Get Mystery Box with random crypto!

' ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረስ ክፍያ መጨመር አይቻልም ' - የአዲስ አበባ ትምህርት ስል | Free Education Ethiopia ✔️︎

" ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረስ ክፍያ መጨመር አይቻልም " - የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ሳይደረሱ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዛሬ ለግልና መንግስተዊ ላልሆኑ ት/ቤቶች ባስተላለፈው ሰርኩላር ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የ 2016 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይቻል ገልጿል።

በከተማው አንዳንድ ተቋማት የክፍያ ጭማሪ ከወላጆች ጋር በቂ ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት መሆኑን በአካል ተገኝቶ ማረጋገጡን የገለፀው ባለሥልጣኑ የክፍያ ጭማሪውን ከተማሪ ወላጅ ተወካዮችና ከባለ ሥልጣን መሰሪያ ቤቱ ጋር ውይይት በማድረግ በሚቀመጥ የጋራ አቅጣጫ ብቻ ወደ ተግባር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ትምህርት ስልጠና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

ከት/ቤት ክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ መልዕክታችሁን በcomment ላይ አድርሱን። ልጆቻሁን የምታስተምሩባቸው ት/ቤቶች ምን ያህል ጨመሩ ?

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!