Get Mystery Box with random crypto!

ፀጉራችሁን አታበላልጡ ▭▬▭ ከፊል የራስ አካልን ላጭቶ ከፊሉን መተው በእ | ፍቅር እስከ ጀነት 📝 🅡𝙖𝙢𝙖𝙨 𝙖𝙡-𝙝𝙖𝙣𝙖𝙣𝙞 🌹

ፀጉራችሁን አታበላልጡ
▭▬▭

ከፊል የራስ አካልን ላጭቶ ከፊሉን መተው በእስልምና እጅግ በጣም የተወገዘ ነው።
ይህንንም የሚያመላክት በርካታ ሀዲሶች ከመኖራቸው ጋር በአላህ ፍቃድ ጥቂቱን ብቻ ለማውሳት እወዳለሁ

عن ابن عُمر رضي اللَّه عنهُما قَالَ: "نَهَى رسُولُ اللَّه ﷺ عنِ القَزعِ" متفق عَلَيْهِ.‎
አብደላህ ኢብን ኡመር ረዲየላሁ አንሁማ እንዲህ ይላል፦
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከቀዝዕ (የራስን ግማሹን ክፍል ላጭቶ ግማሹን ክፍል ከመተው) ከልክለዋል።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

وعَنْهُ ‎ قَالَ: رَأى رَسُولُ اللَّه ﷺ صبِيًّا قَدْ حُلِقَ بعْضُ شَعْر رأسِهِ وتُرِكَ بعْضُهُ، فَنَهَاهَمْ عَنْ ذَلِكَ وَقَال: ‎احْلِقُوهُ كُلَّهُ، أَوِ اتْرُكُوهُ كُلَّهُ‎ رواهُ أَبُو داود بإسنادٍ صحيحٍ عَلَى شَرْطِ البُخَارِي وَمُسْلِم.‎
ከአብደላህ ኢብኑ ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ተይዞ እንዲህ ይላሉ፦
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የራሱን ክፍል ግማሹን ተቆርጦ ግማሹን የተወ የሆነን ህፃን ልጅ ተመለከቱ ወዲያውም ከዚህ ነገር ከለከሉት። እንዲህም አሉ
ወይ ሁሉንም የራስ ክፍል ላጩት ወይም ሁሉንም ተዉት።
ኢማሙ አቡ ዳውድ በሶሒሃቸው በቡኻሪና በሙስሊም መስፈርት ላይ ዘግበውታል

#ልብ እንበል
➲በዚህ ሀዲስ ላይ መልዕክተኛው ትንሽ ልጅ ነው፤ ምንም አያውቅም፤ ምን ችግር አለው ምናምን ብለው አላግራሩለትም። ይልቁንም ወይ ላጩት ወይ ተዉት ብለው ነው የመለሱለት። እንደ ቀላል ነገርም አልተመለከቱትም መልዕክተኛው ﷺ ።

በአሁን ግዜ ያሉት ሰዎች ወጣትነት አታሏቸው አላህንﷻ ከማያውቁ መልዕክተኛውን ﷺ ከማያውቁ ፈረንጅ ኩፋሮች ይዘው አራዳነት መስሏቸው ሸይጧን ሲጫወትባቸውና ሲያሞኛቸው ይስተዋላሉ።
ለአቅመ አዳም ላልደረሱ አካሎች ላይ ፀጉርን ግማሹን ላጭቶ ግማሹን መተው ከተከለከለ በወጣቱ ላይ እማ ሊከለከል ይበልጥ ተገቢ ይሆናል።
وعَن عَلِيٍّ ‎ قَالَ: "نَهَى رسُولُ اللَّه ﷺ أنْ تَحْلِقَ المَرأةُ رَأسَهَا" رواهُ النّسائي
አሊይ ረዲየላሁ አንሁ እንዲህ ይላል፦
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ሴት ልጅ እራሷን ከመላጨት ከልክለዋል።
رواهُ النّسائي
ፀጉራችሁን የምታበላልጡ ሰዎች ሆይ አላህን ፍሩ መልዕክተኛው ﷺ ከከለከሏችሁ ነገር አሁኑኑ በቁርጥ ተከልከሉ።
ۚ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
(ሱረቱ አል-ሐሽር - 7 )
۞ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَلَا تُبْطِلُوا أَعْمَالَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ ሥራዎቻችሁንም አታበላሹ፡፡
(ሱረቱ ሙሐመድ - 33)
عَن أبي هُريرةَ عَبدِ الرَّحمنِ بنِ صَخْرٍ رَضِي اللهُ عَنْهُ قالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يقولُ:
مَا نَهَيْتُكُمْ عَنْهُ فَاجْتَنِبُوهُ، وَمَا أَمَرْتُكُمْ بِهِ فَأْتُوا مِنْهُ مَا اسْتَطَعْتُمْ،
رواه البخاريُّ ومسلمٌ.

ከዚህ አስቀያሚ ፋርነት ተግባር አላህ ይጠብቀን

አላህ ሆይ ወጣቱ ወደ ዲኑ የሚመለስበትን ግንዛቤ ስጣቸው

መልዕክቱን ለወንድሞች አስተላልፉልኝ
ጀዛኩሙላሁ ኸይረን

https://t.me/FKR_ESKE_JENET