Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር❤ እና 🕑ህይወት ➕🎶

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrnahiwot — ፍቅር❤ እና 🕑ህይወት ➕🎶
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrnahiwot — ፍቅር❤ እና 🕑ህይወት ➕🎶
የሰርጥ አድራሻ: @fkrnahiwot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 675
የሰርጥ መግለጫ

💚💛♥️ፍቅር💚💛♥
💚👫እዚህ ምድር ላይ ሲኖር የሠው ልጅ ሙሉ የሚሆነው የኔ የሚለው ሰው ሲኖረው ነው💚💑
በዚህ ቻናል ላይ...የፍቅር ጥቅሶች
💔💞የፍቅር አበባሎዎች💞💔
አሪፍ አሪፍ የፍቅር ታሪክ ያገኙበታል
የፍቅር ጥያቄዎትን ማስተለፍ ከፈለጉ እናስተላልፍሎታለን ‌@nahita2 ላይ ሹክ ይበሎን
💔💘🌹
ዘፈን ግጥም ጠቃሚ ምክሮች...
ከቻልክ❤ ፍቅርን ተናገር፣ አስተምር፣ ኑር!

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-10 15:36:29
1.1K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-29 19:57:44 @fkrbsha
1.1K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 20:14:24 አንድ እንሁን


Cover by meron


ከ ህይወት ምዕራፍ
1.2K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-20 20:14:01 ብቻዬን ቆሚያለሁ


Cover by Tizta

ከ ህይወት ምዕራፍ
1.1K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 19:46:41
#Story

@LoVeS << >>
986 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 19:45:44 የቆንጆዋ ጦስ

8

ሼn
.
.
.
ከሀሳቤ ወጥቼ ቀና ስል ነየሀኒ ቀሚስ ታች ድረስ ወርዶ ቀይ ሰውነቷ በጡት ማስያዣ ብቻ ተሸፍኖ ቁማለች ውስጤን አንዳች ነገር ተሰማኝ እንደመደንገጥም አልኩ ነገር ግን አይኔን ከሰውነቷ ላይ ማንሳት አልቻልኩም ነበር የሰውነቷ ጥራት የተለየ ነው ወደኔ ፊቷን እየዞረች አንተ አልሞቀህም እንዴ አለችኝ ተመስጨ እያየሁዋት እንደነበር ሳታቅ አትቀርም መሰል ፈገግ እንደማለት አለች ብዙም አልሞቀኝም አልኳት አይኔን በግድ ገተገለጠው ሰውነቷ ላይ እያነሳሁ የፈራህ ትመስላለህ በቃ ትንሽ ነፈስ ይበልብኝ እና እመጣለሁ ፈታ እያልክ ጠብቀኝ በቃ አለችኝ መፍራቴን ከድንጋጤየ እንዳወቀችው ገብቶኛል ግን እሷ ምንም ሳይመስላት የኔ እንደዛ መሆን ምን ይባላል? ራሴን ጠየኩ ግን መልስ አልነበረኝም ትዛዟን ተቀብየ የመኝታ ቤቱን በር ወጥቸ ወደ ሳሎን የሚያስወርደውን ደረጃ ጀመርኩ ሳሎን ላይ አሁንም ሙዚቃውና ጭፈራው እንደቀጠለ ነው ሁሉም ሞቅ ብሏቸዋል መመለሴንም ቁብ ያለው አልነበረም ሀኒ እስክትመጣ የቀድሞ መቀመጫየ ላይ ሁኛ አንዴ የቤቱን እቃወች አንዴ ደሞ ወደ ሚጨፍሩት የሀኒ ጓደኞች ላይ እያመላለስኩ መታዘቤን ቀጥያለሁ በዚህ መሀል ቀደም ብሎ ለዳንስ አስነስታኝ የነበረችው ልጅ በእጇ የወይን ብርጭቆ እንደያዘች ወደኔ መጣችና ከጎኔ ተቀመጠች ካለባበሷ ውጭ ሁሉም ነገርዋ ደስ ይላል እንደዚህ አይናፍር አትመሰልኝም ነበርኮ አለችኝ እጇ ላይ ያለውን መጠጥ ወዳፏ እያደረገች ኧረ አይናፍር እንኳ አይደለሁም ግን አባባልሽ ከዚህ በፊት የምታቂኝ አስመሰለብሽ ስል መለስኩላት በአካል እንደዚህ ቀርቤ ያየሁህ ዛሬ ቢሆንም በማወቅ ደረጃ ግን ከዚህ በፊት አውቅሀለሁ ማለቴ በፌስቡክ አለችኝና አስከትላ የምፅፋቸውን ነገሮች በጣም ነው የምወድልህ እንደውም አጋጣሚውን እንዳገኛሁ ብትፈርምልኝ ደስ ይለኛል ብላ እንደመሳቅ አለች አመሰግናለሁ ግን እኔ አላወኩሽም የፌስቡክ ስምሽ ማነው ስል ጠየኳት ስሟን ሳትነግረኝ ሀኒ ከደረጃው ብቅ አለች በቃ መልክት አስቀምጥልሀለሁ ሜሴጅ ላይ ያኔ ታውቀኛለህ ብላ በፈገግታ የታጀበ መልስ ሰታኝ ከጎኔ ተነሳች ሀኒ ደረጃውን እየወረደች አይኗ እኛ ላይ ነበር ደስ ያላት አትመስልም ልጅቱም ያን የምታቅ ይመስል ሀኒ ስትመጣ ስታይ ከጎኔ መነሳቷ ይበልጥ ሌላ ነገር ይመስላል ስል አሰብኩ ጓደኞቿ በጭፈራ ተቀበሏት እና ወደመሀል አስገቧት ሀኒም እጇ ላይ ያለውን ባለትልቅ እስክሪን ስልክ የሰልፊ ፎቶ ማንሻ ዘንጉ ላይ እያስተካከለች ለፎቶ እንዲዘጋጁ ነገረቻቸው የሀኒ እህት ደሞ ባራቱም የቤቱ ማእዘን ያሉትን የጌጥ መብራቶች አንድ በአንድ አበራቻቸው እና እሷም ራሷን ለፎቶ አዘጋጀች የቀረሁት እኔ ነበርኩ ሀኒ በአይኗ ስጠቅሰኝ ስለገባኝ ተቀላቀልኳቸውና ማስታወሻነታቸው ለሀኒ ልደት የሆኑ የተለያዩ ፎቶወች ቦታ እየቀያየርን ተነሳን ። ብዙ ሳይቆይ ለዳንስ ያስነሳችኝ ልጅ ብቻ ስትቀር ቀሪወቹ እየተሰናበቱን ወጡ ሰአቴን አየሁ 12።:30 ይላል የሰአቱ መሮጥ ይገርማል ይህን እያሰብኩ መጣን ተጫወት ብለው ሦስቱም ተያይዘው ወደ ፎቅ ወጡ ወዲያው እነሱ እንደወጡ ገና ስንመጣ የግቢውን በር ከፋታልን የነበረችው ሴት ወደ ሳሎን ገብታ እቃወቹን መነሳሳት እና ማዘጋጀት ጀመረች እነሀኒም ብዙ ሳይቆዩ እንዳወጣጣቸው ተከታትለው ወደ ሳሎን ገቡ የሶስቱም ልብስ ተቀይሯል እንዳዲስ ውብ ሁነው ነው የተመለሱት የሆነ እቅድ ሳይኖር እንዳልቀረ ገመትኩ ሌላ ልደት አለባችሁ እንዴ ስል እየቀለድኩ ጠየኳቸው ባንድ ሳቁና ሀኒ ወደኔ መጥታ ፊትለፊቴ ተቀመጠችና አንድ ነገር ልጠይቅህ ነው እምቢ ብለህ እንደማታስከፋኝ ቃል ግባልኝ አለችኝ አይን አይኔን እያየች ምንድነው ጠይቂኝ የምችለው ከሆነ መቸም እምቢ ልልሽ አልችልም የኔ ምላሽ ነበር ትንሽ ውጭ ማምሸት ፈልገን ነበር እና አብረህ እኛጋ እንድትሆን ፈልጌ ነበር አለችኝ እየተቅለሰለሰች ማምሸት የሚለው እስኪ ይብራራልኝ ስል መለስኩላት እራት ልጋብዛችሁ ፈልጋለሁ በዛውም የምንሄድበት አለን እዛ ፈታ ብለን እንመለሳለን ፕሊስ በቃ እሽ በለኝ ስትል እነሱም ተከትለው ልደትዋ ስለሆነ ደስ ይበላት በቃ እሺ በላት ሲሉ የሷን ጥያቄ በነሱ ሽንገላ ደረቡት ቤት እህቴ እንደምጠብቀኝ እና ማምሸት እንደማልችል ነገርኳቸው ሀኒ ካፌ ቀበል አድርጋ እሽ ቤት አብረን እንሂድና እኔ ላስፈቅዳት አለችኝ ሀኒን እንዲከፋት ስለማልፈልግ ብቻ በሀሳቧ ተስማማሁ ቤት ድረስ ባንሄድም ችግር የለውም ደውየ እነግራታለሁ ስል ሀኒ በደስታ ጥምጥም አለችብኝ እኔም ለህቴ ለመደወል ስልኬን አወጣሁና ወደ ውጭ ወጣሁ ሁለት ግዜ እንደጠራ ስልኩ ተነሳ ሰላምታ ካቀረብኩ ቡሀላ ላመሽ እንደምችልና ከዘገየሁ እንዳትጨነቅ ነገርኳት እንደዛ ዘንጠህ ስትወጣ እንደማትመለስ እኮ አውቄ ነበር ለማንኛውም ራስህን ጠብቅ ብላኝ ተሰነባብተን ስልኩን ዘግቼ ወደ ውስጥ ተመለስኩ በመቀጠልም የተከፈተውን ሙዚቃ ዘግቼ ላፕቶፔን አጠፋፍቸ ከጨረስኩ ቡሀላ ተያይዘን ግቢውን ለቀን ወጣን ምሽቱ በጣም ደስ የሚል እና ቀለል ያለ ንፋስ ያዘለ ነበር በሶስት ቆንጆዎች ታጅቤ ቀጥታ ያመራነው ከተማው ውስጥ ወዳለ ስመ ጥር ሆቴል ነበር እዛ እንደገባን ሁላችን እንደየምርጫችን ምግብ አዘዝን ሀኒ ከምግቡ ጋር አብሮ ዋይን እንዲመጣ አዘዘች ካፍታ ቆይታ በዃላ ምግቡና መጠጡ እኩል መጡና በሳቅ እና በጨዋታ የታጀበ ሀሪፍ ግዜ ማሰለፍ ጀመርን እኔም ከነሱ ጋር ተመሳሰልኩ ሌላ ወይን ተጨመረና ጨዋታው ደራ አሁን ሁላችንም ሀሪፍ ሙድ ውስጥ ገብተናል በተለይ እነሱ ቤትም እየጠጡ ስለነበር ያሁኑ ሲጨመር የለለ ድምቅ እንደማለት ብለዋል የተለያየ የወሬ ርእስ እየተነሳ ሳቅ እና ጨዋታው የተለየ መልክ ይዟል በዙሪያችን ለራት የተቀመጡ ሰወች ሳይቀሩ ትኩረታቸው እኛ ላይ ነበር በዚ መሀል ሀኒ ፊቴን ልታጠብ ብላ ወደ እጅ መታጠቢያው አመራች ታጥባ መጥታ ቁጭ እንዳለች ስልኬ ላይ ሜሴጅ እንደገባ ኪሴ ውስጥ ሲነዝረኝ ተሰማኝ አወጣሁና አየሁት የሀኒ ቴክስት ነበር " እንጥፋቸው " የሚል ነበር መልክቱ ቀና ብየ አየሁዋት እሷም አየችኝ እና ሳቀች ከዛም ለመልክቷ ምላሽ ወዴት ብየ? መለስኩላት የሀኒ እህት እና ጓደኛዋ ምን እንደሚያወሩ ባይሰማኝም በጣም ይሳሳቃሉ ሌላ መልክት ስልኬ ላይ ገባ ከፈትኩት እኔ ነኝ የምወስድህ ደሞ የምነግርህም ነገሮች አሉ ይላል መልክቱ ሰአቴን አየሁ አራት ሊሆን ነው መውጣት እንዳለብን አሰብኩ ግን ወጥቸስ ወዴት ብየ ራሴን ጠየኩ በዚ ሰአት በዚ ሁኔታ ሁኜ ወደ ቤት ለመሄድ የማይቻል ነው የግድ ደሞ እነሱን ቤት ማስገባት አለብኝ ለሀኒ መሄድ እንዳለብን ነገርኳት ስልኳን አውጥታ አየችና ወደነሱ ዙራ የሆነ ነገር አወራቻቸው ምን እንደተባባሉ ግን መስማት አልቻልኩም ሁለቱም ቀና ብለው አዩኝና መልሰው የሆነ ነገር አውሩ ከዛም ሀኒ እነሱ መቆየት እንደሚፈልጉና በዛ ላይ ደሞ ከጓደኛየ ቤት ነው ማደር ያሰቡት እኛ እንውጣ በቃ አለችኝ እና ተሰናብተናቸው ሆቴሉን ለቀን ወጣን አሁን ቆንጆ ሀሳብ መጣልኝ እሷን ቤቷ አድርሻት ጎደኛየ ጋር ደውየለት እሱ ጋር ማደር ያ ካልሆነ ደሞ አልጋ መያዝ ይህን ሀሳቤን ለሀኒ ነገርኳት ደስ አላላትም ከፊትዋ ያስታውቃል ቆይ በመጥፋቱ አልተስማማህም እንዴ አለችኝ ኮስተር ብላ እሺ ወዴት ነው የምንጠፋው ስል የቀድሞ ጥያቄየን ደገምኩላት እሱን እኔ አሳይሀለሁ አንተ ብቻ በሀሳቡ ተስማማ ደሞ የምነገርህ ነገር አለኝ ብየህ የለንዴ የሷ መልስ ነበር የሚሆነው ለማየት ተስማማሁ ዝም ብለህ እሽ ማለት ነው ያንተ ስራ ወዴት እና እንዴት የማለት መብትህን ለዛ
913 views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 12:58:49 ት ተናግራ የቅንጥ ሩጫ እየሮጠች ሳሎኑን ለቃ ወጣች ብዙም ሳይቆይ
ሀኒ ቀይ ቀሚስ ከቆንጆ ጫማጋር ተጫምታ ብቅ አለች
በጣም አምሮባት ነበር ሀኒ ወደ ሳሏን ስትገባ ሶፋው ላይ ተቀምጠው የነበሩት ልጆች አንድ ላይ ተነስተው እያቀፉዋት የሞቀ ሰላምታ ተለዋወጡ ካፍታ ቆይታ ቡሀላ የቤቱ ድባብ ሙሉ ለሙሉ ተቀየረ ማሂም ቀድመው ከገቡት ሴቶች ያልተናነሰ አለባበስ ለብሳ ብቅ አለች ከዛም በሰራተኛዋ እና በማሂ እገዛ ምሳ ቀረበና መበላት ተጀመረ አንዳንዶቹ አንበላም
ስላሉ የራሳቸውን ወሬ አድርተዋል እኔ ከሚበሉት ወገን
ሰለነበርኩ ሀኒ ምን ይምጣ ምን ይጨመር እያለች
ተንከባከበችኝ ማሂም እንደዛው እንዲህ እንዲህ እያለ ምሳው ተበልቶ ተጨረሰ መሂ ኬኩን ሸፍኖት የነበረውን መሸፈኛ አነሳችውና ከኬኩ ፊት ላይ ባለ 21 ቁጥር ሻማ አቆመች ትናንሾቹን ሻማወች ደሞ እያነሳች በኬኩ ዙሪያ ሸጎጠቻቸው ቅድም ከገቡት ልጆች ውጭ አንድ ወንድ እና ሴት ተጨምረዋል ሀኒ ከጠረንቤዛው ፈት ቆመችና ንግግር ማድረግ ጀመረች ,,, ያው ዛሬ ታቃላቹ ዛሬ ልደቴ እንደሆነ ወደዚህ አለም ከመጣሁ ዛሬ ሀያ አንድ አመት ሞላኝ ሶ ዛሬ ለኔ ልዪ ቀን ነው አለች ስትናገር በመሀል በመሀል ሳቋ ይመጣል ቀጠለች እናንተም በዚህ ቀን ልደቴን ለማክበር
ከኔ ጋር ስለተገኛችሁ ከልቤ አመሰግናለሁ እወዳችሗለሁ አለች ተጨበጨበላት ሴቶቹም ባንድ ላይ ጮሁ ሀኒ የልደት መዝሙር እየተዘመረላት በ ሄኖክ ልዩ የሚል ሙዘቃ ታጂባ ሻማ የመለኮስ እና የማጥፋት እንዲሁም ኬክ የመቁረስ ሰርአቱን አከናወነች ከዚህ ቡሀላ ነበር ትርኢቱ የጀመረው
የመጠጥ አይነቶች ተከፈቱና ወደ አንድ እቃ ተቀላቀሉ በትልቁ ስፒከር የባህር ማዶ መዚቃ ተለቀቀ ብዙወቹ እርስ በርስ ይተዋወቁ ስለነበር ቤቱ በጨዋታ ድምቅ አለ ከኔ ውጭ ሁሉም የሚጠጣ ይዘዋል ሀኒ እንድጠጣ ብዙ ልታሳምነኝ ብትሞክርም እኔ ግን እምቢታ ነበር መልሴ ከቆይታ ቡሀላ
ጠረንቤዛው ተነሳና ሶፋወቹ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው የሳሎኑ ወለል በከፊል ለዳንስ ክፍት ሆነ ሁሉም ቁመው የየራሳቸውን እንቅስቃሴ መወዛወዝ ጀምረዋል ሀኒም እነሱ መሀል ሁና ሄድ መለስ ደሞ ጎርደድ መለስ ትላለች ማሂ ሞቅ ሳይላት አይቀርም በየ መሀሉ ወደኔ እየመጣች ዋት ዘ ሄል ኢዝ ሮንግ ዊዝ ዩ come on and join us ትለኛለች ወሬወቿ ከማርኛ ይልቅ እንግሊዘኛ ይበዛቸዋል እሺ እቀላቀላለሁ አልኳትና አየር ለመቀበል ወደበረንዳው ወጣ አልኩ ሀኒ ተከትላኝ ነበር ደበረህ እንዴ አለችኝ ኧረ አልደበረኝም ስለሞቀኝ አየር ለመቀበል ነው የወጣሁት አልኩ እኔን ግን እያጨናነከኝ ነው የደበረህ እየመሰለኝ ቆይ እሽ
ዋይን ጠጥተህ አታቅም አለችኝ ጠጥቸ አቃለሁ አልኳት ለ ግራጁዌሽን የክላስ ተማሪወች ያዘጋጁት ዝግጅት ላይ ብዙ ጠጥቸ በዜና ካልጨፈርኩ ቆርኪ ላይ ገላየን ካልታጠብኩ ብየ አስቸግሬ እንደማቅ ትዝ አለኝ እሽ እሱን እንኳ ልክፈትልህ ትንሽ ፈታ ያደርግሀል ለኔ ስትል አለች እና መልሴን ሳጠብቅ
ጉንጨን ሳም አደረገችኝ እና እጄን ይዛኝ ወደውስጥ ገባች እና ቦታየ ድረስ ወይን አመጣችልኝ በልደትዋ ቀን ላስከፋት አልፈለኩም ነበር ምክንያቱም እወዳታለሁ እንደምንምም እራሴን ፈታ ለማድረግ ሞከርኩ ፋላሻቸው ላይ ያለው ሙዚቃ ብዙም አልተመቻቸውም በዛ ላይ በየመሀሉ የማይፈልጉት አይነት ሙዚቃ እየገባ ሙዳቸውን እያበላሸው ስለነበር ሀኒ እኔ
ያመጣሁትን ሙዚቃ እንዳጫውትላቸው ጠየቀችኝ ላፕቶፔን አወጣሁና ይመቻቸዋል ብየ ያሰብኩትን ሙዚቃወች መርጨ አከታትየ ከፈትኩላቸው በጣም ወደዱት ጭፈራውና ዳንሱ ደራ እኔም የቀረበልኝን ወይን አጋመስኩት ታዲያ በዚ መሀል ነበር ከሴቶቹ አንዱዋ ወዳለሁበት ቦታ ዳንስ በታከለበት
አረማመድ መጣችና እጄን ይዛ አስነሳችኝ ለማንገራገር ሞክሬ ነበር ግን አልተሳካልኝም ነበር ሁሉም ሲንጫጩብኝ ተመካክረው እንደሆነ ገባኝ ወደ መሀል ሄድንና መደነስ ስንጀምር የሀኒ አይን ከኛ ላይ አልነጠል አለ ሌሎቹ የራሳቸውን ጭፈራ እየጨፈሩ ነው ከኔ ጋር የምጨፍረው ልጅ በጣም ነው የምደንሰው ጭፈራዋ ወዲያው ወዲያው ይቀያየራል እኔም የሱዋን እየተከተልኩ መዳነስ ቀጥያለሁ ወዲያው ሙዚቃው ወደ አፍሪካ ሙዚቃ ተቀየረ መሀል ላይ
የነበርነው ደሞ እኔና ለዳንስ ያስነሳችኝ ሴት ነበረች
ሁላቸውም እኛን ከበው ውድድር በሚመስል ትርኢት
መመልከት ጀምረዋል ልጅቱ በጣም አይን ያወጣ ዳንስ
መደነስ ጀመረች ጭራሽ ሰውነትዋን ከኔ ሰውነት ጋር
አዋደደችው በዚህ መሀል ሀኒን ቀና ብየ አየሁዋት ፊትዋ ልውጥውጥ ብሏል ቀስ ብየ ከልጅቱ ተላቀኩና ወደነበርኩበት ቦታ ተመልሸ ቁጭ አልኩ ሀኒም ከቆይታ ቡሀላ መጣችና እንደምትፈልገኝ ነገራኝ ቀድማ ከሳሎን ወጣች እኔም ብዙ ሳልቆይ ተከትያት ወጣሁ ኮሪደሩ ጋር ቁማለች እንወጣሁ እጀን ያዘችኝ እና ደረጃውን መውጣት ጀመረች አረማመድዋ
ትክክል አደለም ሳትሰክር አትቀርም ደረጃውን ወተን
እንደጨረስን ፊትለፊታችን የነበረውን ክፍል ከፈተችውና ስባ አስገባችኝ መኝታ ክፍሏ እንደሆነ ክላሱ ውስጥ ያሉትን እቃወች እንዳየሁ ነበር ያወኩት በተኮላተፈ አማርኛ እ ን ዴ ት እ ን ደ ሞ ቀ ኝ ዩ ሀቭ ኖ አይዲያ አለች የቀሚስዋን የሁዋላ ዚፕ በግድ ለማውለቅ እየተንገዳገደች ሀኒ እኔ እታች
ልጠብቅሽ አንች ቀይረሽ ነይ አልኳት ቀና ብላ አየችኝ እና ምነው ፈራህ እንዴ አይዞህ ማንም እኳ አይመጣ ይሄ የኔ ክላስ ነው አለችኝ አሁንም እየተኮላተፈች ነው ቤተሰቦችሽስ አልኳት ለመጀመሪያ ግዜ ነበር አፍ አውጥቸ ነበር ስለቤተሰቦቹዋ ስጠይቃት ባክህ እነሱ እዚህ አይኖሩም አለችኝ ማለት እና የት ነው ያሉት አልኳት አባቴ ደብረዘይት ነው እናት እና ወንድሜ ደሞ ካናዳ ነው የሚኖሩት ዩ ኖ ካናዳ ብላ በንግሊዘኛ ደገመችው አሁን ሀሳቤ ሁሉ ተበታተነብኝ ደብዳቤው እና የሀኒ ነገር ከበፊቱ ጥርጥሬ ብሶ ፍፁም ልዩነት ፈጠረብኝ አንድ ሚስኪን እናት ብቻ እንዳላት
እና የምትኖረውም እናትዋ ጋር እንደነበር ነበር የማቀው አሁን ደሞ ታሪኩ ሁሉ ሌላ ሆነብኝ በቆምኩበት ከራሴ ጋር ውዝግብ ፈጥሬ ነገሮችን ወደሁዋላ ተመልሼ ማሰብ ጀመርኩ ድንገት ከሀሳቤ ወጥቼ ቀና ስል የሀኒ ቀይ ቀሚስ ወገብዋ ድረስ ወርዶ ቀይ ሰውነቷ በጡት ማስያዣ ብቻ ተሸፍኗ ቁማለች ••••••

ይቀጥላል
1.1K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-19 12:58:06 የቆንጆዋ ጦስ

ክፍል ⓻

ሼን
.
.
.
ፀጉሬን ተሰርቸ ጨርሸ ወደ ካፌው ወረድኩ ካፌው እንደደረስኩ ሀኒ ወንበሯ ላይ እንደተቀመጠች ናት ቀጥታ ወደሷ ወንበር አመራሁ አጠገብዋ ስደርስ በድንጋጤ ድርቅ ብየ ቆምኩ የላፕቶፑ ባግ ተከፍቶ ዲያሪየን ሀኒ እጅ ላይ አየሁት ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ በቆምኩበት ብዙ አሰብኩ ቀጥ ብየ ልወጣም ፈለኩ ግን ወጥቸስ?? በቃ የሆነውን
በፀጋ ለመቀበል ወሰንኩ አንብባውም ከሆነ የፃፍኩት
አንዳችም መጥፎ ነገር የለም ስላሳለፍነው ግዜያቶች እና ስለሷ ካለኝ ስሜት ውጭ ነገር ግን በዚህ አጋጣሚ
ባታውቀው ደስ ይለኛል ,,ወደፊት ተጠጋሁና ጓኗ ያለውን
ወንበር ስቤ ቁጭ አልኩ ድንጋጤየ እንዳያስታውቅብኝ
እየጣርኩ ጨረስክ እንዴ አለች የምቆይ ነበር የመሰላት የኛ እኮ እንደናንተ ብዙ አያቆይም አልኳትና አስከትየ ሙዚቃወቹን ቼክ አደረግሻቸው እንዴ ስል ጠየኳት አሁንም አይኔ ዲያሪው ላይ ነው ላያቸው ፈልጌ ነበር ላፕቶፑን ያወጣሁት ነገር ግን ፓስዋርድ ስለጠየቀኝ መክፈት አልቻልኩም ነበር እሱን ትቸ ግጥሞችህን ማንበብ ጀመርኩ አሁን የተወሰነ ተረጋጋሁ ለካ
የዲያሪየ የመጀመሪያወቹ አስር አስራምስት ገፆች ላይ
በየግዜው የምፅፋቸው ግጥሞች ነበሩ የሰፈሩት
አላነበበችውም በቃ አልኩ ለራሴ የራስህ ግጥሞች ናቸው ግን አለችኝ የራሴ ያልሆነ ግጥም ላይ ስሜን እና ፊርማየን አኑሬ አላቅም ሁሉም የራሴ ግጥሞች ናቸው ስል መለስኩላት በጣም ጎበዝ ነክ አለችኝ በጣም ደስ ያለኝ ደሞ ሆቢያችን መመሳሰሉ ነው እኔም እንዳንተ ጎበዝ ባልሆንም መፃፍ በጣም ነው የምወደው በተለይ ደሞ አጫጭር ልብወለዶች
መጫጫር የሚያዝናናኝ ነገር ነው አለችኝ በጣም ደስ ይላል አንች ልጅ ግን ብዙ ነገራችን እየተመሳሰለ ነው እጣ ፈንታየ ሳትሆኝ አትቀርም አልኳትና በፈገግታ ቀና ብየ አየሗት ማን ያቃል አለች እየሳቀች እንደውም ካረሳሁት የሆነ ቀን ግጥም የምጫጭርበትን ደብተሬን እጋብዝሀለሁ አሁን እንሂድ ሰአቱ እየሄደ ነው አለች ያወጣችውን ዲያሪ ማስታወሻ ባጉ ውስጥ
እያስገባች በጣም ደስ ይለኛል እኔ ራሴ አስታውስሻለሁ
አልኳትና አስተናጋጅዋን በምልክት ጠርቼ ሂሳብ ሰጠሗት እና ከካፌው ወጣን ከካፌው ስንወጣ ሰባት ሰአት ሁኖ ነበር ሀኒን ወዴት እንደምትወስጅኝ አስካሁን አልነገርሽኝም አልኳት አልናገርም ዛሬ ላግትህ አስቤ ነው አለችኝ ታክሲ እንደማስቆም በእጇ ምልክት እያሳየች ልብሴን ላምጣና በናትሽ እስከመጨረሻው አግችኝ አልኳት ቀልዷን በቀልድ መመለሴ ስለገባት ቆንጆ አልጠብስም ብለህ የለንዴ ብላ ቀና
ብላ አየችኝ ኧረ ባክሽ ሀሳቡን የማይቀይረው አስክሬን ብቻ ነው አልኳት ሳቀችና እሽ በቃ ፀባይህን አይተን መልሱን በማስታወቂያ እናሳውቅሀለን አለችኝ በዚህ መሀል አንድ ያልሞላች ታክሲ አገኛንና ሀኒ ወደምታቀው እኔ ደሞ ወዳልተነገረኝ እና ወደማላቀው ቦታ ለመሄድ ተያይዘን ታክሲዋ ውስጥ ገባን ታክሲዋ ውስጥ ከገባን ቡሀላ ለምን እና ወደየት እንደምትወስደኝ ብዙ ነገር ገመትኩ ነገር ግን
አንዱም አላረካኝ ጉዳዩን ለነገሩ ባለቤት ትቸ ዝም ብሎ
መሄድን ምርጫየ አደረኩ ከተወሰኑ ደቂቃወች ቡሀላ
ፌርማታውን ጨርሰን ከታክሲዋ ወርደን የግር መንገድ ጀመርን ጎዳናው ደሞ ሁሌም ሀኒን ወደ ቤት የምሸኝባት መነገድ ነበር ቤትሽ ነው እንዴ የምትወስጅኝ አልኳት ከዚህ በላይ ዝም
ማለት አልቻልኩም እንዴት አወክ አለችኝ እጇላይ ያለውን ስልክ እየነካካች ቤትሽ ስትሄጅ ሁሌም የምሸኝሽ በዚህ መንገድ አይደል ስል መለስኩላት በቃ ዝም ብለህ ተከተለኝ ደርሰሀል አለችኝና ትንሽ እንደሄድን ወደ ግራ የሚወስደውን
መንገድ ተከተለች እና ወደውስጥ ገባን ከዛም ፊትለፊታችን ወዳለ ቀይ ትልቅ የግቢ በር ተጠጋችና በጅዋ ይዛው የነበረውን አቃ ቀስ አድርጋ መሬት ላይ አሳረፈችና ለግቢው በር መደገፊያ ተብሎ የቆመው ግንብ ላይ የተለጠፈውን የመጥሪያ ደውል ተጫነችው ይሄ ሁሉ ሲሆን ፈገግ እያለች ዙራ ከማየት ውጭ ምንም አላወራችኝም እኔም ግራ እንደገባኝ ቆሚያለሁ ከውስጥ ወደግቢው በር የሚመጣ
የግር ኮቴ ይሰማኛል ወዲያው እድሜዋ ሰላሳወቹ መጀመሪያ አከባቢ የምትሆን የማድቤት (የኪችን) ሽርጥ ወገቡዋ ላይ ያበተች የቀይዳማ ሴት በሩን ከፈተችው እና ሀኒ እጅ ላይ የነበረውን እቃ ተቀብላ ወደመጣችበት አቅጣጫ ተመለሰች ሀኒ ዞራ አየችኝ የቆምኩበት ቦታ ላይ አልተንቀሳቀስኩም ና
እንጅ ግባ ምን ሁነህ ነው አለችኝ አጄን በእጇ ይዛ ወደ
ውስጥ እየሳበችኝ ፍራቴ ቢጨምርም ምርጫ ስላልነበረኝ ተከተልኳት የግቢው እይታ በጣም ደስ የሚል ነው በግቢው ዙሪያ በረድፍ የተቀመጡት የተለያዩ የአበባ ተክሎች እኩል
ተከርክመው አረንጓዴ መሬት የ ፈጠሩት ሳሮች ጋር ተዳምረው ግቢው ላይ የተለየ ውበት ሰተውታል የአጥሩን ጥግ ጥግ ይዘው እንደዘበኛ የቆሙት ዘንባባወች በጣም በትኩረትና እንክብካቤ የተያዙ እንደሆኑ ያስታውቃሉ ወደ ቤቱ የሚወስደው መንገድ በሳሮቹ መሀል ተከፍሎ በባለ ቀለም
ሴራሚክ ተረጥርጧል ግቢው ውስጥ አንዳች የወደቀ ብጣሽ ወረቀት እንኳ አይታይም ደረጃውን ጨርሰን በሩ ጋር ስንደርስ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለም እሽ እንዳትፈራ እንዳትጨናነቅ አለችኝ አሽ አልኳት ግን ፈርቸ ነበር ኮሪደሩን ይዘን ወደውስጥ
ስንገባ ሀኒ ማሂ ብላ ተጣራች ወዲያው አንዲት ቀጭን ረዘም ያለች በመልክ ሀኒን የምትመስል ልጅ ከፊታችን ካለው ክፍል ብቅ አለች እና ወደኛ እየ መጣች አይ ገስ ሂ ኢዝ ዛት ፈኒ ቦይ አይደል አለቻትና ወደኔ አየች
እንግሊዘኛዋ ደስ ይላል ሀኒ ስለኔ እንዳወራቻት አወኩ
ወዲያው ሀኒ እሱ ነው የነገርኩሽ ጓደኛየ ተዋወቂው አለቻትና ወደኔ ዙራ እህቴ ናት አለችኝ እጀን ዘረጋሁና ስሜን ሰጠሗት እሷም እጀን እንደያዘች ማሂ አለችና አስከትላ nice to meet you አለችኝ እኔም ስላገኛሁሽ በጣም ደስ ብሎኛል አልኳት
በአማርኛ ያን ያክል ግዜ ከሀኒ ጋር ስናሳልፍ ስለቤተሰቡዋ አንስቸባት አላቅም ምክንያቱም ፖስታው ውስጥ ያገኛሁት ወረቀት ላይ ስለቤተስብዋ ያነበብኩት ነገር ልብ ስለሚነካ
ነገር ስለሆነ ያን ባስታውሳት ስሜትዋ ይጎዳል ብየ ስለማስብ ነበር, , ከትውውቁ ቡሀላ ቀጥታ ወደ ሳሎን ነበር የወሰደችን ሳሎኑ በዲምላይት እና በተለያዩ የግድግዳ መብራቶች እብድ ብሏል ውስጡ ያሉት እቃወች በሙሉ የቅንጦት እቃወች
ናቸው የሳሎኑን ብዙ ቦታ የያዘው ደሞ ቤቱ ውስጥ ያለው ዘመናዊ ሶፋ ነው በሶፋው መሀል አንድ ባለመስታወት ትልቅ ጠረንቤዛ ተቀምጧል ጠረንቤዛው ላይ ወይንን ጨምሮ ከዚህ በፊት አይቻቸው የማላቃቸው አይነት መጠጦች ተደርድረዋል
የልደት በአል ላይ መገኛት ያለባቸው ነገሮች በሙሉ
ጠረንቤዛው ላይ ታድመዋል ርችቶቸ ከለር ስፕሬይ የልደት ኮፊታወች መሀል ላይ ደሞ ማሸጊያው ያልተፈታ ኬክ ይታየኛል ልደት እንዳለ ገባኝ ግን የማን እንደሆነ አላወኩም የተሰጠኝ ቦታ ለይ ተቀመጥኩ እና የሚሆነውን መጠበቅ ያዝኩ ሀኒ ከህትዋ ጋር ሌላኛው ክፍል ናቸው ሰአቴን አየሁ 8:05 ይላል ሀኒ መጣሁ ልብስ ልቀይር ተጨወት አለችኝ እና
ተመልሳ ሄደች በዚህ መሀል ከዚህ በፊት በመልክ እንኳ
አይቻቸው የማላቃቸው ሶስት ሴቶች እና ሁለት ወንዶች በማሂ መሪነት ወደሳሎን የገቡት ሴቶቹ ለእርቃን አሩብጉዳይ የሚባለውን አይነት አለባበስ ነው የለበሱት ገና እንደገቡ ሽቷቸው ቤቱን ቀየረው ወንዶቹ እርጋታ የሚታይባቸው አይነት ናቸው እኔ ከተቀመጥኩበት ሶፋ ትይዩ ተቀመጡ እና ፈታ ብለው የደራ ወሬ ጀመሩ ከመሀከላቸው አንዷ ሀኒስ አልጨረሰችም እንዴ ብላ ማሂን ጠየቀቻት መጣች ልብስ እየቀየረች ነው ብላ እሷም መልበስ እንዳለባ
834 views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ