Get Mystery Box with random crypto!

#ህይወትና_ግምት ወንደላጤ እያለሁ 'ሳገባና ፍቅረኛ ሲኖረኝ' ባዶነቴ እንደሚሞላ፣ አሁን 'የሚ | ፍልስፍና ከፈላስፎች💆

#ህይወትና_ግምት

ወንደላጤ እያለሁ 'ሳገባና ፍቅረኛ ሲኖረኝ' ባዶነቴ እንደሚሞላ፣ አሁን 'የሚደብረኝና የሚሰለቸኝ' ነገር እንደሚቀር አስብ ነበር፡፡

ከፍቅረኛዬ ጋር ግንኙነት ስጀምር ብቻዬን መሆንን 'ቻዎ' አልኩት...ግን ግን ብቸኝነት ይናፍቀኝ ጀመር! እየተጣሉና እየተኳረፉ መኖር ሰለቸኝ፣ አንገፈገፈኝ!

ባህሪዬ ቁጥብና ጭምት አይነት ስለነበር የማገኛቸዉ ሴቶች ደግሞ ተግባቢና ለፍላፊ አይነት ባህሪይ ያላቸዉ ነበሩ፡ ትርፍ የምለዉን ጊዜ እንኳን ሳይቀር ይዘዉብኝ እንደዚህ ሆኖ መቀጠል ሞት ሆኖ ታየኝ...እንዴት ብዬ ለራሴ ላስብ?

አሁን ተመልሼ የብቸኝነትን ኑሮ እየኖርኩት ነዉ፤ደስተኛ ነኝ፡፡ መጀመሪያ እንደነበረኝ አይነት የብቸኝነት ጊዜ እያሳለፍኩ አይደለም...በራሴ ነገሮችን ስርአት እያስያዝኩ ደስ ብሎኝ አለሁ፡፡

ደስተኛ ያልሆንክበትን ማንነት ሌሎች መጥተዉ ደስተኛ እንዲያደርጉህ አትጠብቅ፡፡ ፍቅረኛህ አንተን ደስተኛ የማድረግ አቅሟ ዝቅተኛ ነዉ፡፡ የቱንም ያህል ብትዋደዱ ከራስህ የመነጨ የደስታ ስሜት ካልፈጠርክ እሷ ልትፈጥርልህ አትችልም፡፡

ስታዝን በራስህ፣ ደስ ሲልህም እንዲሁ በራስህ እያደረክ ካላለማመድከዉ እዉነቴን ነዉ የምልህ ማንም ሊያስደስትህ አይችልም፡፡ እንደዉም ተጨማሪ ራስ ምታት፣ ተጨማሪ ቁርጥማት፣ ተጨማሪ ሆድ ቁርጠት ይሆኑብሃል፡፡

ላንቺም ለእህቴ እዉነቱ አንድ አይነት ነዉ፡፡ብቻዬን ስለሆንኩ ነዉ ያዘንኩት ብለሽ ፍቅር ብትጀምሪ ያ ያሰብሽዉ ሰዉ አይሞላዉም..

እግዜርን በደስታ እንዲሞላሽ እጆችሽን ዘርግተሸ ጠይቂ እንጂ ከፍጡር ለዛዉም 'ዛሬ እብድ ብዬልሽ ልሙት!ብሎ ማታ ደግሞ 'ሰለቸሽኝ' ከሚልሽ ተባእት ደስታን አትጠብቂ፡፡

መጀመሪያ በራስሽ ቆመሽ ፍቅር ብትጀምሪ ያምራል..ግንኙነቱም 'ከህፃናት ኩርፊያ ወደ ጎመራ ፍቅር ያድጋል፣ይለወጣል፣ይጠነክራል ማለት ነዉ፡፡