Get Mystery Box with random crypto!

ምድራችን ለአንተ ከአንተ በላይ እኛ እናውቃለን በሚሉ ምሁር መሰል የእውቀት ድሆች ስለተወረረች ከቶ | ፍቅር እስከ ጀነት 📝 🅡𝙖𝙢𝙖𝙨 𝙖𝙡-𝙝𝙖𝙣𝙖𝙣𝙞 🌹

ምድራችን ለአንተ ከአንተ በላይ እኛ እናውቃለን በሚሉ ምሁር መሰል የእውቀት ድሆች ስለተወረረች ከቶም አትደነቅ!

ሰዎች ተሳሳትክ እንጂ ተሳሳትኩ ለማለት አይደፍሩም። ጉድፍህን እንጂ ግድፈታቸውን አያዩም። ሰዎች ብልጥ ነን ለማለት አንተን ሞኝ ያደርጉሀል። ትልቅ ሆነው ለመታየትም ትንሽነትህን ይለፍፋሉ። ቢሆንም ግን አለማወቃቸውን ከማወቅ ቆጥረህ አትፍረድባቸው። አድሚ እንጂ አልሚ ሀሳብ በሌላቸው ሰዎች ራስህን እና ቀንህን አትበጥብጥ። ውስጥህ እስኪቆስልና መንፈስህ እስኪሰበርም ድረስ በጅሎች ጅል ሀሳብ አትበሳጭ። ምድራችን ለአንተ ከአንተ በላይ እኛ እናውቃለን በሚሉ ምሁር መሰል የእውቀት ድሆች ስለተወረረች ከቶም አትደነቅ! ብቻ አልፎ በማሳለፍ ሁሉን እለፍ። ማለፍና መቻል የማያሳልፉህ ዳገትና አቀበት አይኖርም። መቻል ስትችል ሁሉን ማለፍ ትችላለህ!

በጎነትህን እንደቂልነት ቆጥረው ሊብለጠለጡብህ ከሚሹ ፉርሾች ራስህን አርቅ። ሰዎች የአንተን እንጂ የራሳቸውን ግድፈት ፈልጎ ለማግኘት አይጥሩም። በመሆኑም ከሚያበረቱ ይልቅ በሚዝቱ እጆቻው ዝቅ እንድትል ይጫኑሀል። ለሁሉም ኮርተህ እንጂ አቀርቅረህ የማትኖርበትን አኩሪ ተግባር ፈፅም። ከሰዎች ሺ ተራ ወሬ ይልቅ የአንተን ጥቂት የተግባር ፍሬ ዘርተህ አብቅል። ልቀህና ነቅተህ ተራመድ። አቡኩቶና ጋግሮ የሚመግብህ ሰው የለም። የራስህን እንጀራ ራስህ ጋግር። የአንተ ሁነኛ ሰው አንተው ራስህ ነህ፡፡ የራስህ ትክክለኛ ሾፋሪ ራስህ ብቻ ነህ፡፡ ከማንም ምንም አትጠብቅ! ራስህን ለራስህ ብቁ አድርገው። ያኔ ራስህን ሁሉ ወድቆ ሳይሆን ሁሌ ቆሞ ታገኘዋለህ!!

https://telegram.me/FKR_ESKE_JENET