Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የታብሌት አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች፡- 1ኛ= ኦንላይን (Onl | Free Education Ethiopia ✔️︎

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የታብሌት አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች፡-

1ኛ= ኦንላይን (Online) ፈተና ለመውሰድ በየክፍሉ ማገኘት የሚገቡ የፈተና መሳሪያዎች በክፍል ተማሪዎች ብዛት ልክ ታብሌት ኮምፒዮተር , በየክፍሉ አንድ ላብቶኘ , ሶኬት, ቻርጀር, ዲሽ, ጀኔሬተር(መብረት) ወዘተ ናቸው፡፡

2ኛ= ተፈታኝ ተማሪዎች ለ2 ሳምንት ከ2009 ዓ,ም እስከ 2011 ዓ,ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር አቀፍ የተፈተኑትን ፈተና ጥያቄዎች በየት/ቤታቸው ተገኝተው ይለማመደሉ፡፡ ግን ታብሌት ከት/ቤት ውጭ መውሰድ አይቻልም፡፡

3ኛ= ታብሌቱ በተለያዩ አሻረዎች ማለትም በ5 ጣቶች, በፊት ገፅ በምራቅ
በጆሮና በአይን ከተማሪው ጋር ትውውቅ ያደረገ ስለሆነ ተማሪው ወደ ጎን ሲዞርና ሌላ ሠው ሲደረብ ታብሌቱ ይዘጋል፡፡ ስለዚህ ጥያቄ መስራት ስለማይቻል
በፍፁም ኩረጃን አያስተነግድም፡፡

4ኛ= ታብሌቱ የሚሠራው በዋይፋይ (Wi-Fi) በየክፍሉ በተዘረገው ሆኖ ቀጥታ አገር አቀፍ ማሰረጫ ጋር መረጃ ያስተላልፋል፡፡

5ኛ= ፈተናው አራትና በላይ ኮድ ምርጫውን ጭምር ማድረግ ይቻለል፡፡

6ኛ= ዲሽ ሲተከል በነፃ ቦታ ወይም ዛፍና ተራራ የማይገርድና ሲግናሎች በቀላሉ የሚገቡበት መሆን አለበት፡፡ በተተከለው ዲሽ ብቻ ታብሌቱ ስለሚሠራ ችግር እንዳይደርስ በአጥር አጥሮ በዘበኛ ማስጠበቅ አለበት፡፡ ዲሹ በቀጣይ ዲጂታል ቤተመፃህፍት አገልግሎት ስለሚሰጥና በቀጣይ ተማሪ ምዝገባ ከ9-12ኛ ክፍል ስለሚካሄድ የተሻሉ ተማሪዎችን ለመምረጥ ስለሚሰራ በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡

7ኛ= ታብሌቱን ለተማሪዎች የሚያሰለጠኑ ባለሙያዎች በየት/ቤቱ ይመደባሉ፡፡

8ኛ= ፈተና ለሚያስፈፅሙ መ/ራንና ለሌሎች አካለት ስለቴክኖሎጂ አጠቃቀም አጫጭር ስልጠናዎች ይሠጣሉ፡፡

9ኛ= ፈተናው በኦን ላይን (online) መሰጠቱ ወጭ ከመቀነስ አኳያ በወረቀት
ግዥ, በቀለም ግዥ, ፈተና በማጓጓዝ, በእርማት ወዘተ ከሚያወጠው ወጪ በአምስት እጥፍ ያነሰ ነው፡፡

10ኛ= የፈተና ውጤቱን ለተማሪዎች ሞራል ካልሆነ ፈተና እንደጨረሱ ማለፊያውን ውጤት ማወቅ ይቻላል፡፡ ግን በቀናት ልዩነት ውጤቱን እንዲያውቁ
ይደረጋል፡፡

#SHARE
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!