Get Mystery Box with random crypto!

' ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል ' - ት | Free Education Ethiopia ✔️︎

" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016  የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
 
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።

ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።

የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ  ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።

የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።

#MoE

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!