Get Mystery Box with random crypto!

[ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዛሬው ዕለት ከተናገሩት የተወሰደ] 'ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን | Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ።

[ብፁዕ አቡነ አብርሃም በዛሬው ዕለት ከተናገሩት የተወሰደ]

"ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መፈጠሩን ማወጃችን ይታወሳል። በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የምንሰማቸው ነገሮች ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን እየሰማን ነው

"ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ አዲሱ ሲኖዶስ በሚል አዲስ ስም እስካሁን ከሚጠቀሙበትም ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የኤጲስ ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል። ሀይማኖቱንም ሕጉንም መልሰው መላልሰው ጥሰውታል።ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል። ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል። ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል። በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ"

"አስተሳሰባቸው አነጋገራቸው ሁሉ በእኩል ደረጃ እንደሆኑም ተናግረዋል። 25 የተባሉትም የትናንትና ካህናት አገልጋዮች አሁንም ኤጲስ ቆጶሳት እንደሆኑ ተደርጎ ተንጸባርቋል። ዘጠኝ ሰዓት ላይ ይህንን አድርገው ቀኑን ሙሉ አንመጣም ሲሉ ዉለው 10 ሰዓት ላይ ግን ለማንም ለማን መጣን ሳይሉ ቤታቸው ውስጥ[ቤተ ክህነት] ገብተዋል። ... ቤተ ክርስቲያንም እስቲ ሁሉንም ነገር በትዕግሥት እንየው በማለት ዝም ብለን እየተመለከትን ነው። ስለዚህ ሕግን የጣሰ ሰው ስምምነትን ያፈረሰ ሰው ዛሬም ደግመው ደጋግመው እውነት ለማስመሰል ሐሰትን በሚለፍፉ ሰዎች እንዲህ ዓይነት ድፍረት የሚመለከተው አካል ሊመለከተውና አሁንም በቃ ሊለው ይገባል ብለን መልእክታችንን እናስተላልፋለን።"