Get Mystery Box with random crypto!

' የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን U | Free Education Ethiopia ✔️︎

" የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ መግለጫ ልኮልናል።

ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ የነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች ሲሆኑ የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ ብቁ ሆነው የተመዘገቡት ከ48 መንግስት ተቋማት 84,627 እና ከ171 የግል ተቋማት 109,612 በድምሩ 194,239 ተማሪዎች ናቸው፡፡

የመውጫ ፈተናን ለመውስድ ከተመዘገቡት ውስጥ ከመንግስት ተቋማት 77,981 ተማሪዎች ከተመዘገቡት 92.15 ከመቶ እንደዚሁም ከግል ተቋማት 72, 203 ተማሪዎች 65.87 ከመቶ በድምሩ 150,184 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ወስደዋል፡፡

በመንግስት ተቋማት ለፈተና ከተቀመጠት ውስጥ 48,632 ተማሪዎች 62.37 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል፡፡

በተመሳሳይ ከግል ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት ውስጥ 12,422 ተማሪዎች 17.2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል፡፡

በድምሩ ለፈተና ከተቀመጡት ውስጥ 61,054 ተማሪዎች 40.65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ አስመዝገበዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መግለጫ የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን #ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ ብሏል።

(ትምህርት ሚኒስቴር የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay safe