Get Mystery Box with random crypto!

Geez Media Center

የቴሌግራም ቻናል አርማ geezmediacenter — Geez Media Center G
የቴሌግራም ቻናል አርማ geezmediacenter — Geez Media Center
የሰርጥ አድራሻ: @geezmediacenter
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.39K
የሰርጥ መግለጫ

https://t.me/GeezMediaCenter

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 20:10:16 @GeezMediaCenter

ካለፈው የቀጠለ........

ኅብራተ ግስ -- የግስ አይነቶች

፫) ነባር አንቀጽ ግስ

እነዚህ የግስ አይነቶች ከገቢርና ከተገብሮ ግስ የተለዩ ናቸው። ቍጥራቸውም ከተገብሮና ገቢር ግስ አንጻር ትንሽ ናቸው።
ከዚህ በፊት አሥሩ መራሕያን እንደ ነባር አንቀጽ ብለን ያየናቸው ከዚህ ምድብ ይመደባሉ።

ምሳሌ፦
ውእቱ =  ነው
ቦ = አለ፣ ኖረ ፣ ነበረ
አኮ = አይደለም
አልቦ = የለም፣ አልኖረም፣ አልነበረም

፬) መደበኛ ግስ እና ኢመደበኛ ግስ


፩) #መደበኛ_ግስ የሚባሉት ከኀላፊ(ቀዳማይ) አንቀጽ እስከ ትእዛዝ (ራብዓይ)  አንቀጽ የሚዘረዘሩ እና በንኡሳን አናቅጽ የሚዘረዘሩ ግሶች ናቸው።

የመደበኛ ግስ መለያዎች፦


መደበኛ ግስ ኹልጊዜ የሚቀመጠው
በ #ውእቱ_መራሒ ነው። 
የመጨረሻ  ፊደሉ ምንጊዜም #ግእዝ ፊደል ነው።

ምሳሌ፦

ፈነ  =>  ላከ
ወሰ =>  ወሰደ
ተንበ => ለመነ
አእመ => አወቀ
=> ሾመ
ክህ => ቻለ 
=> ጻፈ

ከምሳሌው እንደምናየው ግሶች መጨረሻቸው ግእዝ ፊደል ነው።

መደበኛ ግስ በካዕብ፣
በሣልስ፥ በራብዕ፥ በኀምስ ፥ በሳድስ፥
በሳብዕ አይጨረስም ማለት ነው።

በግእዝ የጨረሰ ቃል ኹሉ #ግስ ላይኾን ይችላል።

የመደበኛ ግስ መራሒው (ባለቤቱ)  #ውእቱ(እሱ) ነው።
ወሰደ ብለን ማን ብለን ስንጠይቅ እርሱ የሚል እናገኛለን።

ለምሳሌ ፦ አኃዝ በግእዝ ፊደል ይጨርሳሉ ነገር ግን ግስ አይደሉም።
አሐደ፥ ክልኤተ፣ ሠለስተ የመሳሰሉት..

፪) ኢመደበኛ ግስ
ከላይ የተዘረዘሩትን የመደበኛ ግስ ጠባያት የማያሟሉ ግሶች ኢመደበኛ ግሶች ይባላሉ

ምሳሌ፦ ይቤ => አለ

መልመጃ ፪.፪

አሥሩ መራሕያን እንደ ነባር አንቀጽ ሲያገለግሉ ያላቸውን ትርጉም አብራሩ።

@GeezMediaCenter
646 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 20:04:08 ሰላም ለኵልክሙ ኦ ፍቁራነ አርድእት።

የግእዝ ቃላት በሙሉ ግስ ተብለው ይጠራሉ በግእዝ ቋንቋ ያሉ ቃላት በሙሉ በ፰(8) ክፍል(አርእስቶች) ይከፈላሉ።

እነርሱም ፩ የቀተለ ዘሮቹ
አወራረድ!!!

ቀተለ ፦ ገደለ
ይቀትል ፦ ይገድላል
ይቅትል ፦ ይገድል ዘንድ
ይቅትል ፦ ይግደል
ቀቲል ቀቲሎት ፦ መግደል
ቀታሊ ፦ የገደለ
ቀታሊያን ፦ የገደሉ
2 የቀደሰ ዘሮቹ አወራረድ
ቀደሰ ፦ አመሰገነ
ይቄድስ ፦ ያመሰግናል
ይቀደስ ፦ ያመሰግን ዘንድ
ይቀድስ ፦ ያመስግን
ቀድሶ ቀድሶተ ፦ ማመስገን
ቀዳሲ ፦ ያመሰገነ
ቀዳስያን ፦ ያመሰግኑ
3 የገበረና ዘሮቹ አወራረድ
ገበረ ፦ አደረገ
ይገብር ፦ ያደርጋል
ይግብር ፦ ያደርግ ዘንድ
ይግበር ፦ ያድርግ
ገቢር ገቢሮት ፦ ማድረግ
ገባሪ ፦ ያደረገ
ገባሪያን ፦ ያድርጉ
4 የአእመረ ዘሮቹ አወራረድ
አእመረ ፦ አወቀ
የአምር ፦ ያውቃል
ያእምር ፦ ያውቅ ዘንድ
ያእምር ፦ ይወቅ
አእምሮ አእምሮት ፦ ማወቅ
አእማሪ ፦ ማወቅ
አእማሪ ፦ ያወቀ
አእማሪያን ፦ ያወቁ
5 የባረከ ዘሮቹ አወራረድ
ባረከ ፦ አመሰገነ
ይባርክ ፦ ያመስግናል
ይባርክ ፦ ያመሰግን ዘንድ
ይባርክ ፦ ያመስግን
ባርኮ ባርኮት ፦ ማመስገን
ባራኪ ፦ ያመሰገነ
ባራኪያን ፦ ያመስግኑ
6 የሤመና ዘሮቹ አወራረድ
ሤመ ፦ ሾመ
ይሠይም ፦ ይሾማል
ይሢም ፦ ይሾም ዘንድ
ይሢም ፦ ይሹም
ሠዩም ሠዩሞት ፦ መሾም
ሠያሚ ፦ የሾመ
ሠያሚያን ፦ የሾሙ
7 የብህልና ዘሮቹ አወራረድ
ብህለ ፦ አለ
ይበል ፦ ይላል
ይበል ፦ ይል ዘንድ
ይበል ፦ ይበል
ብሂል በሂሎት ፦ ማለት
በሃሊ ፦ ያለ
በሃልያን ፦ ያሉ
8 የቆመ ዘሮቹ አወራረድ
ቆመ ፦ ቆመ
ይቀውም ፦ ይቆማል
ይቁም ፦ ይቆም ዘንድ
ይቁም ፦ ይቁም
ቀዊመ ቀዊመት ፦ መቆም
ቀዋመ ፦ የቆመ
ቀዋሚያን ፦ የቆሙ
  

@GeezMediaCenter
498 viewsedited  17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:45:26 መልመጃ ፪.፩

፩) ከሚከተሉት ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ ገቢር ግስ እና ተገብሮ ግስ ለይታችሁ አውጡ።

ሀ) ገብርኤል መልአከ ተፈነወ ኀበ ድንግል ማርያም። (ገብርኤል መልአከ ወደ ድንግል ማርያም ተላከ።)

ለ) ዘመረ ዳዊት ዝማሬ በበገና። (ዳዊት መዝሙርን/ዝማሬን በበገና ዘመረ።)

ሐ) እግዚአብሔር ተሰብሐ በአበዊነ። (እግዚአብሔር በአባቶቻችን ተመሰገነ።)

መ) ለዓለም ጸሐፈ መጽሐፈ። (ለዓለም መጽሐፍን ጻፈ።)

ሠ) ክርስቶስ ተወልደ እምድንግል። (ክርስቶስ ከድንግል ተወለደ።)


፪) ከጥያቄ ቍጥር ፩ ላይ ያወጣችኋቸውን ገቢር እና ተገብሮ ግሶች፣ ገቢሩን ወደ ተገብሮ ግስ፣ ተገብሮ ግሱን ወደ ገቢር ግስ ለውጡ።


@GeezMediaCenter
705 views19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 12:16:18 https://t.me/GorgoraMedia
760 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:44:35 ነሐሴ ፲፯/፳፻፲፬ ዓ.ም
            ምዕራፍ ፪
                 ግስ

.፩. ግስ እና የግስ አይነቶች

ከዚህ በፊት እንዳየነው የአንድ ቋንቋ የተለያዩ የቃል ክፍሎች አሉት። እነዚህ የቃል ክፍሎችም መራሕያን፣ ግስ፣ ተውሳከ ግስ፣ ስም፣ ቅጽል፣ መስተዋድድ፣ መስተጻምር የመሳሰሉት ናቸው።

#ግስ ከእነዚህ የቃል ክፍላት መካከል ሲኾን "ገሰሰ" ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው። ትርጕሙም ዳሰሰ፥መረመረ ማለት ነው።  ግስ ማለት ደግሞ የሚዳሰስ፣ የሚመረመር ማለት ነው።

ግስ ማለት በአጭር ቃል ሲገለጥ በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ #ድርጊትን_ገላጭ_ዐረፍተነገርን_የሚቋጭ ቃል ማለት ነው።

<<ለምሳሌ፦ ዳዊት በሬ ገዝቶ _።>>
ብለን ብንጽፍ ዐረፍተ ነገሩ አልተቋጨም፣ ማሰሪያ፣ መጠቅለያ ቃል ያስፈልገዋል።
በክፍት ቦታው መጣ፣ ሄደ፣ ተቀመጠ፣ አረሰ፣  ወዘተ.... የመሳሰሉ ግሶችን መሙላት ይቻላል።

#ግስ- በዐረፍተ ነገር ውስጥ ድርጊቱ #በማን፣ #በማን_ላይ መፈጸሙን የሚነግረን ቃል ነው። ድርጊትን የሚገልጥ፣  መሆን አለመሆንን የሚያሳይ የቃል ክፍል ነው።

የግስ ምሳሌዎች፦
በልዐ =  በላ
ሖረ  =  ሄደ
ተንበለ =  ለመነ
ቀደሰ =  አመሰገነ
ቀተለ = ገደለ
አእመረ = አወቀ
ተፈነወ =ተላከ
ተገብረ = ተሠራ

..........ወዘተረፈ


፫.፪. ኅብራተ ግስ (የግስ አይነቶች)

አባ
ቶች ግስን ለጥናት እንዲመቻቸው በተለያየ መንገድ ከፍለው ያጠኗቸዋል።

ከድርጊት ከመግለጽ አንጻር ግሶች በሁለት ይከፈላሉ

፩. ገቢር ግስ  (አድራጊ ግስ)

ይህ
አይነት ግስ በአንድ አረፍተ ነገር ውስጥ ድርጊት የአድራጊነትን ወይም ፈጻሚነትን ኹነት የሚገልጥ፣ ቃላትንና ሐረጋትን የሚስብ ነው። በዐማርኛው አድራጊ ግስ፣ በእንግሊዝው active verb (active voice) የምንለው ነው።

ምሳሌ አንድ፦
አብርሃም መርሐ ማኅበረነ።
     (አብርሃም ማኅበራችንን መራ።)
       
ከዚህ ምሳሌ የምረዳው ግሱ #መርሐ የሚለው አድራጊ ግስ መሆኑን ነው። አብርሃም የተባለው ሰው መምራት የተባለውን ድርጊት በማኅበሩ ላይ እየተገበረ ነው። 
አብርሃም #ምን_አደረገ ? ብለን ብንጠይቅ  #መርሐ - መራ የሚል መልስ እናገኛለን።
#ማኅበረነ የሚለው ቃል ደግሞ ተሰሐቢ ቃል፣ ድርጊቱ የተፈጸመበት ነው።
አብርሃም #ማንን_መራ ብለን ብንጠይቅ ማኅበሩን የሚል መልስ እናገኛለን።

ምሳሌ ሁለት፦
እግዚአብሔር ገብረ ሰማየ ወምድረ።
   (እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን  ፈጠረ።)
    
ከዚህ ምሳሌ የምንረዳው #ገብረ የሚለው ግስ ገቢር ግስ (አድራጊ ግስ) መሆኑን ነው።  ገብረ = ሠራ፣ ፈጠረ

<<እግዚአብሔር ገብረ ሰማየ ወምድረ>> በሚለው ዐረፍተነገር ውስጥ እግዚአብሔር መፍጠር የተባለ ድርጊት መፈጸሙን ያስረዳናል።
➻ማን ፈጠረ ብለን ሰንጠይቅ ድርጊት ፈጻሚውን እናገኛለን።
➻ማንን ፈጠረ ስንል ተስሐቢውን/የድርጊቱን ተቀባይ እናገኛለን።
ሰማየ ወምድረ- ሰማይንና ምድርን የሚለውን እናገኛለን

ገቢር ግስ(አድራጊ ግስ) በአንድ ዐረፍተ ነገር ውስጥ #ማን ብለን ስንጠይቅ ድርጊቱ በማን መፈጸሙን የሚነገረን፣ #ማንን ብለን  ስንጠይቅ ድርጊቱን በማን ላይ እንደተፈጸመ የሚነግረን፣ ድርጊት ፈጻሚ አመልካች ቃል ወይም ሐረግ ተሰሐቢ የግስ አይነት ነው።


፪. ተገብሮ ግስ (ተደራጊ ግስ)

ይህ
የግስ አይነት ድርጊቱ በማን ላይ እንደተፈጸመ፣ የድርጊት ተቀባይ አካልን የሚነግረን የግስ አይነት ነው። በዐማርኛው ተደራጊ ግስ፣ በእንግሊዝው passive verb (passive voice) የምንለው ነው። ቃል ወይም ሐረግ አይስብም።

ምሳሌ፦
ክርስቶስ ተሰቅለ በዲበ መስቀል።
    (ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቀለ።)
       
በዚህ ምሳሌ ላይ ማን #እንደሰቀለ ሳይሆን #እንደተሰቀ ይነግረናል።
#ማን_ተሰቀለ ብለን ስንጠይቅ ድርጊቱ የተፈጸመበትን አካል ይነግረናል።


ይህ ግስ የሚገኘው ገቢር ግስ ላይ መነሻ ቅጥያ <ተ> በመጨመር ነው።

ገቢር ግስ          ተገብሮ ግስ
ገብረ
              ተገብረ
ሰቀለ               ተሰቅለ
ሰብሐ              ተሰብሐ
ጸሐፈ               ተጽሕፈ

የተገብሮ ግሶች መነሻቸው <ተ> ፊደል ናት።

ለብዉ-- አስተውሉ፦
በ <ተ> የሚጀምር ቃል ሁሉ ተገብሮ ግስ አይደለም።
ለምሳሌ፦ ተንበለ - ለመነ፣ ተመነየ -ተመኘ  የመሳሰሉ ቃላት ገቢር ግሶች ናቸው።
በ<ተ> የሚጀምር ግስ የተገብሮ ግስ መሆኑን የምንለየው የተሰጠንን ግስ <ተ>ን አውጥተው የቀረው ቃል ገቢር ግስ ከኾነ ነው።

ምሳሌ

ሀ) ዳዊት በልዐ ኅብስተ። (ዳዊት ምግብን በላ። )
ለ) ዮም ተቀደሰ ቅዳሴ። (ዛሬ ቅዳሴ ተቀደሰ።)

፩} የግስ አይነት
ሀ) ግስ ፦ በልዐ = በላ
   የግስ አይነት፦ ገቢር ግስ

ለ) ግስ ፦ ተቀደሰ = ተቀደሰ፣ ተመሰገነ
     የግስ አይነት፦ ተገብሮ ግስ

፪} ገቢር ግስ ወደ ተገብሮ፣ ተገብሮ ወደ ገቢር ግስ ሲቀየር

  ገቢር ግስ    ተገብሮ ግስ

ሀ)   በልዐ            ተበልዐ
ለ)   ቀደሰ             ተቀደሰ

የተሰመረበት  ግስ የተቀየረው ግስ ነው።

#በልዐ የሚለው #ገቢር ግስ ወደ #ተገብሮ ግስ ሲቀየር #ተበልዐ ይሆናል።
#ተቀደሰ የሚለው #የተገብሮ ግስ ወደ #ገቢር ሲቀየር #ቀደሰ ይሆናል።

(ይቀጥላል)

@GeezMediaCenter
877 viewsedited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:15:52 ለቀጣይ ፈተና ስለሚያግዟችሁ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ


፩.  መራሕያን በመደብ፣ በቁጥር፣ በጾታ መድቧቸው

፪. የተሰጠንን ግስ  በንሕነ መራሒ ለመዘርዘር (ለማርባት) የግሱን የመጨረሻ ፊደል ወደ _ በመቀየር _ቅጥያ እንጨምራለን።


፫. በጹጻን የግእዝ ፊደላት የተጻፉ ቃላትን ዘርዝሩ

፬. አንትሙ ከሰትክሙ ካለ ውእቶን __ ይላል

፭.  << ሜላት ወአስቴር አርድእተ ግእዝ ውእቶን >> በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ የተሰመረበት  <<ውእቶን>> የሚለው ቃል ትርጒም__ነው፤ አግልግሎቱም__ነው

፮.  <<እሱ>> ብለን <<ውእ>> ካልን፣ <<እሱን>> ብለ ...... እንላለን።

፯.  << ውእቶን አንስት ሖራ>>  በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ የተሰመረበት ቃል <<ውእቶን>> ትርጉም__ነው? አግልግሎቱም _ነው?


፰. <<፲፼፳፬፻>>ን  ወደ አረብኛ ቊጥር ቀይሩ

፱. << 654321>>ን  ወደ ግእዝ ቊጥር ቀይሩ


፲. ወዐለ የሚለውን ግስ በዐሥርቱ መራሕያን ዘርዝሩ። ወዐለ = ዋለ

፲፩ የሚከተሉትን ቃላት የትርጉም ልዩነታቸውን ተወያዩ

አ) ፈጸመ እና ፈፀመ
በ) ነስሐ እና ነስኀ
ገ)መዐተ እና መአተ
ገ) መአደ እና መዐደ


፲፪. <<ዝንቱ ደብተር ውእቱ፤  ዝንቱ ውእቱ __ ደብተር>>
በክፍት ቦታው ላይ ትክክለኛዎን መራሒ በመሙላት ጻፉ።

፲፫. በርብ መራሕያን (ፈነወ= ላከ) በሚለው ሦስት ምሳሌ ሥሩ።

፲፬. አንተ ፈነውከ____። (ፈነወ = ላከ)
     በባዶ ቦታው ሊገቡ የሚችሉ የመራሕያን አይነት ዘርዝሩ

፲፭. እሷ ብለን ይእቲ ካልን፣ እሷ ራሷ ብለን __እንላለን?

@GeezMediaCenter
1.0K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:18:46 ደብር ርጉዕ ወደብር ጥሉል፣ ለምንት ይትነስዑ አድባር ርጉዓን፤ ደብር ዘሠምሮ እግዚአብሔር የኀድር ውስቴቱ።
መዝ ፷፯፥፲፫-፲፮

የእግዚአብሔር ተራራ የፀናና የለመለመ ተራራ ነው፣ የፀኑ ተራራዎች ለምን ይነሳሉ፣ እግዚአብሔር ያድርበት ዘንድ ይህን ተራራ ወዶታልና፤ በእውነት እግዚአብሔር ለዘለዓለሙ ያድርበታል።

ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ፣ ወይሴብሑ ለስምከ፤ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል።
መዝ ፹፰፥፲፪-፲፫

ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል፤ ለስምህም ይዘምራሉ፣
ክንድህ ከኃይል ጋራ ነው።
እንቋዕ ለበዓለ ደብረ ታቦር አብጻሐነ ወአብጻሕክሙ።

ቀጥሎ

የምልማድ ማብራሪያ

፩. ቃለ ሕይወት በሐመሩ #ሐ ይጻፋል፡፡
ምክንያቱም መነሻ ግሱ #ሐይወ➳ዳነ፣
ሕያው ኾነ ማለት ሲኾን #ሕይወት ከሐይወ የሚወጣ ስም ነው፡፡

ማሕየዊ ፣ ሕያው፣ ሔዋን
ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት


፪. #አደመ➳ አማረ፥ተዋበ
አዳም ➳የሚያምር፣ደስ የሚያሰኝ ፣ውብ ፣
መልከ መልካም ማለት ነው።

ዐደመ➳ሤራ አዘጋጀ
ዐድማ➳ሤራ፥ተንኮል፥ወጥመድ
ዐደመ ➳ጊዜ ቀጠረ፣ ቀን ወሰነ(ሌላ ትርጕሙ)
ተዐዳሚ➳ታዳሚ (ለሰርግ፣ ለጉባኤ፣ለስብሰባ)
ዕድሜ ➳ ቀጠሮ፣ የተወሰነ ጊዜ፣ዘመን


፫. #ዐርበ➳ገባ፥ተካተተ
ምዕራብ➳የፀሓይ መግቢያ፥መካተቻ።
ዕለተ ዐርብ ከዚሁ ግስ የወጣ ነው።
ዐርብ የፍጥረታት መካተቻ ነውና።


፬. #ሰረቀ➳የራሱ ያልሆነን ወሰደ
ምስራቅ➳የሌቦች መገኛ፥መስረቂያ
#ሠረቀ ➳ወጣ፣ ተገኘ፣ ተወለደ
ምሥራቅ ➳የፀሓይ መውጫ

▣ ሴት ልጁን ቆንጆ፣ ዐይናማ፣ መልከ መልካም ማለት ፈልጎ #ምሥራቅ አላት እንበል። ምን ችግር አለው በ #ሰ ቢጻፍ ብሎ አንድ ሰው #ምስራቅ እገሌ ብሎ ቢጽፍ ሰደባት እንደ ማለት ነው። ምስራቅ የሌቦች መገኛ እንደ ማለት ስለኾነ።
ስለዚህ ሌባ ለማለት ሰራቂ እንጂ ሠራቂ አንልም፡፡
ሰረቀ ብርሃን?
ሠረቀ ብርሃን➙ብርሃን ወጣ


፭. #ሰረገ ግስ ሲኾን ትርጕሙ #ደገሰ
ማለት ነው። #ሰርግ ደግሞ ስም ነው ትርጕሙ ድግስ፥ የጋብቻ በዓል ።
#ሠረገ ግስ ሲኾን ትርጕሙ ወደ ውስጥ
ገባ ማለት ነው። #ሠርግ የሚለው ደግሞ ከሠረገ ይወጣል። ስለዚህ #ሠርግ ማለት መስኖ፥የመስኖ ውሃ (ቦዩ) ነው።
"ሠርጎ ገብ" ሲባል ሰምታችኋል?

አደራ ያላገባችሁ ስታገቡ መጥሪያው ላይ #ሠርግ ብላችሁ እንዳታጽፉ። እንዲህ ከኾነ ግእዝ ለሚያውቅ ሰው ድግስ ሊያበሉኝ ሳይኾን ቦይ ሊያስቆፍሩኝ ነው ብሎ አይታደምላችሁምና!

፮. Medhane alem የሚጻፈው በብዙኀኑ ኀ እና በዐይኑ ዐ #መድኃኔዓለም ተብሎ ነው ፡፡
ምክንያቱም መነሻ ግሱ #ድኅነ ➙ዳነ በመኾኑ።

ድኅነት ፣መድኀኒት፥ዳኅና፣

፯. #መሀረ➳ አስተማረ ማለት ሲኾን ከትምህርት ጋር ተያያዥነት ያለው ቃል በሃሌታው "ሀ" ይጻፋል።
#መሐረ ➳ ይቅር አለ ማለት ሲኾን ከምሕረት
ጋር ተያያዥነት ያለው ቃል ኹሉ በሐመሩ "ሐ" ይጻፋል። ስለዚህ ፦
#ኪዳነ_ምሕረት☞የምሕረት፥የይቅርታ ኪዳን
ውል ማለት ሲኾን በሐመሩ ሐ ሲጻፍ ብቻ ነው ትርጕሙ ከይቅርታ ጋር የሚያያዘው፡፡ በሌሎች ከተጻፈ ትርጕሙ ይለወጣል፡፡
መምህር፣ ትምህርት፣ ምሁር
መሐረነ አብ ፣መሓራ ፥ዓመተ ምሕረት


፰. #ሀይመነ ➙አመነ፣ታመነ
ሃይማኖት ➙ማመን ፣መታመን
#ሃይማኖተ አበው ➙የአባቶች ማመን
መታመን ማለት ነው።
መሀይምን ➳ምእመን፣ያመነ፣የታመነ


፱. #ነስሐ➳ተጸጸተ፥ተመለሰ
ንስሐ➳ጸጸት፥መመለስ
#ነስኀ➳ሸተተ፥ከረፋ
ንስኃ ➳መሽተት ፥መከርፋት

ትክክለኛው ንስሓ ነው። ግን የተለመደው በግእዙ ነው። በቅድሚያ ፊደሉን ከለየን በቀጣይ ግእዝና ራብዑን የምንለይበት ደረጃ እንደርሳለን።


፲. #መዐደ➳መከረ፥አስተማረ
ምዕዳን ➳ምክር፥ ተግሣጽ
ቃለ ምዕዳን➳ የምክር ቃል

#መአደ ➳ ሰፈረ ፣ከነዳ፣አስተካካለ
ማእድ➳የምግብ ማቅረቢያ፣ማድ፣ገበታ


፲፩) #መዐተ ➳ተበሳጨ፣ተቆጣ
◦መዐት➳ ብስጭት፣ቍጣ፣ተግሣጽ
◦እም መዐቱ ይሰውረነ➳ከቍጣው፣ ከመከራው ይጠብቀን፥ ይሰውረን

#መአተ ➳በዛ፣
◦ምእት ➳መቶ
◦መአት➳እጅግ ብዙ

◍ እም መዐቱ ➳እመዐቱ
(ወደፊት ትማሩታላችሁ)


፲፪) #ሥን ➳ደም ግባት፣መልክ፣
ሥነ ፍጥረት ➳የፍጥረት ውበት፣
ስለ ፍጥረት የሚያጠና....

#ሰነነ ➳ጥርስ አወጣ ከሚለው ግስ
ስን ➳ጥርስ
ስነ ፍጥረት ➳የፍጥረት ጥርስ
ስነ ሕዝብ ➳የሕዝብ ጥርስ


#ማጠቃለያ፦

ከላይ ፊደላት አንዱ በአንዱ ሲቀያየሩ ምን ያህል የትርጕም ልዩነት እንደሚያመጡ በምሳሌዎች አይተናል።
የኾነ ኾነና እኔና እናንተ የግእዝ ቃላትን በትክክለኛው ፊደል ለመጻፍ ምን ማድረግ አለብን?
ትክክለኛውንስ ፊደል እንዴት እናውቃለን?
ለሚለው በነገው ትምህርት እናያለን።

@GeezMediaCenter
2.8K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 18:49:34 መልመጃ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች ተወያዩባቸው።
(እም እሉ ተስእሎታት ተዝያንው )

ትክክለኛ መልስ የያዘ ነው ብላችሁ
የምታስቡትን ፊደል ምረጡ።

፩. ቃለ Hiwot ያሰማልን!
አ) ህይወት
በ) ሕይወት
ገ) ኅይወት
ደ) ኽይወት

፪. Adam የሚለው ሲጻፍ
አ) ዐዳም
በ) አዳም

፫.የፀሓይ መግቢያን የሚያመለክተው፦
አ) ምእራብ
በ) ምዕራብ

፬. የፀሓይ መውጫን የሚያመለክተው፦
አ) ምስራቅ
በ) ምሥራቅ

፭. የጋብቻ ሥነ ሥርዐት ለመግለጽ ፦
አ) ሰርግ
በ) ሠርግ

፮. Medhanealem ለማለት፦
አ) መድሀኔአለም
በ) መድኀኔዓለም
ገ) መድሐኔዓለም
ደ) መድሐኔአለም

፯. Kidane Mihret ለማለት፦
አ)ኪዳነ ምኅረት
በ)ኪዳነ ምህረት
ገ)ኪዳነ ምሕረት
ደ)ኪዳነ ምኽረት

፰. haimanot የሚለው ሲጻፍ
አ) ሃይማኖት
በ) ሐይማኖት
ገ) ኀይማኖት
ደ) ሓይማኖት

፱. ሰው ስለ ኀጢአቱ ተጸጽቶ ወደ
እግዚአብሔር የሚመለስበት፦
አ) ንሥሀ
በ) ንስኀ
ገ) ንስሐ
ደ) ንሥኸ

፲.ቃለ Medan እና ቡራኬ....
አ) ምዕዳን
በ) ምእዳን

፲፩. እም Meatu ይሰውረነ
አ) መዐቱ
በ) መአቱ

፲፪. Sine ፍጥረት
አ) ሥነ ፍጥረት
በ) ስነ ፍጥረት

@GeezMediaCenter
1.1K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 18:30:16 Channel photo updated
15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:26:45 ቀጣይ ሣምንት ፈተና ይኖረናል ከአሁኑ ተዘጋጁ!!!

@GeezMediaCenter
953 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ