘር(ፒከር) ፦ አይሲ ወይንም ሌሎች የሞባይል ክፍሎች በብሎወር ስናሞቅ እንደ መቆንጠጫ የምንይዝበት ነዉ ።

10. ዲሲ ፓወር ሰፕላይ ፦ ከባትሪ የምናገኘዉን 3.7 ቮልት የሚሆን ቮልቴጅ የሚሰጥ ክፍል ነዉ።

ከዚህም በተጨማሪ ስልካችን ኦፕን ይሁን ሾርት ወይም ስልኮች የሶፍትዌር ችግር እንዳላቸዉና እንደሌላቸዉ ሊያሳየን የሚችል በጣም ጠቃሚ መሳሪያ ነዉ ። በተጨማሪም ስፒከርን ወይም ሪንገርን ለመፈተሽ ይጠቅመናል።

1. ኮምፒውተር ፦ ለሶፍትዌር ጥገና ፣ ለሃርድዌር ላይብረሪ እና ሙዚቃ ለመጫን ይጠቅመናል ።

2. ፍላሽ ቦክስ ፦ በሶፍትዌር ጥገና ሰአት በሞባይልና በኮምፒዉተር መሃል የሚገኝና ሁለቱን አካሎች የሚያግባባቸዉ መሳሪያ ነዉ ።

3. ቦርድ ፕሌት :- የስልካችንን ቦርድ በምንበይድበት ጊዜ ወይም አይሲ በምንነቅልበት ጊዜ ቦርዱ እንዳይነቃነቅ የሚያደርግ መሳሪያ ነዉ ።

4. ሶፍትዌር ኬብል ፦ በሶፍትዌር ጥገና ስአት ስልካችንን ከፍላሸር ቦክስ ጋር የሚያግባባ ነዉ።

5. ቫይብሬተር ፦ ዉሃ ዉስጥ ገብቶ ወይም ስታክ ያደረገ ስልክ እንዲሰራ ቫይብሬተር ዉስጥ ተዘፍዝፎ ፣ የተወሰነ ደቂቃ ይቆያል

Nurhasen Yesuf

#Share with your friend

@Gettechinfo