Get Mystery Box with random crypto!

የ 8ኛ ክፍል ውጤት ወጣ! ' ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/r | Free Education Ethiopia ✔️︎

የ 8ኛ ክፍል ውጤት ወጣ!

" ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ በመግባት ማየት ይችላሉ " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት የ2015 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን አሳውቋል።

50% እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል እንደሚዘዋወሩ የተገለፀ ሲሆን የተለያየ የአካል ጉዳት  ላለባቸው ተማሪዎች  የማለፊያ ነጥቡ 45% መሆኑ ተመላክቷል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ 73,385 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደው 70.6% ያህሉ 50 ፐርሰንትና ከዛ በላይ በማምጣት ማለፋቸው ተነግሯል።

61,840 ከሚሆኑ የቀን ተማሪዎች መካከል 50,812 የሚሆኑት ማለትም 82.16 % ያህሉ የማለፊያ ውጤቱን በማስመዝገብ ወደቀጣዩ የትምህርት እርከን ተዘዋውረዋል።

ተማሪዎች ውጤታችቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ Registration number ና first name በማስገባት መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!