Get Mystery Box with random crypto!

ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን | Free Education Ethiopia ✔️︎

ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና 147 ካምፓሶቻቸው ላይ ሚያዚያ 10 እና 11/2014 ዓ.ም ድንገተኛ ፍተሻ ማካሄዱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በዚህም ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶች ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ ተወስዷል፡፡

በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ መስጠቱን ባለስልጣኑ ገልጿል።

ተቋማቱ በቀጣይ የተገኝባቸው ክፍተቶች በማስተካከል በአስር የሥራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

(የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ የተወሰደባቸው 24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

#የትምህርትና_ስልጠና_ባለሥልጣን

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!