Get Mystery Box with random crypto!

#EntranceExam መልዕክት ለ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ★ኮቪድ + የውስጥ ችግር | Free Education Ethiopia ✔️︎

#EntranceExam

መልዕክት ለ 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

★ኮቪድ + የውስጥ ችግር + ለቴክኖሎጂ አዲስ መሆን እና የትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ድክመት ታክሎበት የ#2012 የኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ተስፋ አስቆራጭ ጊዜያትን እያሳለፋቹህ መሆኑ ግልጽ ነው ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ተስፋ ከመቁረጥና ከመዘናጋት ይታደጋቹህ ዘንድ አንድ ሁለት መረጃ ሹክ ልበላቹህ

የመጀመሪያው መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመፈተን አስፈላጊ የሚባለውን የቅደመ ዝግጅት ስራ በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን ምናልባት የሚቀረው ታብሌት ማከፋፈል ከዛም የፈተና ጊዜ ማሳወቅ ነው። እርግጥ ነው በተማሪው ቁጥር ልክ ታብሌቶች ወደ ሀገር ውስጥ አልገቡም ሆኖም ግን በቀጣይ ቀናት ሙሉ ለሙሉ ታብሌቶች ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ እስካሁንም ገብተው ሊሆን ይችላል { ታብሌት ሀገር ውስጥ አልገባም በሚል መዘናጋት አያስፈልግም}

ሁለተኛው መረጃ ከተፈተናቹህ በኋላ የሚኖራቹህ ጊዜ እጅግ የተጣበበ በመሆኑና ዩንቨርሲቲዎችም የ#2013 የትምህርት ዘመንን በዚሁ ዓመት ለማገባደድ ስለሚፈልጉ የሚጠብቃቹህ ጫና ሊያዘናጋቹህ አይገባም የሚል እምነት አለኝ ።

ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ክፍተቶች የነበሩበት መስሪያ ቤት መሆኑ እሙን ነው ዘንድሮም ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም ፤ የመረጃ ክፍተት የዘንድሮው ትልቁ ችግሩ ሲሆን በቀጣይ ቀናት በተለይም ከፈተናው ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ ችግሮች ሊኖሩ ይችሉም ይሆናል ።

በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ዘመቻ በመክፈት ትምህርት ሚኒስቴር ላይ ጫና ለመፍጠር መሞከር ብልህነት ነው ሆኖም ግን ታብሌት ሀገር ውስጥ አልገባም በሚል መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል ነገ ትምህርት ሚኒስትር ምን ሊላቹህ እንደሚችል አታውቁም

በድጋሚ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራቹህ ግን ለኦንላይን ፈተናው በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀውል በሰሙኑንም ታብሌቶች ሙሉ ለሙሉ ወደ ሀገር ቤት ገብተው ወዲያው የሚከፋፈሉ ይሆናል ከፈተና በኋላ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ውጤት እና ምደባ ይፋ ተደርጎ ዩንቨርሲቲዎች የጥሪ ማስታወቂያ ያወጣሉ
ATC

በጭራሽ አትዘናጉ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!