Get Mystery Box with random crypto!

' ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው ' - የአ/አ ትምህርት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳ | Free Education Ethiopia ✔️︎

" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።

ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ " የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 /1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #የተሳሳተ ነው " ብሏል።

ቢሮው በየትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት #ሀገር_አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11/2016 ዓ/ም ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 ደግሞ የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ካላንደሩ ላይ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ #የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ ብሏል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መሰረት የ2016 ዓ/ም ትምህርት ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም ተቋም እንደሚጀምር #አስረግጦ ተናግሯል ፤ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቀው ብሏል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!