Get Mystery Box with random crypto!

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ | Free Education Ethiopia ✔️︎

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንደሚወስዱ ተገለፀ
-----------------------------------------
የትምህርት ሚኒስቴር የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተናን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም በኦንላይን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ፈተናውን በወረቀት ለመስጠት መወሰኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ( ፒ ኤች ዲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12ሺ ህ በላይ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአካባቢው የትምህርት መሰረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናቸውን በአካባቢያቸው በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚወስዱ ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተፈታኞች በአካባቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ትምህርት ቢሮዎች ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተፈታኞችን በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የማጓጓዝ ስራች እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ተፈታኞቹ ፈተናቸውን የሚወስዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም መቀሌ ፣ አክሱም ፣ አዲግራት እና ራያ የኒቨርስቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!