Get Mystery Box with random crypto!

#Update: የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠ | Free Education Ethiopia ✔️︎

#Update: የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀው ነበር።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ብሏል።
Via Tikvah

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!