Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅረኛዬ ባለ ትዳር ናት የምንተዋወቀው ዩኒቨርሲቲ እየተማርን ነው፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ደስ | 😍ፍቅር አዲስ💖

ፍቅረኛዬ ባለ ትዳር ናት

የምንተዋወቀው ዩኒቨርሲቲ እየተማርን ነው፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል ደስ የሚል የፍቅር ግንኙነት ካሳለፍን በኋላ ትምህርት አልቆ ስንለያይ ወደተለያየ ከተማ በመሄዳችን ቀስ በቀስ እየተረሳሳን ግንኙነታችን ቆመ፡፡ ይህ ከሆነ ከስድስት ዓመታት በኋላ ስልክ ደውላልኝ አዲስ አበባ እንደመጣችና ሥራ እየፈለገች እንደሆነ ነግራኝ በምሠራበት ድርጅት ውስጥ እንድትቀጠር አገዝኳት፡፡

በመሃል በነበሩት ዓመታት ግን የሁለታችንም ህይወት ወደተለያየ አቅጣጫ ሄዷል፡፡ እኔ አግብቼ ሁለት ልጆችን ወልጄያለሁ፡፡ እሷም ትዳር ይዛ የአንድ ልጅ እናት ሆናለች፡፡ ታዲያ አንድ ቦታ እንደመሥራታችን በተደጋጋሚ እየተገናኘን የቀድሞ ፍቅራችን ማገርሸት ጀመረ፡፡

ቀስ በቀስ ደግሞ ከሥራ በኋላ የማንለያይ ሆንን፡፡ ትዳራችንን ረሳነው፡፡ ሰበብ እየፈጠርን አብረን እስከማደር ደርሰናል፡፡ ሁለታችንም በትዳራችን ላይ ምንም ችግር አልነበረብንም፡፡ አሁን ግን መጨረሻውን የማናውቀው ነገር ውስጥ ገብተናል፡፡

እንዴት እንደምናቆም ወይም ምን እንደምናደርግ አናውቅም፡፡ በጋራ ደስ የሚል ጊዜ እያሳለፍን፣ በትዳሮቻችን ላይ አደጋ ፈጥረን ግራ እንደተጋባን ቀጥለናል፡፡

ምን እናድርግ?
ቢ.ዲ. ነኝ