Get Mystery Box with random crypto!

💃እኔ መፃፍ ብችል✍

የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrlene — 💃እኔ መፃፍ ብችል✍
የቴሌግራም ቻናል አርማ fkrlene — 💃እኔ መፃፍ ብችል✍
የሰርጥ አድራሻ: @fkrlene
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 399
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የኔ ቻናል ነው
🌎አለም ውድ ነገር ስትሰጠን መኖር እጀምራለን 😍ፍቅር_🙏እምነት_🤝ይቅርታ እኔ እናንተ የምኖርባት ውብ አለም የነዚህ ግዛት ነች 👈ይህንን ለማሳየት ደግሞ🤔 ጥበብ ትልቋ መልስናት👏😍እኔ መፃፍ ብችል ኖሮ☺
ለሀሳብ ለአስተያየት 👉 @yeAbukaye

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-30 23:14:25 #አዳዴ ዝምታ መልስ ሆኖ ይገኝና ዝም እላለው
185 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, 20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 23:03:10 Channel photo updated
20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 22:43:45 #እንስት የሆንኩ እደው

#በስነ ፍጥረቱ እግዜር ጥበቡን ሲሰራው
በአዳም ጀምሮ ሰውን መስሎ ሰራው
በቀናት ቆይታ ብቸኝነቱን ሊሽሪለት
ከግራው አጥት ወስዶ ሄዋንን ሰራለት
ሙሉ አረገችው ህይወቱ ታደሰ አበራ
ፍቅር ልጆች ቤተሰብ ተባርኮ አፈራ

#ይህንን የሰማው እኔ ተፈጥሬ ስመጣ
በሀሳቤ ማዕበል ደጋግሞ የሚመጣ
ሁሉም አዳም ሴዋኑን ካላገኘ የሚደማ
አልያ የሚያመው ጎኑን ሁሌ እየደማ
እልና በሀሳቤ ጀልባ ተሳፍሬ እየተጓዝኩኝ
አጥንት መሆኔን ደጋግሜ ለራሴ እየነገርኩኝ

#ቦታው የጎደለ የታመመውን ስፈልግ
ህይወት ለኔ ሰታው ፍቅርን ከኔ ሲፈልግ
ለማገኘው አዳም ግጣም ለመሆን
ወደ እርሱ ህይወት ገብቼ ሀሴት ልሆን
ይህን እያሰብኩኝ ባገኘዋቸው ሁሉ
ግጣም መሆኔ ቀርቶ ከጎኔ ጋር እየተጣሉ
ትዕቢቱን ሳላገኝ እውነታውን ሳላየው
በዚህ አይነት የዕድሜዬን ግማሽ ኖሬአለው

#በህይወት ጥሞና በዕድሜም ትምህርት
የገባኝ እውነታ ህይወቴን ፍፁም ቀይሮት
ለካስ የግራ አጥንት መባሌ የፍጥረት ሂደቱ
ከስጋ ከደም ከሱ ጥበቡ ተዋህጄ በውጤቱ
እንስት ሆኛለው የተከበርኩኝ ፍጥረት
በእናቱ በማርያም አምሳል የሰየማት

#እንስት የሆንኩ እደው ፈላጊው ብዙነው
በጥበቤ በብልሀቴ በበረከቱ የምቸረው
እንስት የሆንኩ እደው ተፈላጊ ነኝ
ከውድ እቁ ፍጥረት በላይ ያደረገኝ
እንስት የሆንኩ እደው
የድንግሏ መሬት የዕምነቷ ምድር
በኔ የመሰሏት ኢትዮጲያንም ሀገር
እናም አጥንት መሆኔን አስቤ የተጎዳውት
ዛሬ እንስት ሆኜ አዳሜን ከቤቴ አገኘውት

#ልደት የአብካዬ ሴት

https://t.me/fkrlene
738 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 22:43:44
526 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, 19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 09:53:37
#ስንቶቹ ይሉሻል

ፈገግታሽ ምግቤ መኖሬን ማሳያዬ
ስስት አስተያየትሽ ልቤን ማቅለጫዬ
ማርዬ የኔ ስጦታ የእግዜሬ ድርሻ
ያለፈው አስቀያሚ ህይወቴ ማስረሻ

#እወድሻለው ስልሽ ልብሽ አይደሰት
ማፍቀሬን ለመግለፅ ላንቺው ስለፋበት
በሚኖረኝ ህይወት በሱም አትውደጂኝ
እልፍ አዕላፍ አዳም ነው አንቺን የሚልብኝ

#ከባልጀሮችሽ ከጎረቤት ከሀገር
ከሁሉም የሚጎርፈው የመደረቅ ባህር
በየቱም አስገርሞሽ ከምትሰሚያቸው
ካዳቸውም አታጠቃልኝ የኔንስ ብርቱነው

#እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ ምስልሽ ስታየኝ
ሞላሊዛ የአለም ውቦችም አይታወሱኝ
ብቻ ምን አለፋሽ ልክ እደሰከረ ሰው
የሆድን ምስጢራት ብቅል እደሚያወጣው
አቦ እደ ሀዘነ የሚወደውን አቶ ሆዱ እደሚላወስ
ይሄነው ብሎኳን ስሜቱን በቃላት እደማይመልስ
ልክ እደዛ ነው የኔ ልብ አንቺን ስያስብ

#ብዙም አይግረምሽ በዚም አትውደጂኝ
ስሜቴን በግጥም ገልጬ ብትደሰቺብኝ
አብረሽው ያነበቡት ታድለሽ ቢሉሽም
እዳትደሰቺ እኔን እዳትወጂኝ ይሄ አይበቃሽም
ይሄንን ቃላት አሁን ያልኩሽ ሁሉ
ስቶቹ ይሉሻል ብለው የሚልሽም ስላሉ

#እኔን ፈልገው ፍቅሬን ለጠየቁሽ
ለይታውቂያቸው በስጦታ ብቻ ለተመቸሽ
ልቤን እና አይኔን ስጪልኝ አደራ
ሁሌ እደዳዊት አንቺን ብቻ ሲጣራ
በመልክቴ ጥሬ አንቺን ሲያገኙ ያኔ ነው
ስቶች ከሚሉሽን የኔ በልጦ የሚገኘው
ከቃሎቼ በላይ ማረጋገጫዬ ልቤ ይሁንልኝ
የመኖሬ ምልክት እግዜሩ በሰጠኝ

#ልደት የአብካዬ ------- @yeAbukaye
https://t.me/fkrlene
543 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, edited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 09:12:33
#በህይወታችን ለምናደርጋቸው ሁሉ ነገሮች በማስተዋል የተሞሉ ካልሆኑ ዋጋ ማስከፈላቸውን መቋቋም አንችል ይሆናል
@fkrlene
1.5K viewsአዶኒስ የአቡካዬ, edited  06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 14:05:27 #ተንጠልጥዬ ቀረው

ያንተማ ልብ ወትሮንም እዲህ ነው
አንግሶ አስውቦ ኦናነው የሚያስቀረው
በመሀላ አስሮ በቃልኪዳኑ ትልቅነት
ልቡ የማይፈራ ቃሉን ሲማር አድጎት
ያንተማ ልብ ወትሮም እዲህ ነው
ለነገሩ ክህደት አንጠልጥሎ ማስቀረት
አዳም ያስተማረህ ጉሮሮ ላይ ማስቀረት

በፍቅርህ ተጎድቼ ላንተ ፍቅር ብዙ ሞቼ
አትድረስብኝ የማለትህ ገረማቸው ወዳጆቼ
ግዴለም አጥፋኝ እኔ ከማግኛ ስፍራ ይሁንልህ
ወትሮም ቢሆን የኔ ልብ እዲነው አይግረምህ

ቃሏን ሰታ የምትከዳ ደግሞ ምላ በፍቅር
ዳግመኛ የማገኛት እዛ የክህደት መንደር
አይግረም ያንተ መሄድ የኔን ልብ መግፋትም
እኔ እደሆን ለምጄው ልቤም አልከፋትም

እደው ግን የማዝነው መጨረሻህ የሚናፍቀኝ
ያንተነው በጊዮርጊስ በማሪያም ምሎ የካደኝ
ድሮማ ልቤ ላንተ ደስታ ቆሞ አዳሪው
ቀናትህ ላይ ወራት አመታት በፀሎቱ ጨማሪው

አንተ ግን ሲያምርብህ ዛሬህን ስታገኝ
ለነጋሪት መደነቂያ ስትባል ውብ ነው
ቃልህንም እኔምን ከድተህ ጥለኧው
ይሄው እኔም ከቃልህ ጋር ተንጠልጥዬ ቀረው

#ልደት የአቡካዬ ቃል
@fkrlene
@fkrlene
442 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 14:05:18 #የኮቴሽ ድምፅ

ሁሌ እደለመድኩት መምጫሽን ጥበቃ
ከቤቴ በራፍ ላይ ቁጭ ብዬ ካሳቤ ሳልነቃ
እጠብቅሻለው አቺ ባታውቂኝም እኔ አውቅሻለ
ይሄ ሁሉ አመት ጠርቼሽ እኳን አላውቅም
አንቺን ስጠብቅሽ ምሆነውን አላውቅም
ደርሶ አደንዝዞኝ መድረቄ ሳያንሰኝ
አንቺ እኳን ሄደሽ ዱካሽ ጠፍቶ እኔ አነቃውኝ

እደው የኔን ነገር ለእግዜር ትቼዋለው
ብቻግን እስክት መጪ ኮቴሽን እስክሰማው
ሰአታትን ገፍቼ አሁን አሁን ባደርገው
እያልኩኝ ነው በመላምት ሀሳቤ የምፅናናው
ዛሬ ግን ፊትለፊትሽ ቆሜ እነግርሻለው
አዎ ወይ የኔ ትሆኛለሽ አልያም የሀሳቤ
ብቻ እነግርሽና እገላገላለው ከምዕናብ አለሜ

#ኮቴሽ ተጀመረ …………
አንድ ሁለት እበራፌ ደረሰ መሰለኝ
ተወርውሬ በሬን ከፍቼ ፈጥኜ ወጣውኝ
እድሜያቸው የገፋ አንዲት እናት በደጄ አለፉ
በእናትነት ልባቸው ለልቤ መልዕክት እያስተላለፉ
የኔ ልጅ እድሜህ ከኔ ቢደርስ እደው ብትደክምም
በፍፁም አትልፋ እሷ ያንተ አይደለች አታገኛትም
ልፋ ቢልህ እጂ ወጣትነት ፍቅር ሆኖ
የማታውቃትን ሴት መጠበቅ እዴትስ ተደርጎ

ንግግራቸው ግራ ቢያጋባኝም ተመልሼ ገባው
ምን ለማለት ፈልገው ነው የትስ አውቀው
ደግሞስ ይሄንን ሁሉ ዘመን የጠበኳትን የምተዋት
ኧረ በፍፁም አላስበውም ሁሌም ነው ምጠብቃት
ባትመጣም ብትመጣም ደግሞ ዛሬ ደግሞ ዛሬ
ከመጠበቄም በላይ ልቤን ያጓጓው
የልቤን ሙሉ ልነግራት ቀጠሮ ይዣለው

#ኮቴሽ ቀጠለ…………
እደገና ወጣው ልቤ እየመታች
ድገት ብታገኝሽ ምትልሽን እያሰበች
ልክ ስወጣ ጎልመስ ያለ ሰው በደጄ አለፈ
እሱም ከእናቲቷ የባሰ መልዕክት ያስተላለፈ
ዛሬ ምድነው ማርፈድሽ ሳያንስ ሰአቱ መሄዱ
በደጄ የሚያልፍ ሁሉ እያሟረተ መሄዱ

ዛሬ ላይ ሆነህ ስታየው የምር አይገባህም
ምክንያቱም እሷን እጂ እራስክን አታይም
ነገ የኔ እድሜ ስትደርስ ስታስተውል
ሁሉን ነገር አጥተህ ማፍቀርህ ብቻ ሲቀርህ
ተስፋ ቢስ አድርጎ የሚያስቀርህ
ከሷ አለመምጣት በላይ ነገህ እዳይቆጭህ

በመጠበቅ መሀል ሆነ እራስህን እይ
ብትመጣም ባትመጣም ነገህን አሳይ
ፍቅሬን የማውቃት እኔ ብጎዳም እራሴ
የነሱ መጨነቅ ደርሶ ማሰብ አልታየኝም ለኔ
ብቻ የሰው ሀሳብ መቀበል ልምዴ ቢሆንም
በመናገር ቀጠሮ በዛሬ ልዩቀን ማንንም አልሰማም

ድንገት ዶፍዶፍ የሚል ድምፅ ሰማው
ግራ ተጋብቼ የደጃፌን በር ከፍቼ ወጣው
አንድ ህፃን መጥቶ የደጃፌን መብራት አበራልኝ
ዛሬምነው መብራትህን ሳታበራው አለኝ
ድጋሚ እሩጫውን ቀጥሎት ትቶኝ ሄደ
እራሴን እዳይ እያመላከተኝ ይሆን አልኩኝ
ደጃፌ ድፍን ብሎ ሳላየው የቀረውኝ

የሱ ንቃት ደውል በህፃን አምላክ ነው
ብቻ ግን የሰላም ያድርገው ዛሬ ከብዶኛል
ልትመጪ ቢሆን ብሎ አስመኝቶኛል
እውነትም ጨልሟል ግን አልመጣችም
በፍፁም እደዚህ ቆይታ አታውቅም
ከበሬ መራቄ ይሆን አልኩና እዛው ተቀመጥኩኝ
እደቆየው ያውብ የጆሮዬ ድምፅ ኮቴዋን ሰማውኝ

በሩን በፍጥነት ከፍቼ ስወጣ አየዋትኝ
በጣም ውብ ሆናለች ፀጉሯ ፊቷን ሸፈነብኝ
ጫማዋ ተፈቶ ለማሰር አጎንብሳ ነው
ቀና እስክትል ድረስ ልቤ ከኔ ወታ መሄዷነው
አስራ ጨርሳ ልክ ቀና ስትል…
የደጃፌ መብራት ድርግም
በጣም ተበሳጨው ግንኮ ብርሀን እያየው ነው
ለካስየደጃፌ መብራት የጠፋው የእግዜሩበርቶነው
ሁሌም ቢሆን ግን የኮቴሽን ድምፅ እሰማዋለው

#ልደት የአቡካዬ ቃል
@fkrlene
@fkrlene
389 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 14:04:42 #የማረሻው ቅኔ

ውዴዬ የኔ ሁሌ የምትጠይቂው
አዳዴም ከሜዳው ሽቅብ ስትመለከችው
እደው ግራ አጋብቶሽ ነብስሽን ያስጨነቃት
ልብ ባትያው እጂ እሷ ራሱ መልሱ አላት
… … … … … … #ጥያቄሽ ፩
እደው የቤሬዎቹ መታሰር ሲገርመኝ
ገበሬው እደራሱ ስሪት መምራቱ ደነቀኝ
እዲህ ነው ያልሺኝ ይሄነው ጥያቄሽ
………… #ልብበይ መልሱን ልገርሽ
በሬዎቹማ ዛሬን የምናያት እኔና አቺነን
እደ አንድ ያረጋቸው ማረሻው ያልሽው
እሱ…እሱማ አንድ ያደረገን ፍቅራችን ነው
እና በሬን ከማረሻ አዋህዶ መሪ የሆነበት
አፈርን ቀምሞ ስጋ አልብሶ ሰው ያሰኘበት
…………#የሰራው ፈጣሪሽ እሱ ነው
እደው እዳይገርምሽ ከዚህም በላይ
ጥበብ ከዚህም በላይ ግርምት በጁነው
………………… #ጥያቄሽ ፪
በርግጥ ልቤ ተደምሟል ደንቆታልም
ያሰረው ፈጣሪ ታሰሪዎቹ እኛ ከሆንም
የሚዘራውስ ዘር ከካ የሚበቅለው
ጥፋት እዲሆንም አረም የሚያበቅለው

ልብሽ የሚሻውን በደንብ አውቄዋለው
ውድዬ አድምጪኝ መልሱም ጥያቄው
ጥያቄ የፈጠረብሽ ልብሽነው መልሱ
የሚዘራውን ዘር ምድር ያመጣው እሱ
ነገንበኛ ተስፋ ዛሬን በኛው ፍሬ የሚያዩት
ልጆቻችን ናቸው በጥንድዮሽ ያፈራናቸው
ታዲ ስናሳድግ ነገንም ስናሳያቸው
ጥፋት እዲመስል የሀሳብ አረም
…………………… #አይቄሬነው

አረሙንም ነቅለን ነገን የምናሳያቸውን
እኔና አንቺ ነን በሬ አስመስሎ ፍቅርን ያለበሰን
መሪሆኖ ትናትን ዛሬን የሚያድስ
የጥበብ የፍቅር ፈርቀዳጅ የሚወደስ

የማረሻው ቅኔ ምን ሆነ መሰለሽ
በልባችን ክፍተት እዳይኖረኝ እዳይኖርሽ
ያሰረው ፍቅርነው ሁሉየሚያስደምምልሽ
በትናት ትውውቅ በዛሬውም ፍቅር
ህያዋዊ ቅኔ ፈቺው የትም የማይኖር
የኛ ሰሪው ፈቺው ፈጣሪ ብቻ ነው
እናም እናት ልብሽን አረጋጊያት
አምላክ የሰራውን የሰው ልጅ አይፈታት

ዛም ነገም ሜዳው ላይ በሬዎችን ስታያ
ከምድር አልፎ አለምን ያስጠበበው
ከቶም የማይቅበት የፍቅር ጀማረው
ዛሬም በእኔና አንቺ በማረሻው ቅኔው
……………… #ጨረሰው
እናም ማታ ማታ ጎንሽ አረፍ ሲል
ጥያቄው ሲመጣ ቤትሽን ተመልከች
ማረሻውን ሳይሆን ልብሽን አትኩሪ
መልሱ ከእሷ አለ በሰራት ፈጣሪ

#ልደት የ አቡካዬ ቃል
@fkrlene
@fkrlene
396 viewsአዶኒስ የአቡካዬ, 11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 17:05:45 Channel photo updated
14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ