Get Mystery Box with random crypto!

ዘመን ካሳለፋነው ታሪክ መማር የተሳነን ትናንት ያደናቀፈን ዛሬም የደገመን የዘመን ምርኮኞች የዘመን | Friends Message 💬

ዘመን
ካሳለፋነው ታሪክ መማር የተሳነን
ትናንት ያደናቀፈን ዛሬም የደገመን
የዘመን ምርኮኞች የዘመን እስረኞች
ዘመን መዘመኑ ዘመን መቀየሩ
ብዙም ግድ ያልሰጠን
ከዘመን ጋር መሄድ መጓዝ የተሳነን
ታሪክ ስናወራ ታሪክ ተሰራብን
ችግር ድር አድረቶ ዛሬያችንን ቀማን
የዘመን ምርኮኞች የዘመን እስረኞች
ከዘመን ተጣልተን ከዘመን ተኳርፈን
በትናንት ቆዝመን ዛሬያችንን ገለን
ነገያችንን ቀብረን
ታሪክ ሰናወራ ታሪክ ተሰራብን
ያ ያለፈ ትናንት ዛሬን ከኛ ነጥቆ
ነገን ጋረደብን
እናም...ነገያችን እንዲሆን የጋራ ከፋታ
ትናንትን ተውና ዛሬያችን ይፈታ::