Get Mystery Box with random crypto!

Mesfin mekuria @ GBSS

የቴሌግራም ቻናል አርማ fit2012 — Mesfin mekuria @ GBSS M
የቴሌግራም ቻናል አርማ fit2012 — Mesfin mekuria @ GBSS
የሰርጥ አድራሻ: @fit2012
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.97K
የሰርጥ መግለጫ

GELAN BOYS BOARDING SECONDARY SCHOOL
For any Question & comment 👉👉👉
@SchoolgofaBot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-17 17:34:36 የኮኬት ገንዘብ ቁጠባ ብድር ህብረት ስራ ማህበር አባላት ከተመሰረተ በ6ወሩ ከ500ሺ ብር በላይ የሰበሰበ ሲሆን የአባላት ብዛት 152 ሲሆኑ መንኛውም የኢትዮጵያዊ በማህበሩ ደንብ መሠረት ቆጥቦ መበደር ይችላል ለበለጠ መረጃ በአካል አቶ መስፍን መኩሪያ እና ተገኔ ገዛኸኝን ወይም የማህበሩ አባላትን አነጋግሮ መረጃ ማግኘት ይችላሉ ፡፡ ፎቶውን ይመልከቱ
1.7K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:47:06 ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሁለቱም ትምህርት ቤት መስታወቂያዎችን እንገልፅለን፡፡ ምዝገባን በተመለከተ
2.2K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:13:43 ማስታወቂያ
ለፍሬህይወት ቁጥር 2 እና ለፊታውራሪ ላቅ አድገህ ተማሪዎች በሙሉ
የነባር ከ10ኛ-12ኛ ክፍል የተማሪዎች ምዝገባ ከ16/12/2014 ዓ.ም ጀምሮ ይከናወናል፡፡
3.1K views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 09:47:04 ቀን 15/11/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ ፡፡

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 64.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆናል፡፡

ለውጤቱ መመዝገብም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን እያቀረበ ከሰኞ ማለትም ከ18/11/2014 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታችሁን በቀጣይ በምናሳውቃችሁ አድራሻ አማካኝነት ኦላይን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡
500 views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 09:10:34


ለፈገግታ / የቱን መጽሀፍ ?

ልጅቷ የቤታቸው በር ይንኳኳና ስትከፍተው ቦይፍሬንዷ ነው፤

ግን አባትዋ በቅርብ ርቀት ሰለነበሩ በስነ-ስርአት ሰላም አላለችውም

ወዲያውኑም ልጁ እንዳይቀባጥር በኮድ

እሷ፦ሀይ ሰላም ነው "አባቴ እቤት ነው" የሚለውን የበውቀቱ ስዩም መፅሀፍህን ልትወስድ መጥተህ ነው?
.
ልጁ፦ወዲያውኑ ነቄ ይልና እር እኔስ
የበአሉ ግርማን
"ታዲያ የት ልጠብቅሽ" የሚለውን መፅሀፍ ልወስድ ነበር።
.
እሷ፦ውይ እሱን መጽሀፍ እንኳን ቶሎ አላገኘውም ባይሆን ያአዳም ርታን "ከማንጎው ዛፍ ጥላ ስር" የሚለውን ልስጥህ
.
ልጁ፦ጥሩ በዛው"እንደ ደርስኩ እደውላለሁ" የሚለውን መጽሀፍም እንዳትርሽው.
.
እሷ፦እር ምንም ችግር የለም
የይስማክ ወርቁን "ቶሎ መጣለሁ ጠብቀኝ" የሚለውንም ይዥልህ መጣለሁ:............
ልጅቷ በሩን እንደዘጋች አባቷ አስቆማትና

አባት፦ በጣም የሚገርም ነው ይህንን ሁሉ መጽሀፍ ያነባል?
.
እሷ፦ አወ አባየ እንዲት ያለ ስማርት ልጅ መሰለህ!
.
አባት፦በጣም ደስ ይላል እንደዛ ከሆነማ እኔም አንድ መጽሀፍ ልስጥሽና ትወስጅለት አለሽ:
.
እሷ፦ እሽ አባየ የቱን መጽሀፍ ?
.
.
አባት፦ እዛ መደርደሪያ ላይ ሀዲስ አለማየሁ የፃፈው "በናተ ቤት በኮድ አውርታችሁ ልባችሁ ውልቅ ብሏል" የሚለውን!

┈┈┈••✦✦••┈┈┈
1.2K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 16:33:19 ማጠናከሪያ ትምህርት ተጀምሯል፡፡
1.0K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 12:15:02
ይቀጥላል ገና መች ተነካና፤
ስላኮራችሁን በጣም ደስስስስ ብሎናል።

በሁለት ወርቅ በአንድ ብር
ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን!!!
1.1K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 11:08:56 ህይወት ምርጫ ፣ ሂደት እና ውብ ናት ! ! !

የምንሻውን ለማግኘት

1. የምንፈልገውን በግልፅ ማስቀመጥ
2. በየዕለቱ የምንፈልገው ላይ ትኩረት ማድረግ / በፅሁፍ ፣ በምስጋና፣ በምናብ እናተኩር
3. ተግባራዊ ዕቅድ አውጥተን በየቀኑ መሰረታዊ ተግባር ላይ በወጥነት እንተግብር
4. በማንኛው ሰዓት ንቁ ሆነን የሚሰጠንን የመሻታችንን መልስ ለመቀበል ፍፁም አገልጋይ እንሁን
5. ሁሌም ማስታወስ ያለብን የዘራነው እንደሚበቅል ነው - ገበሬ ዘሩ እንዴት መሬቱን ሰንጥቆ እንደሚወጣ አያውቅም የሚያውቀው ቢኖር የዘራው ካጠጣው ፣ ከተንከባከበው ፣ አረሙን ከነቀለ ፣ ግብዓቱን ከሰጠ እንደሚበቅል ብቻ ነው። እንዴት የሚለው የተፈጥሮው ባለቤት( የፈጣሪ ) ነው ። የእርሱ ትልቅ ድርሻ ዘር መምረጥ ላይ ነው ። በየቀኑ ምን እየዘራን እንደሆነ አስተውለን የምንሻውን ብቻ እንዝራ ከዛም ፈጣሪም ለተፈጥሮ ዘርም ለመዳረሻው ምን ያህል የታመኑ እንደሆኑ እንገነዘባለን ።
ሁሉም የዘራውን ስለሚያጭድ ተማሪዎች ትምህርታችሁ ላይ አትኩሩ ፡፡
┈┈┈••✦✦••┈┈┈
1.1K views08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 11:03:37 ከ10ኛ ወደ 11ኛ ክፍል አልፋችሁ ማጠናከሪያ ትምህርት የምትማሩ ተማሪዎች ሶሻል እና ናቹራል የምትገቡበትን ክፍል ከወላጆቻችሁ ጋር በመነጋገር ወስናችሁ ማጠናከሪያ ትምህርት ላይ ሰኞ ተገኙ ፡፡
996 views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ