Get Mystery Box with random crypto!

የላይብረሪዋ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ አጠናለሁ ብዬ ከገባሁበት ቤት ልቤን አሸፈትሽው ባክሽ | 💋የዲያሪ ላይ ጥቅሶች❤️

የላይብረሪዋ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

አጠናለሁ ብዬ ከገባሁበት ቤት
ልቤን አሸፈትሽው ባክሽ የኔ እመቤት
ድምፅሽ ከፍ ብሎ ወደኔ ቢመጣ
ብድግ አልኩኝና ውዴ አንቺን ልቆጣ
ግን ገና እንዳየሁሽ ልቤ ጥሎኝ ወጣ
ምን አይነት ውበት ነው ያደለሽ ፈጣሪ
ልብ የሚያሸፍት ነው ሆነሽ ላይብረሪ
ሚጠናበት ቦታ መሆኑን ባላጣም
ሳልነግርሽ አላልፍም ቆንጆ ነሽ ግን በጣም።


#ሼር

𝙟𝙤𝙞𝙣 𝙪𝙨