Get Mystery Box with random crypto!

ኖላዊነ ኄር ኖላዊነ ሔር መድኃኔዓለም ለነፍስ ወለ ሥጋ ወለ ኵሉ ዓለም ዕቀበነ (3) ለዓለመ ዓለም | የጃቴ ኪዳነ ምሕረት የፍኖተ ሰማዕታት ሰንበት ት/ቤት መዝሙር ክፍል

ኖላዊነ ኄር
ኖላዊነ ሔር መድኃኔዓለም
ለነፍስ ወለ ሥጋ ወለ ኵሉ ዓለም
ዕቀበነ (3) ለዓለመ ዓለም

ድምጼን ይለዩታል በጎቼ በሙሉ
አይስታቸውም መንገደኛ ሁሉ
በራሱ በአምላክ የተባለላችሁ
በጎች ተሰብሰቡ ወደ በረታችሁ

አዝ =========

ነቢይ ነኝ የሚል የሰፈር ዜናዊ
አድርጎ የሾመ ራሱን ወንጌላዊ
ነጣቂ ተኩላው ተበራክቷል እና
መንጋህን ጠብቀው በእምነት እንዲጸና

አዝ ===========

ከአምላክ የተላከ እውነተኛ እረኛ
ለመንጋው የሚያስብ ያይደለ ምንደእኛ
ፊት የተማረ ነው ኋላም የተሾመ
በሐዋርያዊ ክህነት በእውነት የታተመ

አዝ ===========

ከጌታ የመጣ ካልሆነ ክህነቱ
ከአበው የተለየ ከሆነ ትምህርቱ
በበሩ ያልገባ ሌባ ነው ስላለ
ምእመናን አትስሙት አሳቹ ስላለ

አዝ ==========

ጩኸታችን ሰምተህ ጭንቀታችን አይተህ
በየዘመናችን የሚታደግ ልከህ
እውነተኛ መምህር የበጎች እረኛ
አንተው አሰማራን ተመልከት ወደ እኛ