Get Mystery Box with random crypto!

' የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን ' - ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከተ | Free Education Ethiopia ✔️︎

" የምንሄድበት የለም፤ መፍትሄ ይፈለግልን " - ተማሪዎች

የከፍተኛ ትምህርታቸውን ለመከታተል ከተለያዩ የፀጥታ ችግር ካለባቸው የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ተከትሎ ጭንቀት ውስጥ እንዳሉ ገልፀዋል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሰጠቱን ተከትሎ ፈተና የሚሰጥባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ማንኛውም ተማሪ እንዳይገኝ ተብሏል።

ይህ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ጭንቀት ውስጥ የከተተ ሲሆን ተማሪዎቹ መፍትሄ ይፈለግላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልና ቤተሰቦቹ በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፤ "ወደ መጡበት ቦታ መመለስ የማይችሉ ተማሪዎች ምን ሊደረጉ ነው ? ጦርነት ካለበት ቦታ የመጣን ተማሪዎች አለን ድምፃችን ተሰምቶ መፍትሄ ይፈለግልን፤ ወደ ቤታችን መሄድ አንችልም፤ መሄጃም የለንም" ብሏል።

ሌሎችም ተማሪዎች በተመሳሳይ መሄጃቸው እንደጨነቃቸው ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ብቻ 50 የፀጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች መኖራቸው ለማወቅ የቻለ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለእነዚህ መሄጃ ለጠፋቸው ተማሪዎች ምን አሰቧል በሚል ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የቅርብ ሰው ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚሁ ሰው ዩኒቨርሲቲው ለትምርህት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቦ ከግቢ ይውጡ እንደተባለና ምናልባት ከፈተና መለስ እንደሚመለሱ አስረድተዋል።

መሄጃ የሌላቸው ተማሪዎች እስከዛ የት እንዲያርፉ ታስቧል ለሚለው ጥያቄ፤ ከግቢ ወጥተው ወደየ መጡበት/ቤተሰብ ጋር ይሂዱ መባሉን ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አቅጣጫ ቢያስቀምጡ ጥሩ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ት/ት ሚኒስቴር ሚሰጠን ምላሽ ካለ እናሳውቃለን።
@Free_Education_Ethiopia