Get Mystery Box with random crypto!

#ዕድሌ_ነው... ዕድሌ ነው... በሚስት ልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤ ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድ | ጥበብ

#ዕድሌ_ነው...

ዕድሌ ነው...
በሚስት ልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤
ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድም ሴት አትገኝ
ዕድሌ ነው...
እኔ ዲግሪ ስይዝ፣ ዲግሪ ዋጋ ያጣል፤
ገንዘብ ያለው ሁሉ፣ ዶክትሬት ያመጣል
ዕድሌ ነው...
እኔ መድረክ ስይዝ፣ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ፣ ይሆናል ትንሣኤ።
ዕድሌ ነው...
በቁርባን ለመኖር፣ ንሰሐ ስገባ፤
አቁራቢው ፖትልኮ፣ ቤተመንግሥት ገባ።
ዕድሌ ነው...
እኔ ኳስ ስገዛ፣ ሜዳው ይታረሳል፤
እኔ ቤት ሲኖረኝ፣ ሰፈሬ ይፈርሳል።
ዕድሌ ነው...
ለተሾመ ሁሉ፣ እንዳልኖርሁ ስለፋ፤
እኔ አለቃ ስሆን፣ የሚታዘዝ ጠፋ።
ዕድሌ ነውና...
ከዕለታት አንድ ቀን፣ መንገሤ ባይቀርም፤
እኔ ንጉሥ ስሆን፣ ሀገሪቱ አትኖርም።

* * * *
#ገጣሚ_መላኩ_አላምረው

@filsifina000
@filsifina000
@filsifina000