Get Mystery Box with random crypto!

​​ቅንዑ ቅንዑ ለእንተ ተዐቢ ጸጋ(፪) መድኃኒት ለነፍስ(፪) መድኃኒት ኪዳነምሕረት ለምልማ | የጃቴ ኪዳነ ምሕረት የፍኖተ ሰማዕታት ሰንበት ት/ቤት መዝሙር ክፍል

​​ቅንዑ

ቅንዑ ለእንተ ተዐቢ ጸጋ(፪)
መድኃኒት ለነፍስ(፪)
መድኃኒት ኪዳነምሕረት

ለምልማ የታየች የአሮን በትሩ
የአዛኝቷ ነገር ድንቅነው ምስጢሩ
ከሴቶች ተመርጣ ንጹሕ ስለሆነች
በንጽሕናዋ እሳትን ታቀፈች
አዝ = = = = =
ስምሽን የጠራ ዝክርሽን ዘክሮ
ይኖራል በገነት አይቀርም ተባሮ
እኛም እናምናለን በቃል ኪዳንሽ
አይረሳንምና መሐሪው ልጅሽ
አዝ = = = = =
ስወለድ ጀምሮ ጨቅላ እንኳን ሆኜ
እስካሁን አለሁኝ ኪዳኗን አምኜ
እሷን በማመኔ ሁሉ ተሰጥቶኝ
ዘወትር እኖራለሁ ምንም ሳይጎድለኝ
አዝ = = = = =
እንኳን ላመነባት ለሚከዳት አዛኝ
እንደ ኪዳነምሕረት የት አለ የሚገኝ
ከደጇ ላይ ወድቀን ስሟን ስናነሳ
ይሰረይልናል መርገምና አበሳ

(=>ለምትበልጠው ፀጋ ቅኑ
የነፍስ መድኃኒት ለሆነች ኪዳነ ምሕረት)


ዲያቆን የማነብርሃን ግርማ

"የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ"
፩ ቆሮ ፲፪:፴፩