Get Mystery Box with random crypto!

ተፈታኞች ከነገ ጀምሮ ይገባሉ። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማ | Free Education Ethiopia ✔️︎

ተፈታኞች ከነገ ጀምሮ ይገባሉ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከነገ ሐምሌ 16 ጀምሮ ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓዙት በተዘጋጅላቸው ተሽከርካሪዎች ነው።

ተፈታኞች ዩኒፎርማቸውን መልበስ ፤ ብርድልብስና አንሶላ ይዘው መገኝት ይጠበቅባቸዋል። 

ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ ሞባይል፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

ተማሪዎቹ ከቤታቸው ሲወጡ፦
- መታወቂያ ፣
- አድሚሽን ካርድ
- የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸውን እንዳይረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንዲያስታውሷቸው ጥሪ ቀርቧል።

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ይሰጣል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!